ኢትዮጵያ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን ማጣራት የሚችል ፋብሪካ ሥራ አስጀመረች
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ ጀምሯል ።
በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካው፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከርና የሰለጠነ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ፋብሪካው የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ከመደገፍ ባለፈ፣ በውድ ማዕድናት ማጣራት ዘርፍ ኢትዮጵያን የቀጣናው ማዕከል ለማድረግ እንዲሁም ግልጽና ተወዳዳሪ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት እንደሚያግዝ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል ።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

2 days ago