1 day ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የእንግሊዙ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ፣ ስፔናዊውን ድንቅ አማካይ ሮድሪን ለማስፈረም ከስፔኑ ታላቅ ክለብ ባርሴሎና የቀረበለትን የ38.5 ሚሊዮን ፓውንድ የመነሻ ጥያቄ ውድቅ አደረገ! ሲቲ ተጫዋቹን ለመሸጥ በሩን ክፍት ቢያደርግም፣ ለዝውውሩ ግን ቢያንስ ከ60 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ካልቀረበለት እንደማይደራደር አሳውቋል።
የ30 ዓመቱ ኮከብ በኢትሃድ ስታዲየም ያለው ኮንትራት በመጨረሻው ዓመት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን አዲስ ውል ባለመፈረሙ ምክንያት "የፊታችን ክረምት ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆን?" የሚለው ጉዳይ የዝውውር ገበያውን እያሟሟቀው ይገኛል።
መጀመሪያ ላይ የአውሮፓው ነገስታት ሪያል ማድሪድን ይቀላቀላል ተብሎ በስፋት ቢታሰብም፣ አሁን ግን የላሊጋው ተቀናቃኝ ባርሴሎና በዝውውር ፉክክሩ ፊት አውራሪ ሆኖ ብቅ ብሏል። ቢቢሲ ስፖርት ከታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጠው ከሆነ፣ የካታሎኑ ክለብ ከተጫዋቹ ጋር ድርድር ለመጀመር ይሁንታ አግኝቶ አርብ ዕለት ይፋዊ የመነሻ ጥያቄውን ለሲቲ አቅርቧል። ባርሴሎና ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ንግግሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም አሳውቋል።
በሌላ በኩል ሮድሪን ለማስፈረም ከሪያል ማድሪድ ጋር የነበረው ድርድር ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተረጋግጧል። የስፔኑ ሬዲዮ 'ካዴና ሰር' የሮድሪን ወኪል ፓብሎ ባርኬሮን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ስፔን የዓለም ዋንጫን ካነሳች በኋላ ሪያል ማድሪድ ለተጫዋቹ "እምቢ ለማለት የሚያስቸግር" እጅግ ማራኪ ጥያቄ አቅርቦለት ነበር።
ከፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እስከ ዋና ስራ አስፈፃሚው ሆሴ አንጄል ሳንቼዝ ድረስ ዝውውሩን እውን ለማድረግ ሌት ተቀን ቢሰሩም፣ እና ድርድሩም በከፍተኛ መከባበር ቢካሄድም፤ ሮድሪ ሌላ አማራጭን በመቀበል የራሱን የግል ውሳኔ አሳልፏል። ማድሪድም ይህንን የተጫዋቹን ውሳኔ አርብ ዕለት ሲሰማ፣ ውዥንብርን ላለመፍጠር ሲል ተጫዋቹን በማመስገን በሰለጠነ መንገድ ከዝውውር ፉክክሩ ራሱን አግልሏል።
የ2024ቱ የባሎንዶር አሸናፊ የሆነው ሮድሪ፣ በ2024-25 የውድድር ዘመን በገጠመው ከባድ የጉልበት ጉዳት እና ባለፈው የውድድር ዘመን ባስተናገደው የቋንጃ ጉዳት ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ ከሜዳ ርቆ አሳልፏል። ይሁን እንጂ በክረምቱ የዓለም ዋንጫ አስደናቂ ብቃቱን ዳግም በማሳየት ስፔንን ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን እንድትሆን ከመምራቱም በላይ፣ የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
ባለፈው ወር በጀርባው ላይ በተደረገለት ቀዶ ጥገና ምክንያት አሁን ላይ ከሜዳ የራቀ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ማንችስተር ከሚገኙት የቡድን አጋሮቹ ጋር ለልምምድ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።
የነሀሴ ወር የዝውውር መስኮት ሁለተኛ ሳምንት ላይ እንደመገኘታችን፣ ማንችስተር ሲቲ የሮድሪን ጉዳይ በፍጥነት እልባት በመስጠት ጠንካራ ተተኪ ለማስፈረም ቆርጦ ተነስቷል። ሲቲዎች የ18 ዓመቱን ሞሮኳዊ የሊል አማካይ አዩብ ቡአዲን ወደ ኢትሃድ ለማምጣት ድርድር ላይ ቢሆኑም፣ የፈረንሳዩ ክለብ የጠየቀው 86 ሚሊዮን ፓውንድ ግን ለዝውውሩ ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
የሮድሪ ቀጣይ ማረፊያ ካምፕ ኑ ይሆን? የዝውውር መስኮቱ የሚዘጋበት ቀን እየተቃረበ ሲመጣ፣ የዚህ ኮከብ ተጫዋች ፊርማ እጣ ፈንታ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

4 days ago
ቪኒ የኛ ብቻ ነው በምንም አታስቡት
#ethiopia | ሪያል ማድሪድ ቪኒሽየስ የነጮቹ ኩራት ነው ይለቃል ብላችሁ አታስቡት ሲል ክለቡ ገለፀ።
ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን በክለቡ ለማቆየት ፈጣን እርምጃ መውሰዱን ነው ምንጮች የገለፁት።
የበርናቤው አመራሮች ቪኒሲየስን የክለቡ የወደፊት የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ዋና አካል አድርገው እንደሚመለከቱትና በቡድኑ ውስጥ ያለው ሚና ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ብራዚላዊውን የፊት መስመር አጥቂ ቪኒሽየስ ጂኒየር በሳንቲያጎ በርናቤው ለማቆየት በዓመት 22 ሚሊዮን ዩሮ ለመክፈል አዲስ የውል ማራዘሚያ ጥያቄ አቅርቧል።
ሪያል ማድሪድ ለቪኒሲየስ ያቀረበው አዲስ ውል በዓመት 22 ሚሊዮን ዩሮ የሚያስገኝ ሲሆን ይህ ክፍያ ተጫዋቹን በክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ከሆኑት የቡድኑ ተጫዋቾች ከፊት የሚያሰልፈው ነው።
ከተጫዋቹ ጋር የሚደረገው ድርድር በቀጣይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።
አሁን በወጡ መረጃዎች መሠረት ቪኒሲየስ የቀረበለትን አዲሱን ውል ተቀብሎ ለመፈረም አወንታዊ ምላሽ መስጠቱን ከቅርብ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #spain #football #realmadrid #vinícius #transfernews

ሊዮኔል ሜሲ በስፔን በሰደድ እሳት ለወደሙ አካባቢዎች 80 ሺህ ዩሮ ለገሰ
#ethiopia | የእግር ኳስ ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ በስፔን ማድሪድ ሴራ ኦኤስቴ ክልል በሰደድ እሳት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት የሚያግዝ 80 ሺህ ዩሮ መለገሱን የማድሪድ ማህበር ፕሬዝዳንት ዩሮፕ ፕሬስን ጠቅሰው አስታውቀዋል።
አደጋው ወደ 30 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ የደን መሬት ያወደመ ሲሆን የሜሲ ድጋፍም የወደሙትን አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ሜሲ ከዚህ ቀደም በስፔን ለተከሰቱ የሰደድ እሳት አደጋዎች ለቀይ መስቀል ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በቫሌንሲያ ለተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና በቬኔዙዌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጎጂዎችም ከባለቤቱ አንቶኔላ ጋር በመሆን እርዳታ አበርክቷል።
በተጨማሪም በጋራሃን ፋውንዴሽን በኩል 500 ሺህ ዩሮ በመለገስ በካንሰር ለተጠቁ ህጻናትና ለአርጀንቲና ሆስፒታሎች ያደረገው ድጋፍ የሚጠቀስ ሲሆን ሜሲ በሜዳ ውስጥ ባለው ድንቅ የእግር ኳስ ብቃቱ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጭ በሚያሳየው ታላቅ የሰብአዊነት ተግባር ይታወቃል ።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

