Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የአቢሲኒያ ባንክ አጠቃላይ የሀብት መጠን ከ 381 ቢሊየን ብር በላይ ደረሰ

👉 ባንኩ በ 2018 ብቻ ከ 143 ሚሊየን ብር በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) አቢሲኒያ ባንክ 30ኛ መደበኛ እና 17ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዎኖች ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በአድዋ ሙዚየም እያካሄደ ይገኛል።

በዚህ ወቅት የባንኩን የ2018 አመታዊ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድሊቀመንበር አቶ መኮንን ማንያዘዋል “የ 2018 የሒሳብ አመት በሀገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የኢኮኖሚ ጫናዎች የነበሩ ቢሆንም ተቋቁመን ማሳለፍ ችለናል” ብለዋል።

ባንኩ በዓመቱ 15.85 ቢሊየን ያልተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ጠቅላላ ሀብት መጠን 381.5 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቋል።

አቢሲኒያ ባንክ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ከተለያዩ ማህበራት ጋር እንደሚሰራ ጠቅሰው በዓመቱ በአጠቃላይ 143.7 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደተደረገ ተናግረዋል።

በመሰረት ሙሉ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.