Logo
Tigu S Alemayew
‎የመጨረሻ አማራጬ ስለሆነ አንድ ነገር ከመሆኔ በፊት ግልፅ አድርጌ ልንገራችሁ። ለእናቴ ስል ነው ይሄን ለመፃፍ ሶሻል ሚዲያ ላይ የወጣሁት። የማያልፍ የለም አውቃለሁ ግን አንዴ ብታነቡት ነው። ይህ የእኔ ያለፉት ጥቂት አመታት አጭር ታሪክ ነው ለታሪክ ይቀመጥልኝ!!

‎የዛሬ አራት አመት አከባቢ እማዬን፤ እናትዬን ካንሰር አገኘብኝ። ያኔ እኔ 12ተኛ ክፍል ነበርኩ። 2015 ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አመቱን ሙሉ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስትሰቃይ ነው የከረመችው። እኔም ከዛ በኋላ ፍፁም ሌላ ሰው ሆንኩ። በእኩለ ቀን አይኔን ሳልዘጋ ያቃዠኛል፤ መከራዋ ድንገት ድቅን ይልብኛል፤ ከሰዎች ጋር ቆሜ የሚታየኝ የሚሰማኝ ግን ሲቃ ነው ትምህርቱም አስጠላኝ ( btw I was really famous for my IQ and academic performance... እኔ ነበርኩ ማትሪክ ከፍተኛ ይሰራል ተብዬ ምጠበቀው) እናቴ ለኔ ትምህርት ራሷን ጥላ፤ እኔ በትምህርት ትልቅ ደረጃ ደርሼ ለማየት ሁሉ ነገሯን ሰውታ ቀርፃ ነው ያሳደገችኝ። የዘወትር የልጅነት ህልሜም አድጌ በሳይንሱ ዘርፍ ስኬታማ ሆኜ አሳይቻት የደስታና የተድላ ኑሮ ማኖር ነበር። 12ተኛ ክፍል ላይ ግን ሁሉም ነገር ተጠቅልሎ ገሃነም ገባብኝ። ስቃዩዋ እንደ ቁስል እየጠዘጠዘኝ እንኳን ላጠና ሌላ ነገር ማሰብ ራሱ አልቻልኩም (ድንገት ደንግጬ እነሳለሁ በለሊት... ስልክ እንዳልደውል ሰዓቱ በጣም ሄዷል)።

‎እንዲህ እንዲህ እየተባለ ማትሪክ ደርሶ ግቢ ገባን። ገና ከመግባቴ ከህንፃ ደረጃ ላይ ወድቄ ተሰባበርኩላችሁ። ሰው ፈተና ላይ እያለ እንደ እቃ በሽቦ ይጠግኑኛል😂 ካልተፈተንኩ ብዬ ቀወጥኩት ክሊኒኩ ውስጥ (እናቴ ከሰማች አውቃለሁ ምን እንደሚፈጠር) ግንኮ እግሬ በድን ሆኗል..ተሸክመው አስደግፈው አስተኙኝ። ሞላልቼ ተሸክመውኝ ይወጣሉ.. ሞላልቼ ተሸክመውኝ ይወጣሉ.. እያልን እያልን ፈተናው ልክ ሲያልቅ innovation ላይ እንድትሰሩ የተመረጣቹ ልጆች እዚሁ ቅሩ ሲባል አጋጣሚውን ተጠቅሜ እስክድን ግቢ ለመቆየት ወሰንኩ እሷ still ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ናት (I was in love with robotics btw)

‎ከሁለት ወር በኋላ እኔም ዳንኩ እሷም 'አሁን ደህና ስለሆነችና regular check up ህክምናዋን ከቤት እየመጣች በትክክል እስከተከታተለች ድረስ እስከ full life expectancy'ዋ መኖር ትችላለች "ድናለች"(it's not a fatal type of cancer if well-treated) ተብላ ቤት መጣች። በደስታ አበድን። "back to normal life somehow".. ከዛ ውጤትም መጣ (519)። I knew I had a bad year ግን still ተበሳጭቼ ነበር (የ highschool ego'ዬ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም ነበር 😁)። ግቢ ገባሁ። ፍሬሽ year እግዚአብሔር ይመስገን በሰላም ጨረስኩ። 2nd year'ም ምንም አይልም ነበር። 3ተኛ አመት ላይ ግን ድጋሚ አመማት። traumaዬ እንዳለ መመለስ ጀመረ. እንቅልፍ እምቢ አለኝ... በዚያ ላይ the way the medical expenses hit us last time, ቃል የለኝም ታቁታላቹ የበሽታውን ባህሪይ (የደሟ ናሙና በየሁለት ወሩ ነው ውጪ ሚላከው).. እሱን እሱንም ሳስብ I knew we ain't gonna afford a single tablet this time!!!

‎በመጨረሻም አሁን ላይ እንደገና ደከማት። ደምም አንሷታል ብለው ደም ሰጥተው ቤት ላኳት። ከመጣች በኋላ ግን በጣም አመማት። ከአልጋ ላይ ራሱ ተነስታ መቆም አትችልም ከቀን ወደ ቀን ስቃይ ነው ምግብም ብዙ አይበላላትም ዶክተሩ ግን በቀጣይ ቀጠሮ ሰውነቷ ተመልሶ ማየት ፈልጋለሁ ብሏት ነበር። እንዲ ብሎ ከላካት በኋላ አሁን እንደዚ እንደደከማት አላየም። መድሃኒቱም አለቀ እስከ ቀጠሮው ቀን የምትውጠው። አሁኑኑ ዶክተር ካላያት እየተባለ ነው ግን we can't afford it right now! ቁጭ ብዬ ስቃዩዋን ማየት ከበደኝ 😭😭😭 የምሰራው video editing'ም በቂ ገንዘብ ሊያመጣልኝ አልቻለም። I can't lose her man I CAN'T!!!!! እማዬን አድኑልኝ!! ከማበዴ በፊት እናቴን አትርፉልኝ ዝም ብላቹ አትዩኝ PLEASE🙏🙏😭😭😭

‎በገንዘብ ካልቻላችሁ በፀሎታቹ አግዙኝ... It must mean something, right?? ለምታውቁት ሰው ሼር ብታረጉልኝ ባለውለታዎቼ ናችሁ!! እወዳችኋለሁ።

CBE: 1000558030759
17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.