Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የታካሚዎች ዲጂታል መረጃ አያያዝ እና ጥበቃ የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት ያሟላ እንደሆነ ተገለጸ

መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ የታካሚዎች ዲጂታል መረጃ አያያዝ፣ ደህንነት እና ሚስጥራዊነት ጥበቃ የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት እንደሚያሟላ በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገመቺስ መልካሙ ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል።

በተጨማሪም፤ ሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የታካሚዎች መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓቶች እንደምትከተል አብራርተዋል።

የመጀመሪያው "ዲ ኤች አይ ኤስ ቱ" የተባለው ሥርዓት ሲሆን፣ በጤና ተቋማት የታካሚዎችን ጠቅላላ መረጃ የሚሰበስብና በሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚጋራ ነው።

ሁለተኛው "ኤሌክትሮኒክ ኮሚኒቲ ኸልዝ ኢንፎርሜሽን ሲስተም" ደግሞ በገጠር ጤና ኬላዎች የሚያገለግል ሲሆን፣ እስከ አሁን የ31 ሚሊዮን ሰዎችን የግል መረጃ መመዝገቡ ተጠቅሷል።

የታካሚዎችን የግል የጤና መረጃ ባለሙያዎች ብቻ እንዲመለከቱት ይደረጋል የተባለ ሲሆን፤ በብሔራዊ ደረጃ ቁጥራዊ መረጃዎችን ብቻ የሚያሳየው ይህ አሠራር፣ የዓለም ጤና ድርጅት የታካሚዎች መረጃ ደኅንነት ጥበቃ መስፈርትን እንደሚያሟላ ተገልጿል።

ሥርዓቱ የታካሚዎች የግል የጤና መረጃ ከጤና ተቋሙ ውጪ አገልግሎት ላይ እንዳይውል በቪፒኤን በተሰኘ ኢንተርኔት በሌለባቸው አካባቢዎች ኢንተርኔት ለመጠቀም በሚያስችል ኔትወርክ እንዲሠራ መደረጉንም አቶ ገመቺስ አብራርተዋል።

በመሰረት ሙሉ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.