22 hours ago
🎉🎉 30ኛ ዙር የትዊተር #ንቁ_ተሳታፊ አሸናፊዎች!!
✅ አሁንም የኢትዮ ቴሌኮምን https://x.com/ethiotelecom እና ቴሌብር የትዊተር ገጾች https://x.com/telebirr በመከተል መልእክቶችን ላይክ፣ ኮመንት፣ ሪፖስት እንዲሁም ሼር በማድረግ 10 ጂቢ ወርኃዊ የኢንተርኔት ጥቅል በዕጣ ያሸንፉ!
📥 አሸናፊዎች በትዊተር ገጾቻችን በውስጥ መልእክት (DM) የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን!
#ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

1 day ago
ሼር
ዛሬ አንጠብቃችዃለን በ 12 ሰዓት በአለም ሲኒማ ይምጡ አብረን እንሳቅ ትኬቱ ቀድሞ ሊያልቅ ስለሚችል ከሁሉ በጄ ወይም ከአለም ሲኒማ በር አሁኑኑ ቀድመው ወንበርዎን መርጠው ትኬትዎይ ይግዙ

3 days ago
የፈረሰውን የአማኑኤልን ቤት አብረን እንሥራ!
(የደሀና ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የማደስና የዕርዳታ ጥሪ)
የጥሪው ጭብጥ
ለብዙ ዘመናት የእግዚአብሔር ቃል ሲነገርበትና ምእመናን ሲገለገሉበት የቆየው የደሀና ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን መቅደስ በአሁኑ ወቅት በመፍረሱ ምክንያት ታሪካዊውና ቅዱሱ ቦታ የምስጥና የሸረሪት መኖሪያ ለመሆን በቅቷል።
የአካባቢው አባቶችና ምእመናን የፈረሰውን የእግዚአብሔር ቤት እንደገና ለመሥራት፦
«የአማኑኤል ወዳጆች የት አላችሁ? እጃችሁን ዘርጉልን፤ የፈረሰውን ቤቱን አብረን እንሥራ!» በማለት አጣዳፊ የድረሱልን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
እንዴት መደገፍ ይቻላል?
ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ እንደየአቅማችን፦
በገንዘብ እርዳታ፦ ከ200 ብር ጀምሮ አነሰ፤ በዛ ሳንል ካለን ላይ በማካፈል፣
በአስራትና በበኩራት፦ የገጠሪቷን ቤተክርስቲያን በማሰብና በመደገፍ የበረከቱ ተካፋይ መሆን እንችላለን።
የባንክ ሂሳብ ቁጥር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000781694588
የሂሳብ ስም: የደሀና ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን
ለበለጠ መረጃ እና ለጸሎት
ስልክ ቁጥር: 0941929014
(እርዳታ ያደረጋችሁ ምእመናን የክርስትና ስማችሁን በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ በዚሁ ስልክ ቁጥር በመላክ በኪዳን፣ በሰዓታት፣ በቅዳሴና በጸሎት አባቶች እንዲያስቡአችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።)
መልእክቱን ሼር (Share) በማድረግ የጽድቁ ተካፋይ ይሁኑ!
Sponsored by
Surafel
5 days ago
🚨😱 በአዲስ አበባ የመሰረተ ልማት ዝርፊያ ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል?
ይህ ቪዲዮ የሚያሳየው ሰሚት ኮንዶሚኒየም (ኤል ጂ ኮሌጅ አካባቢ) የተፈጸመውን አሳዛኝ የንብረት ዝርፊያ ነው! ከዚህ ቀደም በመንገድ መብራት ምሰሶዎች (ፖሎች) ላይ የነበሩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ተዘርፈው ምንም ዓይነት የእርምት እርምጃ እና ቁጥጥር ባለመደረጉ፣ አሁን ደግሞ ሌቦች ዓይን ባወጣ ድፍረት መሬት በመቆፈር የከርሰ ምድር የመንገድ ዳር መብራት ገመዶችን በቪዲዮው በምታዩት መልኩ ዘርፈው ወስደዋል!
ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ መሠረት፤ በዚህ ጥፋት ምክንያት በግቢው ውስጥ ያሉት የመንገድ ዳር መብራቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
አካባቢው በጨለማ በመዋጡ ለነዋሪዎች ደህንነት እጅግ አስጊ ሆኗል!
ይህ የህዝብ እና የሀገር ሀብት ውድመት ዝም ተብሎ ሊታለፍ አይገባም! ቪዲዮውን ሼር (Share) በማድረግ ለሚመለከተው አካል ድምጻችንን እናድርስ! #addisababa #ethiopia #summitcondominium #addisababacity #ethiopiannews
10 days ago
አንድ ቤተሰብ… አንድ ሕይወት… የእኛን እርዳታ ይጠብቃል!
