Logo
AHADU RADIO FM 94.3
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 23 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ

👉🏽 በ 2018 ዓ/ም ብቻ 86 ሺ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

‎ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በሴቶች እና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ  በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ  በሳምንት ውስጥ 3 ቀን  የ9 ዙር በረራዎች መኖሩን ገልጸዋል ።

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በትክክል መጥቀስ እንደማይቻል ገልጸው በርካታ ዜጎች ምቹ ባልሆነ እና  አንድ ቦታ የሚቀመጡበት እስርቤት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

እኚሁ ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ስነ ልቦናዊ ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጠቅሰው በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በ2019 ዓ.ም በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ መካከል ከ23 ሺ በላይ  ዜጎች መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ለተመላሽ ዜጎች ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እንዲሁም የግንዛቤ ፈጠራ ፣ የስነ ልቦና ስልጠና እና ሌሎችንም ማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በ ቃልኪዳን ኃይሌ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
20 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.