5 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የ'ሪያል ማድሪድ ፋውንዴሽን' በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመላው አፍሪካ ካከናወናቸው ስኬታማ ተግባራት መካከል በኢትዮጵያ አዲስ የማህበራዊ ስፖርት አካዳሚ መክፈቱ በዋና ማሳያነት ተጠቅሷል። ፋውንዴሽኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ23 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ 52 የማህበራዊ ስፖርት ፕሮጀክቶችን ያካሄደ ሲሆን፣ በዚህም 10,628 የሚሆኑ ህጻናትን፣ ታዳጊዎችን እና ወጣቶችን የዕድሉ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
በዘመኑ ከተመዘገቡት ትልልቅ ስኬቶች አንዱ በሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ የማህበራዊ ስፖርት አካዳሚ መከፈቱ ነው። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም አንጎላ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሴኔጋል እና ግብጽን ጨምሮ በ23 የአፍሪካ ሀገራት ፕሮጀክቱ ተደራሽ ሆኗል።
በአካታችነት በኩል ፋውንዴሽኑ ሴት ታዳጊዎች በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ በማሳደግ እና ሴት አሰልጣኞችን በማበረታታት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ አካል ጉዳተኛ ህጻናት፣ ወጣት ስደተኞች እንዲሁም በከባድ ድህነት እና በግጭት የተጎዱ ማህበረሰቦችን የዕድሉ ተጠቃሚ አድርጓል። ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ባሻገር ትምህርታዊ ድጋፍን፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን፣ የህጻናት ጥበቃን፣ የጾታ እኩልነትን እና ማህበረሰባዊ ትስስርን ማጠናከር የትምህርት ቤቶቹ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
የአካባቢውን አሰልጣኞች አቅም በስልጠና፣ በክትትል እና በተሞክሮ ልውውጥ ማሳደግ የፕሮጀክቱ ሌላኛው ስኬት ነው። ይህ አካሄድ ከዚህ ቀደም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የነበሩ ወጣቶች አሁን ላይ ለተተኪው ትውልድ አሰልጣኝ እና አርአያ የሚሆኑበትን ቀጣይነት ያለው ሞዴል ለመፍጠር አስችሏል።
ፋውንዴሽኑ ይህንን ዘላቂ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማምጣት ከተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ሌሎች ፋውንዴሽኖች፣ ኩባንያዎች እና የአካባቢው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል።

Sponsored by
Surafel
8 days ago
አርሴናል በቪኒሲየስ ጁኒየር ዙሪያ ፍላጎቱን አጠናክሯል፤ ነገር ግን ስምምነት ገና አልተደረሰም
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሴናል የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት እያጠናከረ መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ የስፖርት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ሆኖም እስካሁን በሁለቱ ክለቦች መካከል ይፋዊ የዝውውር ድርድር አልተጀመረም።
ሪያል ማድሪድ ከ26 ዓመቱ አጥቂ ጋር የኮንትራት ማራዘሚያ ውይይት እያደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም። ይህም አርሴናል ሁኔታውን በቅርብ እንዲከታተል አድርጎታል።
እንደ Sky Sports እና The Guardian ዘገባ፣ አርሴናል ቪኒሲየስ አዲስ ኮንትራት ካልፈረመ የክለቡ ቀጣይ ዋነኛ የዝውውር ኢላማ እንደሚሆን ይታመናል። ሆኖም ዝውውሩ በግዙፍ የዝውውር ክፍያና ደመወዝ ምክንያት በእጅጉ አስቸጋሪ እንደሚሆን ተገልጿል።
በመሆኑም በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው "Breaking" የሚለው ምስል ቪኒሲየስ ወደ አርሴናል መዛወሩ ተጠናቋል የሚል ይፋዊ ማረጋገጫ አይደለም። እስካሁን ያለው ሁኔታ የፍላጎት ደረጃ ላይ ያለ እና ውይይቶች ገና ያልተጠናቀቁ መሆናቸውን የታማኝ የስፖርት ምንጮች ያስረዳሉ።

9 days ago
ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም በዝውውር መስኮቱ ትኩረት ስቧል፦ የብሩኖ ጊማራኤስ፣ ሊዊስ ኦል እና ክርስቲያን ሮሜሮ አዳዲስ መረጃዎች
በአውሮፓ የእግር ኳስ የዝውውር መስኮት ታላላቅ ክለቦች ስብስባቸውን ለማጠናከር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በርካታ ትኩረት ሳቢ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል የኒውካስል ዩናይትድ አማካኝና አጋዥ ብሩኖ ጊማራኤስን ለማስፈረም የሚያደርገውን ንግግር አፋጥኗል። እንደ ዘ ታይምስ (The Times)፣ ዘ ሳን (The Sun) እና ኢኤስፒኤን (ESPN) ዘገባዎች ከሆነ፤ አርሰናል ተጨማሪ ክፍያዎችን (add-ons) ጨምሮ 80 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ ሂሳብ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሷል። በተለይም አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ከኒውካስል ለመልቀቃቸው ተከትሎ አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም ያለው እምነት ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል ማንቸስተር ዩናይትድ የኒውካስሉን የግራ መስመር ተከላካይ ሊዊስ ኦልን በዝውውር አማራጭነት እየተመለከተው ይገኛል። በተመሳሳይ የዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ጣሊያኑ ክለብ ሮማ የመዛወር ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌለው ታውቋል።
በተጨማሪም ከአሰልጣኝ አንጌ ፖስቴኮግሉ ስብስብ ቶተንሃም ጋር በተያያዘ የስፓኒሹ አትሌቲኮ ማድሪድ የአርጀንቲናውን ማዕከላዊ ተከላካይ ክርስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት ዳግም ያቀጣጠለው ሲሆን፤ የፖርቱጋሉ ፖርቶ ደግሞ የቶተንሃሙን የግራ መስመር ተከላካይ ሶውዛን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየቱ ተገልጿል።