አቤል መለሰ በትምህርቱ የላቀ ውጤት ያስመዘገበ፣ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በትጋት ሲዘጋጅ የነበረ ብሩህ ተማሪ ነበር።
ይሁን እንጂ ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመለስ፣ በፒያሳ ሀገር አቀፍ ቲያትር አካባቢ ከተገነባ ሕንፃ 13ኛ ፎቅ ላይ የወደቀ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ከባድ ቁስ በራሱ ላይ በመውደቁ ከባድ የራስ ቅል ጉዳት ደረሰበት።
በላንሴት ጠቅላይ ሆስፒታል የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ቢደረግለትም፣ ከአደጋው በኋላ ለ7 ወራት ያህል እስካሁን ድረስ በአልጋ ላይ ራሱን ስቶ ይገኛል።
መጀመሪያ የሕክምና ወጪውን የሸፈነው ተቋራጭ በኋላ ድጋፉን በማቋረጡ፣ ቤተሰቡ አሁን ከፍተኛ የሕክምና ወጪ ጫና ውስጥ ገብቷል።
ዛሬ አቤል ሕይወቱን ለማዳን የእኛን እገዛ ይሻል። 🙏
እባክዎ በሚችሉት መጠን ያግዙ። የእርስዎ ትንሽ ድጋፍ ለአቤል ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።
የባንክ ሒሳብ (CBE)
እታለማሁ አሰፋው ወ/መድኅን (ወላጅ እናት)
1000348860538
+251-911-398024 / +251-931-534451
እባክዎ ይህን መረጃ SHARE በማድረግ ለብዙ ሰዎች ያድርሱ። ምናልባት የእርስዎ አንድ ሼር ወይም አንድ አስተዋጽኦ የአቤልን ሕይወት ለማዳን ወሳኝ ሊሆን ይችላል።
ፈጣሪ የሚረዱትን ይባርክ።
Via: ቤተሰቡ

11 days ago
የአፋልጉኝ ተማጽኖ
#ethiopia | እናታችን ፋንዬ ሽፈራው ትላንት ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ገደማ በላፍቶ 2ሺህ አካባቢ የእግር ጉዞ ለማድረግ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።
የለበሱት ልብስ: ሙሉ ጥቁር
የመጨረሻ የታዩበት ቦታ: ላፍቶ 2ሺህ አካባቢ
ያያችሁ፣ ያለችበትን የምታውቁ ወይም ፍንጭ ያላችሁ ወገኖች እባካችሁን በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ደውላችሁ በመጠቆም እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን፦
+251-913- 810057
+251-913 -63 44 40
+2519 -93-93 82 92
(ፈላጊ ልጆቻቸው)
#ሼር #share

14 days ago
የአፋልጉኝ ተማጽኖ – እባካችሁ ተባበሩን
#ethiopia | ማስተዋል መልሰው አጥናፉ (በቅጽል ስሟ ሚሚ) ትባላለች። ትንሽ የአዕምሮ ሕመም አለባት።
በ2018 ዓ.ም. ሐምሌ 14 ጠዋት እንደተለመደው በአራብሳ የሚገኘውን አቡዬ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ከቤቷ ወጥታ ከዚያ በኋላ አልተመለሰችም።
በዕለቱ የለበሰችው፦
- ሙሉ ነጭ ቀሚስ
- ነጭ ነጠላ
- ነጭ ሲሊፐር ጫማ
የጠፋችበት አካባቢ አራብሳ ቢሆንም፣ በየትኛውም አካባቢ ካያችኋት እባካችሁ በፍጥነት ለቤተሰቧ ያሳውቁ። የእናንተ አንድ መረጃ ቤተሰቧን ከከባድ ጭንቀት ሊያድን ይችላል።
የመገናኛ ስልክ ቁጥሮች
- 📞 0935 164242 – ሜሮን መልሰው (እህት)
- 📞 0920 427395 – ሸዊት (እህት)
- 📞 0913 282943 – አቶ መልሰው አጥናፉ (አባት)
እባካችሁ ይህን መረጃ በማጋራት ተባበሩ። አንድ ሼር ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ ሊሆን ይችላል። 🙏

እጅግ በጣም ልብ ይሰብራል
የሚካኤል ወዳጆች የት ናችሁ
