በኢትዮጱያ ዓመት 19 ሺ ሴቶች በጡት ካንሰር ሲያዙ ከ9 ሺ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ተገለፀ።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ህይወት ሰለሞን 70 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ወደ ጤና ተቋም የሚሄዱት የካንሰር በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ በኋላ በመሆኑ የሞት መጠኑ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።
የጡት ካንሰርን ለመከላከልም ሆነ በጊዜ ለማከም መደበኛ በሆነ መልኩ የቅድመ ምርመራ ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኢትዮጱያ በዓመት 19 ሺ ሴቶች በጡት ካንሰር ሲያዙ ከ9 ሺ በላይ የሚሆኑት ሂወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
የህመም ስሜት ከመጀመሩ በፊት ሴቶች ራሳቸውን በራሳቸው የሚመረምሩበት እንዲሁም በጤና ተቋም በመሄድ ቅደመ ካንሰር ምርመራ የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ ስላለ ይህን እድል ሊጠቀሙ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሞት ቁጥሩ ከፍተኛ መሆኑ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም መሄዳቸው የሚያሳየው በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን ነው ብለዋል።
በመሰረት ሙሉነህ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

2 days ago