#ጤናመረጃ
የሀበሻ ጎመን ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች!
የሀበሻ ጎመን በቪታሚኖች (C, A, K) በማዕድናት (ካልሲየም፣ ብረት) እና በፀረ-ኦክሲዳንት ንጥረ ነገሮች እጅግ የበለፀገ ነው።
1. ለአጥንት ጥንካሬና ጤንነት፦ የሀበሻ ጎመን እጅግ ከፍተኛ የካልሲየም (Calcium) እና የቪታሚን ኬ (Vitamin K) ይዘት ስላለው፣ ለአጥንት መገንባት፣ ለጥንካሬ እና የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል አስተዋጽኦ አለው።
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር፦ በውስጡ ባለው ከፍተኛ የቪታሚን ሲ መጠን ምክንያት፣ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓት በማገዝ ከኢንፌክሽኖች እና ከተለያዩ በሽታዎች ይጠብቃል።
3. የደም ማነስን ለመከላከል፦ ጎመን በውስጡ ከፍተኛ የiron ማዕድን ይዟል። ይህም የሰውነታችንን ቀይ የደም ሴል ምርት በማገዝ የደም ማነስ ችግር እንዳይከሰት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
4. ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፦ ልክ እንደ ጥቅል ጎመን ሁሉ፣ የሀበሻ ጎመንም ከፍተኛ የፋይበር (የቃጫ) ይዘት ስላለው የሆድ ድርቀትን ለመከላከል እና የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል።
5. ለአይን ጤንነትና እይታ፦ በአይን ላይ የሚመጡ የዕድሜ መግፋት ጉዳቶችን እና ሌሎች የዓይን በሽታዎችን የመከላከል አቅም ያላቸውን ሉቲን እና ቪታሚን ኤ በበቂ መጠን ይዟል።
6.ለቆዳና ለፀጉር ውበት፦ በውስጡ የሚገኙት ቪታሚኖች (A,C,E) እና ፀረ-ኦክሲዳንቶች ለቆዳ ጤንነት፣ ለወጣትነት ገጽታ እና ለፀጉር ጥንካሬ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
ጠቃሚ ምክር :- የሀበሻ ጎመንን ከመጠን በላይ ሳያበስሉ (ሳይሞት) በመጠኑ አብስሎ መመገብ በውስጡ ያሉትን ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ለማግኘት ይረዳል።(ኢትዮ-መረጃ)
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
Seledadotio

19 days ago