ይሕ የምትመለከቱት የሞዬ አማንጉልት አጣራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለ20 ዓመት በመጋረጃ ውስጥ ተከልሎ በመቃብር ቤት ውስጥ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አባቶች በጠና እየታመሙ የድረሱልን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች የት አላችሁ እጃችሁን ዘርጉልን እያሉ እየተማፀኑ ይገኛሉ እንደምትመለከቱት ዙርያውን ክፍት ስለሆነ መቅደሱ የእንስሳ መራቢያ ሆኖ አባቶች ክፉኛ ችግር ውስጥ እየከተታቸው ይገኛል ስለሆነም ኦርቶዶክሳዊያን የሆንን ሁላችን ከ200 ብር ጀምሮ ለሚካኤል ቤተክርስቲያን ማሰሪያ ለንዋየተ ቅድሳት ማሟያ የሚሆነውን አስራታችሁንም በማውጣት ካላችሁ ላይ በመስጠት አሰሩልን ተራዱን ድረሱልን እያሉ ይገኛሉ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር
1000392881879
የሞዬ አማንጉልት አጣራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን 🙏✨
📞 ለበለጠ መረጃ
0952530207
(እባክዎን የክርስትና ስምዎን በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ በዚሁ ስልክ ይላኩላቸው በፀሎት ያስቧችኋል)
ሼር (Share) በማድረግ ድምፅ ሁኑልኝ! 🙏⛪
15 days ago
ጎንደር - ብርሃኑ ነጋ እና ፍትፍቴ መሰንቆ
* ለባህል ጥበቃ የሚታትረው ቡቻች
#ethiopia | ብርሃኑ ነጋ ይባላል። በጎንደር ግን ከስሙ ይልቅ "ቡቻች" በሚለው የልጅነት ስሙ ይታወቃል። ይህን ስም ያወጡለት እናቱ ናቸው።
የ31 ዓመቱ ቡቻች በአዘዞ ተወልዶ ያደገ ሲሆን፣ በፋሲለደስ ባህል ማዕከል ተወዛዋዥና ባህላዊ ከበሮ ተጫዋች ነው። በተጨማሪም የእስክስታዋ ንግሥት አርቲስት እንየ ታከለ የባህል ምግብ አዳራሽ የባንዱ ማናጀር ሆኖም ያገለግላል።
ዛሬ ግን በሌላ የፈጠራ ሥራው እየተደነቀ ነው። ከአባቱ ነጋ መኮንን የወረሰውን የባህል ፍቅር ወደ ተግባር በመቀየር፣ ፍትፍቴ መሰንቆ በእጁ እየሠራ ለገበያ ማቅረብ ጀምሯል። ከዚህ በተጨማሪ ከበሮ፣ ዋሽንትና ክራር በመሥራት የኢትዮጵያን ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ለማስቀጠል እየተጋ ነው።
ወጣቶች ብዙዎች ሥራ ፍለጋ በሚባዝኑበት ዘመን፣ ቡቻች ግን የአባቶቹን ውርስ በእጁ እያኖረ ወደ ሥራና ፈጠራ መቀየሩ የሚያስደንቅ ነው። ይህ ጥረቱ ለራሱ ብቻ ሳይሆን የጎንደርን እና የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል ለትውልድ የሚያሸጋግር ውድ አስተዋፅኦ ነው።
በትጋት፣ በፅናትና በፈጠራ የተቀረጹት የቡቻች ነጋ እጅ ሥራዎች ከጎንደር ተነስተው ባህርዳርን አልፈው ዛሬ አዲስ አበባ ድረስ ደርሰዋል። በእጁ የሚሠሩ መሰንቆዎች፣ ዋሽንቶች፣ ክራሮችና ሌሎች ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች በገበያ ተፈላጊ ሆነዋል።
በመጀመሪያ አንድ መሰንቆ በ2,500 ብር ይሸጥ ነበር። የሥራው ጥራት እየተሻሻለ፣ ፍላጎቱም እየጨመረ በመምጣቱ ዛሬ መደበኛው መሰንቆ እስከ 8,000 ብር ይሸጣል። በብረት መቃኛ (tuning pegs) እና በድምፅ ማጉያ ጃክ የተሟላ ዘመናዊ መሰንቆ ደግሞ 15,000 ብር ይደርሳል።
ይህ የዋጋ ለውጥ የሚያሳየው የእጅ ጥበቡ እውቅና እያገኘ መምጣቱን፣ የሥራው ጥራት ከፍ ማለቱን እና ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ ለተጫዋቾች የተሻለ አማራጭ ማቅረቡን ነው።
ቡቻች የሚሠራው መሣሪያ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ሙዚቃ ለቀጣይ ትውልድ የሚያሸጋግር ሕያው ቅርስ ነው። እንደዚህ ያሉ ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች ሊበረታቱና ሊደገፉ ይገባል።
ትጋት፣ ጥረት፣ ፈጠራ እና ለባህል ያለው ፍቅር በእውነት የሚያስመሰግኑ ናቸው።
እንደ ቡቻች ያሉ ወጣቶች የባህላችን ሕያው አምባሳደሮች ናቸው።
ለቡቻች
ደውሉለት፤ እዘዙት
+251-918-138857
+251-904-365617
#ሼር # Share