10 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሪያል ማድሪድ ቤት ድባቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቷል። ክለቡ የዓለም እግር ኳስ ፈርጥ እና የቡድኑ ዋልታ በሆነው ቪኒሽየስ ዙሪያ እያደረገ ያለው የኮንትራት ድርድር አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ፣ የ26 ዓመቱ ኮከብ በስፔን ዋና ከተማ ስላለው የረጅም ጊዜ ቆይታው ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ የወደቀበት ወቅት ላይ ይገኛል። የኮንትራት ማራዘሚያው ሒደት አለመሳካቱ፣ የቤርናባው የበላይ ጠባቂዎች ሁኔታውን እያስተናገዱበት ባለው መንገድ ላይ ጠንካራ ትችቶች እንዲሰነዘሩባቸው በሩን ወለል አድርጎ ከፍቷል።
ይህን ጠንካራ ትችት የሰነዘረው የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና ቫለንሲያ ግብ ጠባቂ ሳንቲያጎ ካኒዛሬስ ነው። በካዴና ኮፔ የ'ትዬምፖ ዴ ሁዌጎ' ፕሮግራም ላይ በሰጠው አስተያየት፣ ሎስ ብላንኮዎቹ በቪኒሽየስ ዙሪያ ያላቸውን የትርክት ቁጥጥር እንዳጡ በግልጽ ተናግሯል። ቪኒሽየስ አሁን ባለው ኮንትራት መሰረት በሚቀጥለው ክረምት በነጻ ሊለቅ ስለሚችል፣ ክለቡ የፋይናንስ እና የስፖርታዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ቀድሞ ጠንካራ አቋም መውሰድ ነበረበት ብሏል።
ካኒዛሬስ ቁጣውን ሲገልጽ፣ "ሪያል ማድሪድ ለሁሉም ነገር ይዘገያል። ተጫዋቹ የፈረመው ስምምነት የለውም የሚባለው እውነት ከሆነ፣ ማድሪድ አሁኑኑ እሱን የመሸጥ ግዴታ አለበት። ተጫዋቹን ኮንትራቱን ጨርሶ እንዲወጣ በማድረግ ከመቶ ሚሊዮን ዩሮ በላይ ማጣት አይቻልም፤ ግን ይህ የሚሆን ይመስለኛል። ይህ ይቅር የማይባል የአመራር ስህተት ነው" በማለት የክለቡን ቦርድ ክፉኛ ወቅሷል።
ማድሪዶች በዚህ የኮንትራት ውዝግብ ውስጥ እያሉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሀያል ክለብ አርሰናል ይህንን ውጥንቅጥ ለመጠቀም አድፍጦ እየጠበቀ ይገኛል። መድፈኞቹ ለብራዚላዊው ኮከብ እውነተኛ ፈላጊ ሆነው ብቅ ያሉ ሲሆን፣ የሚኬል አርቴታው ስብስብ ይህንን ፈጣን የክንፍ ተጫዋች ወደ ለንደን ለማምጣት ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑን ከእንግሊዝ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቪኒሽየስ አሁን ባለው ክለቡ ተገቢው ክብር እንዳልተሰጠው ከተሰማው፣ የፕሪሚየር ሊጉ ማራኪነት እና ሊቀርብለት የሚችለው ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ ከስፔን ሊያባብለው የሚችልበት አቅም አለው። ይሁን እንጂ፣ ማድሪዶች አሁንም ቢሆን ቪኒሽየስን በአዲስ ኮንትራት እንደሚያስሩት ሙሉ በሙሉ በራስ መተማመን እንዳላቸው ተዘግቧል።
ይህንን የተወሳሰበ የዝውውር ሒደት ይበልጥ እንዲወሳሰብ የሚያደርገው ደግሞ ክለቡ አዲስ ተሰጥኦን ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት፣ በተለይም የያን ዲዮማንዴ እምቅ ዝውውር ነው። አንዳንድ የስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት፣ ወጣቱን ኮከብ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ማድሪድ ከቪኒሽየስ ውጪ ላለው ህይወት ቀድሞ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳይ የቅድመ-ጥንቃቄ እርምጃ ነው። ምንም እንኳን ይህ ግምት ቢኖርም፣ አዲሱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ ብራዚላዊውን ኢንተርናሽናል የአዲሱ ፕሮጀክታቸው ቁልፍ አካል አድርገው ለማቆየት ቆርጠው መነሳታቸው ተነግሯል።

11 days ago
የአርሰናል የዝውውር ኢላማ የነበረው ቪኒሺየስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ እንደሚቆይ ተገለፀ
በአርሰናል በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ብራዚላዊው የክንፍ አጥቂ ቪኒሺየስ ጁኒየር በዚህ የዝውውር መስኮት ከሪያል ማድሪድ እንደማይለቅ ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ኮከብ አጥቂውን የመሸጥ ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌለው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የክለቡ አመራሮች ከተጫዋቹ ጋር አዲስ የረጅም ጊዜ ውል ለማስፈረም በሚደረገው ንግግር ሙሉ በሙሉ በራስ መተማመን ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

12 days ago
ሪያል ማድሪድ ለቪኒሲየስ 160 ሚሊዮን ዩሮ ጠየቀ አርሰናል ሂሳቡን ለመክፈል ፍላጎት ማሳየቱ ተገለጸ
የብራዚሉንና የሪያል ማድሪዱን የፊት መስመር ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለማስፈረም ሰፊ ፍላጎት ያሳየው አርሰናል፣ ማድሪዶች ለተጫዋቹ የጠየቁትን ግዙፍ የዝውውር ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑ ተዘገበ።
ሪያል ማድሪድ የ26 ዓመቱን አጥቂ የዝውውር ዋጋ 160 ሚሊዮን ዩሮ (137 ሚሊዮን ፓውንድ)ማድረጉን የስፓንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የክለቡ ፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ከተጠቀሰው ዋጋ በታች ለማንኛውም ድርድር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የዝውውር ፓኬጁ የተረጋገጠ ክፍያ እና ከተጫዋቹ ብቃት ጋር የተያያዙ ተጨማሪ ክፍያዎችን (add-ons) ያካተተ ነው።
እንደ ቪኒሲየስ ያሉ በውል ማጠናቀቂያ ዓመታቸው ላይ የሚገኙ ልሂቃን አጥቂዎች የወደፊት ቆይታ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ቢሆንም፣ የሪያል ማድሪድና የአሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ዋና ፍላጎት ተጫዋቹን አዲስ ውል ማስፈረም ነው።
ማድሪዶች በዚህ ሳምንት ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ተጨማሪ ድርድር ለማድረግ ቀጠሮ የያዙ ሲሆን፣ ተጫዋቹን በነጻ ከማጣት ይልቅ አሁን ለመሸጥ ከተገደዱ ግን የተመነውን ከፍተኛ የካሳ ክፍያ ቅድመ ሁኔታ አድርገዋል።
ባለፈው የውድድር ዘመን ለማድሪድ 22 ግቦችን ማስቆጠር የቻለውና በዓለም ዋንጫው ደግሞ ለብራዚል 4 ግቦችን ያስቆጠረው ቪኒሲየስ፣ አሁንም የአርሰናል ዋነኛ የዝውውር ኢላማ ነው። ምንም እንኳን በሁለቱ ክለቦች መካከል ይፋዊ የጽሁፍ ድርድር ባይጀመርም አርሰናል የፊት መስመሩን በጥራት ለማጠናከር ሲል ማድሪድ የጠየቀውን ግዙፍ የዝውውር ሂሳብ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆኑ ተሰምቷል።
በሪያል ማድሪድ በኩል የሚደረገው የአዲስ ውል ድርድር ካተቋረጠ በቀር አርሰናል የተመነውን ዋጋ በመክፈል ኮከቡን ወደ ኤሚሬትስ ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

