2 months ago
🚨😱 በአዲስ አበባ የመሰረተ ልማት ዝርፊያ ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል?
ይህ ቪዲዮ የሚያሳየው ሰሚት ኮንዶሚኒየም (ኤል ጂ ኮሌጅ አካባቢ) የተፈጸመውን አሳዛኝ የንብረት ዝርፊያ ነው! ከዚህ ቀደም በመንገድ መብራት ምሰሶዎች (ፖሎች) ላይ የነበሩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ተዘርፈው ምንም ዓይነት የእርምት እርምጃ እና ቁጥጥር ባለመደረጉ፣ አሁን ደግሞ ሌቦች ዓይን ባወጣ ድፍረት መሬት በመቆፈር የከርሰ ምድር የመንገድ ዳር መብራት ገመዶችን በቪዲዮው በምታዩት መልኩ ዘርፈው ወስደዋል!
ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ መሠረት፤ በዚህ ጥፋት ምክንያት በግቢው ውስጥ ያሉት የመንገድ ዳር መብራቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
አካባቢው በጨለማ በመዋጡ ለነዋሪዎች ደህንነት እጅግ አስጊ ሆኗል!
ይህ የህዝብ እና የሀገር ሀብት ውድመት ዝም ተብሎ ሊታለፍ አይገባም! ቪዲዮውን ሼር (Share) በማድረግ ለሚመለከተው አካል ድምጻችንን እናድርስ! #addisababa #ethiopia #summitcondominium #addisababacity #ethiopiannews
Comments