🚨 ከስድስት የአሜሪካ ግዛቶች 1.6 ሚሊዮን እንቁላሎች እንዲሰበሰቡ ኤፍዲኤ ማስጠንቀቂያ አወጣ | በአሜሪካ የሚኖሩ ወዳጆቻችሁ እንዲጠነቀቁ ሼር አድርጉላቸው! #usanews #eggrecall #salmonella #fda #ethiopiansinusa
Sponsored by
Surafel
16 days ago
የአፋልጉኝ ተማጽኖ
ስም: አቤኔዘር ዮሴፍ
አድራሻ: ቂርቆስ 38 ታቦት ማደሪያ
አቤኔዘር ዮሴፍ ከቤቱ ወጥቶ በመጥፋቱ ቤተሰቦቹ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ።
ጠበል ለመጸበል ይመላለስ ነበር።
በጠፋበት ወቅት የለበሰው:
ጥቁር ጃኬት
ግራጫ (Grey) ሱሪ
ቀይ የክር ኮፍያ
ማንኛውም ሰው ልጁን ካየው ወይም ስለሚገኝበት መረጃ ካለው፣ እባክዎ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በአስቸኳይ ያሳውቁ፦
ወ/ሮ ኮራች ደመቀ (እናቱ)
አቶ በሀይሉ ጅንጋ፡ 0913 84 66 64
በለጡ አድባር፡ 0910 98 98 75
ሶፊያ ከሊል፡ 0910 57 96 94
እባክዎ ይህን መረጃ በሰፊው ያጋሩ። አንድ ማጋራትዎ አቤኔዘር ወደ ቤተሰቡ እንዲመለስ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
#missing #ethiopia #addisababa #share #ሼር

17 days ago
20 days ago
#ጤናመረጃ
የሀበሻ ጎመን ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች!
የሀበሻ ጎመን በቪታሚኖች (C, A, K) በማዕድናት (ካልሲየም፣ ብረት) እና በፀረ-ኦክሲዳንት ንጥረ ነገሮች እጅግ የበለፀገ ነው።
1. ለአጥንት ጥንካሬና ጤንነት፦ የሀበሻ ጎመን እጅግ ከፍተኛ የካልሲየም (Calcium) እና የቪታሚን ኬ (Vitamin K) ይዘት ስላለው፣ ለአጥንት መገንባት፣ ለጥንካሬ እና የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል አስተዋጽኦ አለው።
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር፦ በውስጡ ባለው ከፍተኛ የቪታሚን ሲ መጠን ምክንያት፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓት በማገዝ ከኢንፌክሽኖች እና ከተለያዩ በሽታዎች ይጠብቃል።
3. የደም ማነስን ለመከላከል፦ ጎመን በውስጡ ከፍተኛ የiron ማዕድን ይዟል። ይህም የሰውነታችንን ቀይ የደም ሴል ምርት በማገዝ የደም ማነስ ችግር እንዳይከሰት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
4. ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፦ ልክ እንደ ጥቅል ጎመን ሁሉ፣ የሀበሻ ጎመንም ከፍተኛ የፋይበር (የቃጫ) ይዘት ስላለው የሆድ ድርቀትን ለመከላከል እና የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል።
5. ለአይን ጤንነትና እይታ፦ በአይን ላይ የሚመጡ የዕድሜ መግፋት ጉዳቶችን እና ሌሎች የዓይን በሽታዎችን የመከላከል አቅም ያላቸውን ሉቲን እና ቪታሚን ኤ በበቂ መጠን ይዟል።
6.ለቆዳና ለፀጉር ውበት፦ በውስጡ የሚገኙት ቪታሚኖች (A,C,E) እና ፀረ-ኦክሲዳንቶች ለቆዳ ጤንነት፣ ለወጣትነት ገጽታ እና ለፀጉር ጥንካሬ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
ጠቃሚ ምክር :- የሀበሻ ጎመንን ከመጠን በላይ ሳያበስሉ (ሳይሞት) በመጠኑ አብስሎ መመገብ በውስጡ ያሉትን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ለማግኘት ይረዳል።(ኢትዮ-መረጃ)
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
Seledadotio

የመጨረሻ አማራጬ ስለሆነ አንድ ነገር ከመሆኔ በፊት ግልፅ አድርጌ ልንገራችሁ። ለእናቴ ስል ነው ይሄን ለመፃፍ ሶሻል ሚዲያ ላይ የወጣሁት። የማያልፍ የለም አውቃለሁ ግን አንዴ ብታነቡት ነው። ይህ የእኔ ያለፉት ጥቂት አመታት አጭር ታሪክ ነው ለታሪክ ይቀመጥልኝ!!
