በኢትዮጵያ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ምጣኔ ከ4% በላይ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ሕጉ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከነበረው ቢቀንስም፣ አሁንም ከ4% በላይ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ፣ የቤተሰብ እቅድ እና አፍላ ወጣቶች ባለሙያ አቶ በሪሁን ስባጋዲስ እንደገለጹት፣ ከ60% በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ደኅንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
እንደ ሀገር ደኅንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ለማቋረጥ ፆታዊ ጥቃት ሲያጋጥም፣ የእናትየውን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ ከተረጋገጠ እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸው አቶ በሪሁን አስገንዝበዋል።
በአይፓስ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት በተከበረው ዓለም አቀፍ ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ቀን ላይ የአይፓስ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ደመቀ ደስታ፣ ተቋማቸው ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እየሠራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ደኆንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥን ተደራሽ ለማድረግ አይፓስ ከ20 ሺህ በላይ ባለሙያዎችን በማሰልጠን እንዲሁም ከ1,600 በላይ የሚሆኑ ጤና ተቋማትን በመደገፍና ግብዓት በማሟላት ላይ ይገኛል።
በተጨማሪም ድርጅቱ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል፣ የስነ-ተዋልዶ ጤናን ለወጣቶች እና ለአካል ጉዳተኞች ማዳረስ እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ እየሰራ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በቃልኪዳን ኃይሌ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

1 day ago