14 days ago
ቪኒሲየስ ጁኒየር ወደ አርሰናል?፦ አርሰናል የሪያል ማድሪዱን ኮከብ ለማስፈርም እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል በግራ መስመር የፊት ማጥቃት ክፍሉን ይበልጥ ለማጠናከር የብራዚልና የሪያል ማድሪድ ኮከብ የሆነውን ቪኒሲየስ ጁኒየርን ወደ ኤሚሬትስ ለማምጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተዘገበ።
እንደ ዘገባዎች ገለጻ በክሉቦች መካከል እስካሁን ምንም ዓይነት ይፋዊ ግንኙነት ያልተደረገ ቢሆንም፣ የአርሰናል ፍላጎት ግን እውነተኛ ነው። የ2024 የባሎንዶር ዕጩ የ26 ዓመቱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች በሪያል ማድሪድ የማጠናቀቂያ የኮንትራት ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ አዲስ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ማድሪዶች ተጫዋቹን በሚቀጥለው ክረምት በነጻ ከማጣት ይልቅ አሁን ለመሸጥ ሊገደዱ ይችላሉ።
አርሰናል በዚህ የዝውውር መስኮት ሊያዛቸው ከቀረጻቸው የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል ጁሊያን አልቫሬዝ፣ ያን ዲዮማንዴ እና ብራድሊ ባርኮላ የሚገኙበት ሲሆን፣ የቪኒሲየስ ዝውውር ከተሳካ ግን ለኤሚሬትሱ ቡድን ትልቅና አስደናቂ ማጠናከሪያ ይሆናል።
የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ስብስብ በዚህ የበጋ የዝውውር መስኮት ሊያንድሮ ትሮሳርድን በ17 ሚሊዮን ፓውንድ ለቤሺክታሽ የሸጠ ሲሆን፣ በምትኩ ክሪስቶ ጾሊስን በ34 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል።
ሆኖም በቦታው ላይ የሚጫወተው ገብርኤል ማርቲኔሊ ባለፈው የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ማስቆጠር የቻለው አንድ ግብ ብቻ በመሆኑ ቡድኑ ተጨማሪ አማራጭ ይፈልጋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ምክንያት በዕረፍት ላይ የሚገኘው ቪኒሲየስ፣ ከአዲሱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ጋር ያለው ግንኙነት ትኩረትስቦ ነበር። ምንም እንኳን ተጫዋቹ እና አሰልጣኙ ያለፉት ክስተቶች አልፈው አዲሱን የውድድር ዘመን በአዲስ መንፈስ ለመጀመር ዝግጁ እንደሆኑ ቢነገርም፣ የአርሰናል ፍላጎት ይፋ መሆን ግን የ2026/27 የውድድር ዘመንን በፕሪሚየር ሊጉ ሊጀምር እንደሚችል ጠንካራ ጥቆማ ሰጥቷል።

15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ፣ የዓለም ዋንጫው ኮከብ እና የወርቅ ኳስ አሸናፊው ሮድሪ በቀጣዩ ሳምንት የወገብ ቀዶ ሕክምና እንደሚያደርግ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ተጫዋቹ በኢቲሃድ ስታዲየም እንደሚቆይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሮድሪ ስፔይን በሰሜን አሜሪካ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አርጀንቲናን 1-0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ስትሆን የቡድኑ አጋፋሪ እና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ መመረጡ ይታወሳል። በውድድሩ ወቅት 756 ስኬታማ ኳሶችን በማመቻቸት እና በርካታ ኳሶችን በመቀማት የቡድኑን የተከላካይ ክፍል በግንባር ቀደምትነት መርቷል።
የዓለም ዋንጫን፣ የአውሮፓ ሻምፒዮንነትን፣ አራት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የቻምፒዮንስ ሊግን፣ የባሎንዶርን እና ሌሎች በርካታ ዋንጫዎችን በስሙ ያጻፈው አማካይ፣ ኮንትራቱ ለመጠናቀቅ የመጨረሻ ዓመቱ ላይ በመድረሱ ወደ ማድሪድ በመመለስ ሪል ማድሪድን ሊቀላቀል ይችላል የሚሉ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል።
ሆኖም አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሮድሪ ማንኛውም አሰልጣኝ ሊያሰለጥነው የሚመኘው ድንቅ ተጫዋች መሆኑን ገልጸው፣ የዝውውር ጭ ወሬዎች በታላላቅ ተጫዋቾች ዙሪያ የተለመዱ በመሆናቸው ስጋት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
አሰልጣኙ አክለውም ሮድሪ ሰኞ ዕለት ቀላል የወገብ ቀዶ ሕክምና እንደሚያደርግና ከቀዶ ሕክምናው በኋላ አስፈላጊውን ዕረፍት አድርጎ ወደ ቡድኑ እንደሚመለስ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት ኦገስት 16 ከአርሰናል ጋር በሚደረገው የኮሚዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ እና በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ከቦርንመስ ጋር በሚደረገው ፍልሚያ ላይ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

16 days ago
ኤንድሪክ እንደ አንጀሊና ጆሊ
#ethiopia | የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ኤንደሪክ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የብራዚል አምባሳደር ሆኖ መሾሙን ተቋሙ አስታወቀ።
የ20 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ኤንድሪክ የህጻናትን መብት ለማስከበር እና በሀገሪቱ የዩኒሴፍን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ በብራዚል የዩኒሴፍ አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል።
የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና የሪያል ማድሪድ ተጫዋች የሆነው ኤንደሪክ ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ የህጻናት እና ታዳጊዎች መብትን ለማስከበር ከሌሎች የዩኒሴፍ አምባሳደሮች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተገልጿል።
ኤንድሪክ ያለው ተጽዕኖ እና የሚያሳየው አርአያነት ለዚህ የኃላፊነት ሚና ትክክለኛ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።
ዩኒሴፍ ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ በአለም ዙሪያ አምባሳደሮችን ሲሾም ቆይቷል።
እነዚህ አምባሳደሮች የሚመረጡት በስራቸው በሰፊው የሚታወቁ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና የህጻናትንና የወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያላቸው በመሆናቸው ነው።
በተለይም መልካም ምሳሌ መሆን የሚችሉ አርቲስቶች አትሌቶች እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ለዚህ ቦታ በተለያዩ ጊዜያት ይሾማሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #endricknamedunicef #ambassadorinbrazil #usaangelinajolie