የዛሬ አራት አመት አከባቢ እማዬን፤ እናትዬን ካንሰር አገኘብኝ። ያኔ እኔ 12ተኛ ክፍል ነበርኩ። 2015 ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አመቱን ሙሉ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስትሰቃይ ነው የከረመችው። እኔም ከዛ በኋላ ፍፁም ሌላ ሰው ሆንኩ። በእኩለ ቀን አይኔን ሳልዘጋ ያቃዠኛል፤ መከራዋ ድንገት ድቅን ይልብኛል፤ ከሰዎች ጋር ቆሜ የሚታየኝ የሚሰማኝ ግን ሲቃ ነው ትምህርቱም አስጠላኝ ( btw I was really famous for my IQ and academic performance... እኔ ነበርኩ ማትሪክ ከፍተኛ ይሰራል ተብዬ ምጠበቀው) እናቴ ለኔ ትምህርት ራሷን ጥላ፤ እኔ በትምህርት ትልቅ ደረጃ ደርሼ ለማየት ሁሉ ነገሯን ሰውታ ቀርፃ ነው ያሳደገችኝ። የዘወትር የልጅነት ህልሜም አድጌ በሳይንሱ ዘርፍ ስኬታማ ሆኜ አሳይቻት የደስታና የተድላ ኑሮ ማኖር ነበር። 12ተኛ ክፍል ላይ ግን ሁሉም ነገር ተጠቅልሎ ገሃነም ገባብኝ። ስቃዩዋ እንደ ቁስል እየጠዘጠዘኝ እንኳን ላጠና ሌላ ነገር ማሰብ ራሱ አልቻልኩም (ድንገት ደንግጬ እነሳለሁ በለሊት... ስልክ እንዳልደውል ሰዓቱ በጣም ሄዷል)።
እንዲህ እንዲህ እየተባለ ማትሪክ ደርሶ ግቢ ገባን። ገና ከመግባቴ ከህንፃ ደረጃ ላይ ወድቄ ተሰባበርኩላችሁ። ሰው ፈተና ላይ እያለ እንደ እቃ በሽቦ ይጠግኑኛል😂 ካልተፈተንኩ ብዬ ቀወጥኩት ክሊኒኩ ውስጥ (እናቴ ከሰማች አውቃለሁ ምን እንደሚፈጠር) ግንኮ እግሬ በድን ሆኗል..ተሸክመው አስደግፈው አስተኙኝ። ሞላልቼ ተሸክመውኝ ይወጣሉ.. ሞላልቼ ተሸክመውኝ ይወጣሉ.. እያልን እያልን ፈተናው ልክ ሲያልቅ innovation ላይ እንድትሰሩ የተመረጣቹ ልጆች እዚሁ ቅሩ ሲባል አጋጣሚውን ተጠቅሜ እስክድን ግቢ ለመቆየት ወሰንኩ እሷ still ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ናት (I was in love with robotics btw)
ከሁለት ወር በኋላ እኔም ዳንኩ እሷም 'አሁን ደህና ስለሆነችና regular check up ህክምናዋን ከቤት እየመጣች በትክክል እስከተከታተለች ድረስ እስከ full life expectancy'ዋ መኖር ትችላለች "ድናለች"(it's not a fatal type of cancer if well-treated) ተብላ ቤት መጣች። በደስታ አበድን። "back to normal life somehow".. ከዛ ውጤትም መጣ (519)። I knew I had a bad year ግን still ተበሳጭቼ ነበር (የ highschool ego'ዬ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም ነበር 😁)። ግቢ ገባሁ። ፍሬሽ year እግዚአብሔር ይመስገን በሰላም ጨረስኩ። 2nd year'ም ምንም አይልም ነበር። 3ተኛ አመት ላይ ግን ድጋሚ አመማት። traumaዬ እንዳለ መመለስ ጀመረ. እንቅልፍ እምቢ አለኝ... በዚያ ላይ the way the medical expenses hit us last time, ቃል የለኝም ታቁታላቹ የበሽታውን ባህሪይ (የደሟ ናሙና በየሁለት ወሩ ነው ውጪ ሚላከው).. እሱን እሱንም ሳስብ I knew we ain't gonna afford a single tablet this time!!!
