አዲሱ ካቢኔ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ተናገሩ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት መደበኛ ጉባኤውን ሲያካሂድ አዳዲስ የካቢኔ ዕጩዎችን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የካቢኔ አባላት ሹመት በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም አንድ የካቢኔ አባል ብቻ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ሁለት አባላት እንዲኖሩት መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በዚሁ ሹመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሐረሪ ክልል ተወላጅ በሚኒስትር ደረጃ እንዲሾሙ መደረጉን ጠቁመዋል።
ከአካታችነት አንጻር አሁንም ያልተሟሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖም ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር ትልቅ መሻሻል መኖሩን ገልጸዋል።
አክለውም ሹመቱ ቅድመ ሁኔታዎችና መስፈርቶች ግምት ውስጥ የገቡበት መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመታቸው ለጸደቀላቸው አዳዲስ ሚኒስትሮች መጪው የስራ ጊዜ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ በመጠቆም በትኩረትና በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በተመስገን ተጋፋው
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

11 hours ago