በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገፁጿል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ወደ አፋር ክልል በመጓጓዝ ላይ መሆኑንም ነው የተገለፀው።
ለተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ መሆኑን ያነሳው ኮሚሽኑ የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ሲል ነው ያስታወቀው።
በዚሁ መሠረትም በአፋር ክልል የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ በማድረስ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የአፋር ክልል በራሱ አቅም የሚያደርገው ድጋፍ እና ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑም የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑንና ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ አፋር ክልል መንቀሳቀሳቸውን ጠቁሟል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

2 days ago