በመጨረሻም አሁን ላይ እንደገና ደከማት። ደምም አንሷታል ብለው ደም ሰጥተው ቤት ላኳት። ከመጣች በኋላ ግን በጣም አመማት። ከአልጋ ላይ ራሱ ተነስታ መቆም አትችልም ከቀን ወደ ቀን ስቃይ ነው ምግብም ብዙ አይበላላትም ዶክተሩ ግን በቀጣይ ቀጠሮ ሰውነቷ ተመልሶ ማየት ፈልጋለሁ ብሏት ነበር። እንዲ ብሎ ከላካት በኋላ አሁን እንደዚ እንደደከማት አላየም። መድሃኒቱም አለቀ እስከ ቀጠሮው ቀን የምትውጠው። አሁኑኑ ዶክተር ካላያት እየተባለ ነው ግን we can't afford it right now! ቁጭ ብዬ ስቃዩዋን ማየት ከበደኝ 😭😭😭 የምሰራው video editing'ም በቂ ገንዘብ ሊያመጣልኝ አልቻለም። I can't lose her man I CAN'T!!!!! እማዬን አድኑልኝ!! ከማበዴ በፊት እናቴን አትርፉልኝ ዝም ብላቹ አትዩኝ PLEASE🙏🙏😭😭😭
በገንዘብ ካልቻላችሁ በፀሎታቹ አግዙኝ... It must mean something, right?? ለምታውቁት ሰው ሼር ብታረጉልኝ ባለውለታዎቼ ናችሁ!! እወዳችኋለሁ።
CBE: 1000558030759

22 days ago
🔔 የተቃጠለችውን ቤተ ክርስቲያን ዳግም ለመገንባት የበኩልዎን ይወጡ! 🔔
ስትቃጠል ያዘናችሁ እና የተቆጫችሁ ሁሉ፣ አሁን ታሪክ የምንሠራበት ጊዜ ደርሷል! የእሳት ቃጠሎ አጋጥሟት የነበረችዉን የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ለማጠናቀቅ፣ ዓለም አቀፍ የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል።
ይህንን ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አስፈጽመን ለትውልድ የማስረከብ አደራ አለብን። በመላው ዓለም የምትገኙ የድንግል ማርያም ወዳጆች እና በእመቤታችን ውለታ ያለባችሁ ሁሉ፤ ድምፃችንን በመስማት አብራችሁን እንድትቆሙ በወላዲተ አምላክ ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።
ዛሬውኑ በቀጥታ ሥርጭቱ መርሐ ግብር ላይ በመደወል የአቅምዎን ድጋፍ ያድርጉ! (መርሐ ግብሩ ከሐምሌ 10 እስከ 12፣ ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል)
የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች፦
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፡ C1212
🏦 አሐዱ ባንክ ፡ 1111
🏦 አባይ ባንክ ፡ 7474
🏦 አቢሲኒያ ባንክ ፡ 2713
🏦 አዋሽ ባንክ ፡ 013521763662901
በውጭ ሀገር ለምትገኙ የዲያስፖራ አባላት፦
📲 Zelle ፡ 7025888907 (Edean Tolla)
🌐 Wegen Fund ፡ ሊንክ ኮመንት ላይ አለ።
ለበለጠ መረጃ እና በቀጥታ ሥርጭቱ ላይ ለመሳተፍ ስልክ ቁጥሮች፦
📞 0959833333 📞 0959877777
(የእግዚአብሔር ቤት ታንጾ እንዲጠናቀቅ ይህንን መልእክት ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያጋሩ!)
27 days ago
#ጤናመረጃ 🍋
10 አስገራሚ የሎሚ የጤና ጥቅሞች!
ሎሚን🍋 አዘውትሮ መጠቀም ከሚያስገኛቸው
ጥቅሞች ዋና ዋናዎቹን አጠር አድርገን እንያለን።
1) በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል፤ በቪታሚን ሲ የበለፀገ በመሆኑ ከጉንፋንና ከተለያዩ ተላላፊ ቫይረሶች ይከላከላል።
2) ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፤ ጠዋት በለጋ ውሃ መጠጣት በጉበት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድና አንጀትን ለማረጋጋት ይረዳል።
3) የቆዳን ውበት ይጠብቃል፤ የኮላጅን ምርትን በማፋጠን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፤ መልክን ያጠራል።
4) የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያለው ሲትሪክ አሲድ የካልሲየም ጠጠር እንዳይፈጠርና በሽንት እንዲወገድ ያደርጋል።
5) የደም ማነስን ይከላከላል፤ ሰውነታችን ከምግብ የሚያገኘውን የብረት (Iron) ንጥረ ነገር በቀላሉ እንዲመጥ ያግዛል።
6) ለአፍ ጠረን መፍትሔ ነው፤ በአፍ ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችን በማጥፋት ጠረንን ያድሳል፤ የጥርስ ሕመምንም ያስታግሳል።
7) ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል፤ በውስጡ ያለው የፔክቲን ፋይበር የረሃብ ስሜትን የሚቀንስና ስብን ለማቃጠል የሚረዳ ነው።
8) የልብን ጤንነት ይጠብቃል፤ መጥፎ ኮሌስትሮልን በመቀነስ ለልብ ሕመም እና ለድንገተኛ ስትሮክ የመጋለጥ ዕድልን ያጠባል።
9) ካንሰርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያሉ ተፈጥሯዊ ውህዶች (Flavonoids) የካንሰር ሴሎች እንዳይፈጠሩና እንዳይስፋፉ ይረዳሉ።
10) የደም ግፊትን ያስተካክላል፤ በውስጡ የሚገኘው ፖታሲየም የደም ስሮችን በማዝናናት የደም ግፊት ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል።

28 days ago
የማይቆም የሚመስለው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጉዞ …
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ኪሊያን ምባፔ፣ የባሎንዶር አሸናፊው ኦስማን ዴምቤሌ፣ ኦሊሴ፣ ሪያን ሼርኪ፣ ዴዝሪ ዱዌ፣ ኡፓሜካኖ እና ዊሊያም ሳሊባን የመሳሰሉ ከዋክብቶች ይገኛሉ፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እየተሳተፉ ከሚገኙ ሀገራት መካከል ውዱ ስብስብ ሲሆን፤ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ቅድመ ግምት ተሰጥቷል፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ጀምሮ እስከ ሩብ ፍጻሜ ድረስ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል፡፡