በፈረንሳይ በሰደድ እሳት ምክንያት ከ20 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ
በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ ዢሮንድ (Gironde) በተባለው ክልል እየተስፋፋ ባለው የበረታ የሰደድ እሳት ምክንያት ከ12 ሺሕ በላይ ሰዎች ከአካባቢው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ባለሥልጣናት ተጨማሪ 8,800 ሰዎችን ደግሞ ወደ ደኅና ቦታ ለማዛወር ላይ ይገኛሉ።
በአካባቢው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዘገባ መሠረት በአርካሾን የባሕር ወሽመጥ (Bay of Arcachon) ዙሪያ እስካሁን ከ3,400 ሄክታር በላይ ደንና መሬት በወረረው እሳት የወደመ ሲሆን፣ ወደ 700 የሚጠጉ የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር በመታገል ላይ ናቸው።
ከአካባቢው ለቅቀው እንዲወጡ ከተደረጉት መካከል አብዛኞቹ በሌዥ-ካፕ-ፌሬ (Lège-Cap-Ferret) ባሕረ ገብ መሬት አቅራቢያ በነበሩ የካምፕ ማረፊያዎች ያረፉ ጎብኚዎች ናቸው። የዢሮንድ ክልል ፕሪፌክት (ወኪል) ሶፊ ብሮካስ ሌሊቱን ከተፈናቀሉት መካከል 10 ሺሕ ያህሉ የካምፕ ጎብኚዎች እንደሆኑ ገልጸው፣ በክላዌ (Claouey) መንደር የሚካሄደው የማፈናቀል ሂደት በረጋ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝና እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጠዋል።
የዢሮንድ የእሳት አደጋ መከላከል አገልግሎት ሃላፊ ማርክ ቨርሜለን እንደገለጹት፣ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ሌሊቱን በሙሉ እሳቱን ለመቆጣጠር ሳያቋርጡ ሲታገሉ አድረዋል። የሙቀት መጠኑ እየጨመረ እና የነፋሱ ሃይል እየበረታ መምጣቱ አደጋውን ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው የጠቆሙት ሃላፊው፣ የነፋሱ አቅጣጫ ሊገመት የማይችል በመሆኑ ጥንቃቄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በቦርዶ ኤርፖርት አቅራቢያ የተነሳን እሳት ለመቆጣጠር ሲታገሉ የነበሩ ሁለት የአካባቢው እሳት አደጋ ሠራተኞች ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ የደን አካባቢዎች እና መንገዶች እንዲዘጋ ተደርጓል።
በአካባቢው ነዋሪ የሆነችው የ19 ዓመቷ ያሲሚና ደ ፍሬታስ እንደገለጸችው፣ በምስራቅ አካባቢ የጭስ እና የቃጠሎ ጠረን ከተሰማ በኋላ አየሩ በካሪ እና በድቅድቅ ጭስ መሸፈኑን ተናግራለች። ፖሊስ ቤተሰቧን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ አፈናቅሎ አቅራቢያ ወደሚገኝ የቤት ውስጥ ስፖርት መስሪያ እንደወሰዳቸውና በእከካው ሽብር ምክንያት የቤት እንስሶቻቸውን ጥለው ለመውጣት መገደዳቸውን ገልጻለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰደድ እሳት አደጋው በደቡባዊ አውሮፓ ሀገራትም እየተስፋፋ ይገኛል። በስፔን ከማድሪድ ደቡብ በኩል ከሚገኘው ቶሌዶ አቅራቢያ ነዋሪዎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በጣሊያን ሲሲሊ ደግሞ አንድ የእሳት አደጋ ሠራተኛ እሳቱን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት ወቅት ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል

