Logo
AHADU RADIO FM 94.3
በትምህርት ቤቶች የዓይን ምርመራ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

‎ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት አንድ ተማሪ የሚያገኘው እውቀት እና መረጃዎች ከ 80 በመቶ በላይ የሚሆነው በአይን ለመረዳት የሚያስችል በመሆኑ የእይታ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች የሚፈለገውን ያህል ክህሎት እንዳይኖራቸው ተግዳሮት እንደሚሆን ተገልጿል።

በ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራት ፕሮግራም ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዩሐንስ ወጋሶ
የማየት ችግር የሚያጋጥማቸው ተማሪዎች ችግር ለመፍታት በትምህርት ቤቶች የዓይን ምርመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አንድ ተማሪ የዕይታ ችግር ካለበት የትምህርት አቀባበሉ ዝቅተኛ የሚሆንበት እድል በመኖሩ እንደሀገር አሉታዊ ተፅኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የአይን ምርመራ የሁሉም ዜጋ ቀዳሚ ትኩረት መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
                   
በትምህርት ቤቶች ላይ የሚደረገው የዓይን ምርመራ ውጤታማ እንዲሆን መምህራን ማሰልጠን እንደሚገባ አንስተው በቀላሉ የተማሪዎች ችግር እንዲለዩ ያስችላል ብለዋል።

የዓይን ምርመራ ስራ በዘመቻ የሚካሄድ ሳይሆን መደበኛ በሆነ መንገድ ለነባር ተማሪዎች እና አዳዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች ምርመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ይሄ ተግባራዊ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የትምህርት ቤት ጤና እስትራቴጂ በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓለም ለ 26 ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ 18ተኛ ጊዜ የአለም አቀፍ የአይን ጤና ቀን ባለፈው ሳምንት በመከሩ ይታወቃል።

በህይወቴ ጌትነት

#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
16 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.