በእነዚህ ጨዋታዎች ተጋጣሚዎቹ ላይ 16 ግቦችን ያስቆጠረው ብሔራዊ ቡድኑ የተቆጠረበት ሁለት ግብ ብቻ ነው፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ካስቆጠራቸው 16 ግቦች መካከል ስምንቱን ያስቆጠረው የ27 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ነው፡፡
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውድ ልጅ የሆነው ኪሊያን ምባፔ አስደናቂ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት በተካሄደው የዓለም ዋንጫ 8 ግቦችን በማስቆጠር በወቅቱ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ወርቅ ጫማውን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ውድድሩ ሳይጠናቀቅ እስከ ሩብ ፍጻሜ ድረስ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ብቻ 8 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በቀጣይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የግብ መጠኑን ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ሦስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን ምባፔ በእግር ኳስ ሕይወቱ በዓለም ዋንጫ ውድድር በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 20 ጨዋታዎችን አድርጎ 20 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ሌላኛው የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ደግሞ የባሎንዶር አሸናፊው ኦስማን ዴምቤሌ ሲሆን በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ አምስት ግቦችን አስቆጥሮ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በባየርን ሙኒክ ቤት ድንቅ ጊዜ አሳልፎ ወደ ዓለም ዋንጫ የተጓዘው ኦሊሴ ሌላኛው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አስደናቂው ተጫዋች ነው፡፡
ኦሊሴ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ድረስ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡
በዚህም በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻቶ በማቀበል ቀዳሚው ተጫዋች ነው፡፡
ዊሊያም ሳሊባ እና ኡፓሜካኖ ደግሞ የቡድኑ የመከላከል ጥንካሬ ናቸው፡፡
በ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ እየተመራ አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚያደርገው እንቅስቃሴ ይጠበቃል፡፡
ዲዴ ዴሻምፕ በተጫዋችነት ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በፈረንጆቹ 1998 የዓለም ዋንጫን ማሳካታቸው ይታወሳል፡፡
ወደ አሰልጣኝነት ከመጡ በኋላ በፈረንጆቹ 2018 ፈረንሳይን በአሰልጣኝነት እየመሩ የዓለም ዋንጫን ያሳኩ ሲሆን በ2022 ደግሞ የፍጻሜ ተፋላሚ ነበሩ፡፡
አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ በአሰልጣኝነት ሕይወታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ፈረንሳይን ሻምፒዮን ያደርጉ ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

29 days ago
የእርዳታ ተማጽኖ
26 ዓመቱ ወጣት ሰዒድ መሐመድ ሁሴን የእኛን ድጋፍ ይፈልጋል
#ethiopia | የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነው የ26 ዓመቱ ወጣት ሰዒድ መሐመድ ሁሴን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከሥራ ውጭ በመሆናቸው ላለፉት 4 ዓመታት በከባድ ሕመም ሲሰቃይ ቆይቷል። በዚህ ጊዜም የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) ሕክምና እያደረገ ቆይቷል።
በሐኪሞች ቦርድ ውሳኔ መሠረት በአስቸኳይ ወደ ሕንድ በመጓዝ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና ማድረግ እንዳለበት ተገልጿል። ሆኖም ለሕክምናው የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ የአቅም ችግር ገጥሞታል።
ስለዚህ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወገኖች በአቅማችሁ መጠን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ይህን ወጣት ሕይወቱን እንዲያተርፍ እንድትረዱት በክብር እንጠይቃለን።
የድጋፍ መረጃ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የአካውንት ቁጥር: 1000290802467
የአካውንቱ ስም: ሰዒድ መሐመድ ሁሴን
ኢ-ብር / ቴሌብር
ስልክ ቁጥር: 0935 284 117
ስም: ሰዒድ መሐመድ
አንድ ትንሽ ድጋፍዎ ለአንድ ወጣት አዲስ የሕይወት ተስፋ ሊሆን ይችላል።
🙏 እባክዎ መልእክቱን በማጋራትም ቢሆን የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያድርጉ። #ሼር #share

30 days ago
ማስጠንቀቂያ_ለእህቶቻችን እና ለወላጆች!