21 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ለአሥራ ስድስት ዓመታት ያህል.. “ጆሃንስበርግ” የምትለው ቃል ለስፔን እግር ኳስ ፍጹም ወርቃማ እና የተቀደሰች ትርጉም ነበራት። እሷ ከማድሪድ 8,000 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ብቻ አልነበረችም፤ ይልቁንም አይከር ካሲያስ የወርቅ ጽዋውን ወደ ሰማይ የሰቀለባት፣ አንድሬስ ኢኒየስታ በ116ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ ታሪክን ዘላለም ያደረገባት እና ስፔን “አንድ ቀን የዓለም ሻምፒዮን መሆን እችል ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የቀበረችባት የታሪክ ማህደር እንጂ!
አሁን ግን የእግር ኳሱ የክብር ካርታ ወደ አዲሱ ዓለም፣ ወደ ኒውዮርክ እየመራን ነው። በሁድሰን ወንዝ ማዶ በኒው ጀርሲ፣ ሌላኛዋ አዲስ እና አስፈሪዋ የስፔን ብሔራዊ ቡድን እያንዳንዱ ታዳጊ በሕልሙ ሊጫወተው የሚመኘውን ያንን ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታ ልታደርግ ተዘጋጅታለች። በዚያ በጆሃንስበርግ የኢኒየስታ ታሪካዊ ግብ ሲቆጠር አንዳንዶቹ የቡድኑ ተጫዋቾች ገና ዳዴ በማለት ላይ ነበሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ በየሰፈሩና በየፓርኩ ያንን ግብ እየደገሙ ያደጉ ታዳጊዎች ናቸው። ዛሬ ግን ያቺ የመጀመሪያዋ የክብር ኮከብ በእነሱ ላይ ከባድ ሸክም መሆኗ ቀርቶ ወደ ቀጣዩ ታሪክ የሚመራቸው ፋኖስ ሆናለች።
ይህ ጉዞ ግን በምቾት የተሞላ ቀጥተኛ መንገድ አልነበረም። ለአሥራ ስድስት ዓመታት የፈጀ፣ ስድስት አሰልጣኞችን የቀያየረ እና የቡድኑን ማንነት ሙሉ በሙሉ የለወጠ ከባድ ጉዞ እንጂ። የመጀመሪያው ምዕራፍ የወርቃማው ትውልድ ቀጣይ ክፍል ነበር። ቪሴንቴ ዴል ቦስኬ የዓለም ሻምፒዮኑን ቡድን ይዘት ሳይበርዝ አስቀጥሎ፣ ከሁለት ዓመት በኋላ በኪየቭ ጣሊያንን 4 ለ 0 በሆነ አስደናቂ እግር ኳስ በማሸነፍ የዩሮ 2012 ዋንጫን በድጋሚ አነሳ። ያ ስብስብ በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ታላቅ ታሪክ ጻፈ - የአውሮፓ ዋንጫን፣ የዓለም ዋንጫን እና የአውሮፓ ዋንጫን በተከታታይ በማሸነፍ ዓለምን በበላይነት የገዛበት ዘመን ነበር።
ነገር ግን ምንም ዓይነት ታላቅ ግዛት ለዘላለም አይኖርም! የ2014ቱ የብራዚል የዓለም ዋንጫ የዚያ ወደር የለሽ ትውልድ የውድቀት ማብሰሪያ ሆነ። በኔዘርላንድስ የደረሰባቸው አስደንጋጭ ሽንፈት እና በቺሊ መረታት ያንን ታሪካዊ ምዕራፍ በድንገት ዘጋው። ስፔን ከዓለም ሻምፒዮንነት ተነስታ በምድብ ደረጃ ተሸኝታ ወጣች። እግር ኳስ ለስፔናውያን ታላቅ ትምህርት ሰጣቸው - ክብር ለዘላለም የሚሰጥ ስጦታ አይደለም! ከሁለት ዓመት በኋላ በፈረንሳዩ ዩሮ፣ ጣሊያን ስፔንን በሩብ ፍፃሜ ስታስወጣ፣ የዴል ቦስኬ ዘመን እና ዋና የነበረው ያ ትውልድ ሙሉ በሙሉ ማክተሙ ታወጀ።
ከዚያ በኋላ ስፔን ወደ መልሶ ግንባታ ገባች። ጁለን ሎፔቴጊ የቡድኑን ታሪካዊ ቅርስ ሳይበታትን አዲስ ትውልድ የመፍጠር ከባድ ኃላፊነት ተረከበ። ቡድኑን በብቃት ለሩሲያው የዓለም ዋንጫ ቢያሳልፍም፣ ጨዋታው ከመጀመሩ ሁለት ቀን በፊት ከሪያል ማድሪድ ጋር ውል ማሰሩን ተከትሎ ከኃላፊነቱ መባረሩ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ትልቁ ድራማ ሆነ። ፈርናንዶ ሄሮ ቡድኑን በድንገተኛ አደጋ ቢረከብም፣ ስፔን በሩሲያ በፔናሊቲ ተመትታ ስትወጣ ስሜቱ እጅግ መራራ ነበር።
በመቀጠል የመጣው ሉዊስ ኤንሪኬ ግን ፍጹም አዲስ አብዮት ይዞ መጣ። ያረጁ ተዋናዮችን በማስወገድ፣ ወጣቶችን ወደ ፊት በማምጣት ፈጣንና ኃይለኛ ቡድን ፈጠረ። በልጃቸው ሕመም ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ቢርቁም፣ በረዳታቸው ሮበርት ሞሬኖ አማካኝነት ቡድኑ ሳይሸነፍ ጉዞውን ቀጠለ። ኤንሪኬ ሲመለሱም ፕሮጀክቱን አፋጠኑት። በ2021 ዩሮ ስፔን እስከ ግማሽ ፍፃሜ ተጉዛ በጣሊያን ብትሸነፍም፣ ቡድኑ ወደ ቀድሞ አስፈሪነቱ መመለሱን አበሰረ። ነገር ግን በኳታር የዓለም ዋንጫ ኮስታሪካን 7 ለ 0 በማሸነፍ በደመቀ ሁኔታ የጀመረው ጉዞ፣ በሞሮኮ የቅጣት ምት (ፔናሊቲ) ተረቶ በከባድ ሐዘን ተጠናቀቀ። ስፔን በተከታታይ ሦስት ትላልቅ ውድድሮች ሩብ ፍጻሜ እንኳን መድረስ አለመቻሏ ፌዴሬሽኑ አዲስ መንገድ እንዲፈልግ አስገደደው።
ሉዊስ ዴ ላ ፉየንቴ ለዓመታት በታችኛው የዕድሜ ክልል ውስጥ የስፔንን ወጣቶች ሲቀርጽ የቆየ ጥልቅ መሃንዲስ ነው። የዩሮ ከ19 እና ከ21 ሻምፒዮን፣ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆኑ የወደፊቱን ትውልድ በደብ ያውቀው ነበር። የእሱ ስልት ግለሰብን ሳይሆን እንደ አንድ ጠንካራ ቤተሰብ መጫወትን ማዕከል ያደረገ ነበር። ውጤቱም ወዲያውኑ መጣ!
መጀመሪያ የኔሽንስ ሊግን አሸነፈ... በመቀጠልም የ2024ቱን የአውሮፓ ዋንጫ በታላቅ የበላይነት በማንሳት ስፔንን ዳግም ወደ አውሮፓ የክብር ማማ መለሳት። ያ ቡድን በሮድሪ፣ ፔድሪ፣ ፋቢያን፣ ላሚን ያማል እና ኒኮ ዊሊያምስ የሚመራ፣ ወጣቶችና አንጋፋዎች የተቀላቀሉበት፣ ፍጹም የማይፈራ ስብስብ ሆነ። አሰልጣኙ እንደተናገሩት ያ ዩሮ ገና ጅምር እንጂ ማሳረጊያ አልነበረም።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ዴ ላ ፉየንቴ ኳስን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን፣ መሮጥ፣ መጫን፣ እና አስፈላጊ ሲሆን መከላከል የሚችል ሁለገብ ቡድን ገንብቷል። ይህ ቡድን በአጨዋወቱ ከ2010ዱ ቡድን ቢለይም፣ በአሸናፊነት ስነ-ልቦናው ግን ፍጹም አንድ አይነት ነው።
ከጆሃንስበርግ እስከ ኒውዮርክ በትክክል 5,852 ቀናት አልፈዋል። ተዋናዮቹ ተቀይረዋል፣ ስታዲየሞቹ ሌላ ሆነዋል፣ ተቀናቃኞቹም ተለውጠዋል። አይከር ካሲያስ የአምበልነቱን ማዕረግ ለአዲሱ ትውልድ አስረክቧል። ዣቪ፣ ኢኒየስታ እና ቪያ ቦታቸውን ለሮድሪ፣ ላሚን ያማል እና ኦያርዛባል ለቀዋል። ነገር ግን የዴል ቦስኬን ታሪካዊ መንገድ ዛሬ ዴ ላ ፉየንቴ በዚያው ወርቃማ ስሜት እያስቀጠለው ይገኛል—ያንን የመጀመሪያዋን የክብር ኮከብ በቴሌቪዥን እያዩ ያደጉት ታዳጊዎች፣ ዛሬ ሁለተኛዋን ኮከብ ለመጨበጥ በኒውዮርክ ሜዳ ላይ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል!