በጀሞ አካባቢ የተፈጸመ የእገታ ሙከራ እና የተማርንበት ትልቅ ትምህርት
ትላንት በጀሞ አካባቢ በማህበራዊ ሚዲያ (ኢንስታግራም) በተደረገ ትውውቅ ምክንያት በአንዲት እህታችን እና በጓደኛዋ ላይ የወንጀል ሙከራ ተፈጽሟል።
ለሁላችንም መማሪያ ይሆን ዘንድ የታሪኩ ዝርዝር እና ሁላችንም ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ነገሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ?
ግለሰቡ በኢንስታግራም (Instagram) ከአንዲት ሴት ልጅ ጋር ካወራ በኋላ "ጀሞ አካባቢ ነኝ፣ እስቲ እንገናኝ" ይላታል። እሷም ለጥንቃቄ በማሰብ ብቻዋን ከመሄድ ይልቅ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመሆን ልታገኘው ትሄዳለች።
ልክ እንደተገናኙ ግን ግለሰቦቹ መኪና ይዘው በመጠበቅ ሁለቱንም ሴቶች በኃይል መኪና ውስጥ አስገብተው ለማገት ይሞክራሉ። መኪናውን ሳያንቀሳቅሱት እዚያው ባለበት ቦታ ላይ ሆነው ወደ ውስጥ ሊያስገቧቸው ሲታገሉ የአንደኛዋን ስልክ ቀምተው "ውረጂ" በማለት ከመኪናው ላይ ሊወረውሯት ሲሞክሩ፣ እህታችን በከፍተኛ ድፍረትና ድንጋጤ ውስጥ ሆና "ሌባ! ሌባ!" በማለት በጩኸት አካባቢውን ታናውጣለች።
የአካባቢው ህብረተሰብ የድረሱልኝ ጩኸት በሰማ ጊዜ በፈጠረው ፈጣን ርብርብ እህቶቻችንን ከከፋ አደጋ የታደጋቸው ሲሆን፣ ወንጀለኞቹንም እጅ ከፍንጅ በመያዝ በአሁኑ ሰዓት በጀሞ መርያም ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ይገኛል።
ለደራሹ የጀሞ ህብረተሰብ ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባል!
ከዚህ ክስተት ሁላችንም ምን እንማራለን?
ዋናው እና ትልቁ መማሪያ ማንም ሰው በማህበራዊ ሚዲያ ስለተዋወቀው ብቻ ሰውን በቀላሉ ማመን እንደሌለበት ነው።
በሶሻል ሚዲያ የምናየው ሰው ትክክለኛ ማንነቱን ላይገልጽ ስለሚችል ወንጀለኞች ሰዎችን ለማጥመድ የውሸት አካውንቶችን በስፋት ይጠቀማሉ። በዚህ አደጋ ላይ እንዳየነው ጓደኛ መያዝም ብቻውን ዋስትና አይሆንም፤ ምክንያቱም ወንጀለኞቹ ሁለቱንም በአንዴ ለማገት ሞክረዋል።
ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ማንነቱ ካልታወቀ ሰው ጋር በአካል መገናኘት በፍጹም አይመከርም። የግድ መገናኘት ካስፈለገ እንኳን ሰፊ ህዝብ ያለበት፣ ግልጽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ መሆን አለበት እንጂ ወደ መኪና አካባቢ መጠጋትም ሆነ መግባት ፍጹም የተከለከለ ነው።
እባካችሁ ይሄ መረጃ ለብዙ እህቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና ለወላጆች ትልቅ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ሼር (Share) በማድረግ ለሌሎች አጋሩ።
ዛሬ የደረሰውን ሰምተን ካልተጠነቀቅን ነገ በኛ ወይም በቤተሰባችን ላይ ሊደርስ ይችላል!
#የደህንነት_መልዕክት #ጀሞ #አዲስ_አበባ #ጥንቃቄ
Via ጉርሻ Page

1 month ago
ስራ #ሼር አድርጉልኝ ፈላጊ ጋር እንዲደርስ🧡አመሰግናለሁ በጣም።
ለሆዳችሁ ቆንጆ የባህር ዳር በርበሬ እና ሽሮ
ውበታችሁን ለመጠበቅ ደግሞ በብዙሃኑ የተመሰከረለት ቀሲል እና እርድ አለኝ (ወንዶችዬ ከፈለጋችሁ ለራሳችሁ አልያም ደግሞ ለእህት፣ለሚስት፣ለእናትህ መግዛት ትችላለህ❤)
ሁሉንም በብዛት መረከብ የምትፈልጉ ካላችሁ አብረን መስራት እንችላለን በinbox ፃፉልኝ🌻ወደ ውጭ ሃገር እንዲላክላችሁ የምትፈልጉ ካላችሁም አውሩኝ
መልካም ቅዳሜ🌻

Comments