1 month ago
ክርስቲያኖ ሮናልዶ
የሰው ልጅ የጽናት፣ የፍላጎትና ተፈጥሮን የመፈታተን አቅም እውነተኛ ማሳያ
#ethiopia | በስፖርቱ ዓለም ታሪክ ውስጥ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሰው ልጅ ፍላጎት፣ ጽናትና ተፈጥሮን የመፈታተን አቅም የት ድረስ ሊጓዝ እንደሚችል በተጨባጭ ያሳየ ታላቅ እምቅ ኃይል ነው።
የእሱ የሕይወት ጎዳና ከተራ የስፖርት ስኬት ባሻገር ከድህነት አዘቅት፣ ከውድቅነትና ከሞት አፋፍ ተነስቶ የእግር ኳስን ዓለም በበላይነት እስከ መምራት የደረሰ እውነተኛ የጽናት ማሳያ ነው።
ይህንን አስገራሚ ጉዞ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ በውስጡ ያስተናገዳቸው እጅግ አስገራሚና አነጋጋሪ የሆኑ የተቃርኖ ማዕበሎች ናቸው።
የዚህን ስፖርተኛ ሕይወት ወደኋላ መለስ ብሎ ለተመለከተ ሰው ገና ከጅምሩ በፈተናዎች የተሞላ እንደነበር ይገነዘባል።
እናቱ እርግዝናውን ለማቋረጥ እስከ ማሰብ ደርሰው የነበረ ቢሆንም ያ ሊወለድ ያልተፈለገ ሕፃን ዛሬ የዓለማችን እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ለመሆን በቅቷል።
ፈተናው በዚህ ሳይበቃ ገና በ15 ዓመቱ ልቡ ባልተለመደ ፍጥነት ይመታ እንደነበር በሕክምና መረጋገጡ የእግር ኳስ ሕልሙን ሊቀጭበት የነበረ ቢሆንም በተደረገለት ስኬታማ የቀዶ ጥገና ሕክምና አማካኝነት ታሪክ መሥራቱን ቀጥሏል።
ይህ ዓይነቱ ጽናት ነው እንግዲህ እስከ ቅርብ ጊዜው መረጃ ድረስ በኦፊሴላዊ የክለብና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ ከ900 በላይ አስገራሚ ግቦችን ለማስቆጠር ያስቻለው።
የሮናልዶ የሕይወት መስመር በከፍተኛ ስቃይና በታላቅ ደስታ መካከል የሚዋዥቅ እውነተኛ ማዕበል ነው።
በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረው የቤት ናፍቆት፣ የአባቱ በሱስ ምክንያት መሞትና በዓለም አቀፍ መድረኮች በተደጋጋሚ የሚሰነዘሩበት ጠንካራ ትችቶች የእሱ የሕይወት ስቃይ መገለጫዎች ሲሆኑ በአንጻሩ ደግሞ በሪያል ማድሪድ ቤት ያስመዘገባቸው ከ400 በላይ ግቦች፣ ያሸነፋቸው አምስት የባሎንዶር ሽልማቶችና የዩሮ 2016 የድል ዋንጫ የእሱ የደስታ ከፍታዎች ነበሩ።
ይህንን ሁሉ ስኬት ዘላቂ ያደረገው ደግሞ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ዕድሜያቸው ሲገፋ ብቃታቸው በሚቀንስበት ወቅት እሱ ግን ገዛ አካሉን እንደ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ማሽን በጥንቃቄ በመንከባከብ ዕድሜን የሚፈታተን የብረት ዲሲፕሊን ማሳየቱ ነው።
ይህ ባለ ታሪክ በ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ላይ በ41 ዓመቱ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ በመጫወት የራሱን የመጨረሻ የእግር ኳስ ምዕራፍ አሳይቷል።
ምንም እንኳን ቡድኑ በስፔን ተሸንፎ ከውድድር ውጪ ቢሆንም እሱ ግን በውድድሩ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ግቡን በማስቆጠር በአለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ግብ በማስቆጠር በእድሜ ትልቁ ተጫዋች በመሆን ሌላ አዲስ የታሪክ አሻራ ጥሎ አልፏል።
የዚህ ታላቅ ስፖርተኛ የሕይወት ታሪክ ቅቤውን የሚያቀልጠው እሳት እንቁላልን እንደሚያጠነክረው ጥንታዊ ምሳሌ የሚጠቀስ ነው።
ብዙዎችን ሊያደቅና ከተስፋ ሊያስቆርጥ የሚችለው ከባድ ፈተናና ሥቃይ ለእሱ ግን ወደር የሌለው የብረት ዲሲፕሊን መፍጠሪያና በዓለም ስፖርት ታሪክ ውስጥ ለዘላለም የማይረሳ ደማቅ ታሪክ መሆን የሚያስችለው ዋነኛ የብርታት መሣሪያ ሆኖለታል።
ዛዲግ አብርሀ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
#ethiopia #getutemesgen #getunews #africanleadershipexcellenceacademy

በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ አስፈላጊው ተጫዋች - ቤሊንግሃም…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ እንግሊዛዊው ተጫዋች ጁድ ቤሊንግሃም ምርጥ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡
አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ጁድ ቤሊንግሃምን በተለያየ ጊዜ በተደረጉ የወዳጅነት እና የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች በጉዳትና በአቋም መውረድ ከስብስባቸው ውጪ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም ተጫዋቹ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ ላይ የመገኘቱ ነገር ጥያቄ ውስጥ ገብቶ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ሀገራት ለ2026 የዓለም ዋንጫ ስብስባቸውን ይፋ ሲያደርጉ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ጁድ ቤሊንግሃምን በስብስባቸው ላያካትቱት ይችላሉ የሚል ሃሳብ በስፋት ሲንጸባረቅ ነበር፡፡
ምክንያቱም ደግሞ ጁድ ቤሊንግሃም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ስኬታማ የሚባል ጊዜን ማሳለፍ ባለመቻሉ ነው፡፡
በመጨረሻም አሰልጣኙ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ጁድ ቤሊንግሃምን ወደ ስብስባቸው ማካተታቸው ይታወሳል፡፡አሰልጣኙ የመሐል ሜዳ ተጫዋቹን ወደ ስብስባቸው ካካተቱ በኋላም ለቦታው መፋለም እንዳለበት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ለ2026 የዓለም ዋንጫ የመጠራቱ ነገር አጠራጣሪ የነበረው ቤሊንግሃም አሁን በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ አስፈላጊው ተጫዋች ሆኗል፡፡
ጁድ ቤሊንግሃም በ2026 የዓለም ዋንጫ ጥሩ ጊዜን እያሳለፉ ከሚገኙ እንግሊዛዊ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡ተጫዋቹ በሦስቱም የምድብ ጨዋታዎች በቋሚነት ወደ ሜዳ በመግባት ለብሔራዊ ቡድኑ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
ቤሊንግሃም በሦስት የምድብ ጨዋታዎች ሁለት ግብ አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለ ሲሆን÷ ሁለት ጊዜ የጨዋታው ኮከብ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
በምድብ 3ኛ ጨዋታ ግብ አስቆጥሮ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ቤሊንግሃም በአንድ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረና ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለ በእድሜ ትንሹ እንግሊዛዊ ተጫዋች ሆኗል፡፡
ቤሊንግሃም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 50 ጨዋታዎችን ያደረገ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋችም ነው (በ22 ዓመት ከ359) ቀናት፡፡ ከዚህ ቀደም ዋይን ሩኒ በ23 ዓመት ከ159 ቀናት 50 ጨዋታዎችን በማድረግ ክብረ ወሰኑን ይዞ ነበር፡፡
ይህንን ክብረ ወሰን እንግሊዝ ከጋና ጋር ባደረገችው የምድብ 2ኛ ጨዋታ ባሳለፍነው ሳምንት የግሉ ያደረገው ጁድ ቤሊንግሃም በትናንትናው ዕለት 23 ዓመቱን ይዟል፡፡
በቀጣይ በዓለም ዋንጫ እንግሊዝ በምታደርጋቸው ጨዋታዎች ጁድ ቤሊንግሃም የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተጠባቂ ነው፡፡
እንግሊዝ ከፈረንጆቹ 1966 በኋላ የዓለም ዋንጫን ለማሳካት በምታደርገው ጉዞ ውስጥ ቤሊንግሃም ትልቁን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

ሪያል ማድሪድ ከዳኒ ሴባዮስ ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሪያል ማድሪድ ከስፔናዊው ተጫዋች ዳኒ ሴባዮስ ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል።
ዳኒ ሴባዮስ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በሪያል ማድሪድ ለሰባት የውድድር ዘመናት ቆይቷል።
የ29 ዓመቱ ተጫዋች ለሪያል ማድሪድ 215 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን 16 ዋንጫዎችን አሳክቷል።
ክለቡ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ዳኒ ሴባዮስ በሎስብላንኮቹ ቤት በነበረው ቆይታ ላሳየዉ ቁርጠኝነት እና ትጋት ምስጋናውን አቅርቦ ሪያል ማድሪድ ሁልጊዜም የእሱ ቤት መሆኑን ገልጿል።
ሪያል ማድሪድ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሌላኛው ስፔናዊ ተጫዋች ዳኒ ካርቫሀል ጋር መለያየቱ ይታወሳል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ዛሬ በቦስተን ስታዲየም የዓለማችን ምርጦቹ ሁለት አጥቂዎች ፊት ለፊት ሲገናኙ የእግር ኳስ አፍቃሪው አይን ሁሉ ወደዛው ያመራል። ፈረንሳይ ከኪሊያን ኤምባፔ ጋር፣ ኖርዌይን ከኤርሊንግ ሃላንድ ጋር ታፋልማለች! ሁለቱም ሀገራት በኮከብ አጥቂዎቻቸው አስደናቂ ብቃት ታግዘው የምድባቸውን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በድል አጠናቀዋል። ኤምባፔ እና ሃላንድ በሁለቱ ጨዋታዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ግቦችን በማስቆጠር በአጠቃላይ 4 ግቦችን አስመዝግበው ውድድሩን አሙቀውታል። በአሁኑ ሰዓት ሊዮኔል ሜሲ በ5 ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።
ሁለቱም ሀገራት ወደ ጥሎ ማለፉ ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም፣ የምድብ 9 (Group I) አንደኛ ሆኖ ለማጠናቀቅና በጥሎ ማለፉ የተሻለ ተጋጣሚ ለማግኘት ሲሉ ሁለቱም ኮከቦች በቋሚነት ይሰለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህን ልብ አንጠልጣይ ፍልሚያ ከመመልከታችን በፊት፣ ቢቢሲ ስፖርት ተጫዋቾቹ ለሀገራቸው ያላቸውን ፋይዳ እንደሚከተለው ዳስሶታል።
በክለቦቻቸው ያላቸው ወሳኝነት እንዳለ ሆኖ፣ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የሁለቱ ተጫዋቾች ተጽእኖ እጅግ የገዘፈ ነው። ከነሐሴ 2022 ጀምሮ ፈረንሳይ ኤምባፔን አሰልፋ 69.8% ጨዋታዎቿን ስታሸንፍ፣ እርሱ በሌለበት ግን የማሸነፍ መጠኗ ወደ 50% ይወርዳል። የምንጊዜም የፈረንሳይ ከፍተኛ ግብ አግቢው ኤምባፔ በሜዳ ላይ ሲኖር ፈረንሳይ በጨዋታ በአማካይ 2.3 ግቦችን ስታስቆጥር፣ በሌለበት ደግሞ 1.9 ግቦችን ታስቆጥራለች። በሌላ በኩል ኖርዌይ ያላት የተጫዋቾች ስብስብ ጥልቀት አነስተኛ በመሆኑ፣ ሃላንድ ለሀገሩ ያለው ወሳኝነት ከማንም በላይ ነው። ከነሐሴ 2022 ጀምሮ ኖርዌይ ሃላንድን አሰልፋ 64.5% ጨዋታዎቿን ስታሸንፍ፣ እርሱ በሌለበት ግን የማሸነፍ መጠኗ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ 33.3% ይንኮታኮታል።
ይህ የዓለም ዋንጫ ሁለቱም ተጫዋቾች በትልልቅ መድረኮች ጫና እንደማይበገሩ በሚገባ አሳይቷል። ትኩረቱ ሁሉ በሜሲ ላይ ቢሆንም፣ ኤምባፔ የዓለም ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አግቢነት ሪከርድን ለመስበር የጊዜ ጉዳይ ብቻ የሆነለት ይመስላል። በ16 የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች 16 ግቦችን ያስቆጠረው ፈረንሳዊው ኮከብ፣ ከ39 ዓመቱ ሜሲ የሚያንሰው በሁለት ግቦች ብቻ ነው። ኤምባፔ ከሜሲ በ12 ዓመት ማነሱ ደግሞ ሪከርዱን በእጁ ለማስገባት ሰፊ እድል ይሰጠዋል።
በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎውን እያደረገ ያለው ሃላንድ በበኩሉ፣ ውድድሩን እንደለመደው እያመሰቃቀለው ይገኛል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ከአንድ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ በታሪክ 6ኛው ተጫዋች ሲሆን፣ ባለፉት 50 ዓመታት ደግሞ ከእንግሊዙ ሃሪ ኬን (2018) ቀጥሎ ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗል። የሃላንድ የቅርብ ጊዜ የብሔራዊ ቡድን አቋምም እጅግ አስደንጋጭ ነው። በተከታታይ 12 የብሔራዊ ቡድን የውድድር ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን፣ ባለፉት 6 ጨዋታዎች ብቻ 16 ግቦችን መረብ ላይ አሳርፏል። አጠቃላይ የብሔራዊ ቡድን ግቦችን ስንመለከት በ100 የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች 60 ግቦችን ካስቆጠረው ኤምባፔ ጋር ሲነጻጸር፣ ሃላንድ በ52 ጨዋታዎች ብቻ 59 ግቦችን በማስቆጠር (ከኤምባፔ በ48 ጨዋታዎች አንሶ) አንድ ግብ ብቻ ዝቅ ብሎ ይገኛል።
የሁለቱን ኮከቦች አጠቃላይ እንቅስቃሴ ስናነጻጽር በዚህ የውድድር ዘመን በክለብ ደረጃ ኤምባፔ ኳስ በመንካት፣ እድል በመፍጠር እና ሙከራ በማድረግ ከሃላንድ ይበልጣል። ምንም እንኳን ሃላንድ በማንችስተር ሲቲ የተሻለ አሲስት ቢኖረውም፣ በዚህ የዓለም ዋንጫ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ኤምባፔ 14 ስኬታማ ኳስ የማታለል እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ፣ ሃላንድ ያደረገው አንድ ብቻ ነው። ነገር ግን ኳስን ወደ ግብ በመቀየር ሃላንድ ትልቅ የበላይነት አለው። ባለፉት አራት የክለብ የውድድር ዘመናት 23.43% ሙከራዎቹን ወደ ግብ ሲቀይር፣ ኤምባፔ ግን 18.24% አሳክቷል። የመከላከል አስተዋጽኦን በተመለከተ ኤምባፔ ወደ ኋላ ተመልሶ በመከላከል ረገድ ከሃላንድ እጅግ ያንሳል። ለሪያል ማድሪድ በዚህ ዓመት ሲጫወት ከ900 ደቂቃ በላይ ከተጫወቱ 1,483 የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ተጫዋቾች ውስጥ በመከላከል አስተዋጽኦ 1,481ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሁለቱ ኮከቦች ለሀገራቸው ያላቸው ፋይዳ በቅርብ ጊዜ የግብ ተሳትፎአቸው በግልጽ ይታያል። ከነሐሴ 2022 ጀምሮ ኤምባፔ በ44% የፈረንሳይ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ 33 ግቦችን እና 17 አሲስቶችን ሲያበረክት፣ ሃላንድ ደግሞ በ43.9% የኖርዌይ ግቦች ላይ ተሳትፎ በማድረግ 39 ግቦችን እና 4 አሲስቶችን አድርጓል።
ፈረንሳይ ዋንጫውን ለማንሳት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ቀዳሚዋ ናት፤ ሃላንድ ራሱ ሳይቀር ፈረንሳይ ዐርቡን ጨዋታ አሸንፋ ዋንጫውን ልትወስድ እንደምትችል በቅርቡ ተናግሯል። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን እጅግ አደገኛው የግብ ክልል አጥቂ የሆነውን ሃላንድን የያዘችው ኖርዌይ፣ በፈረንሳይ ላይ ያልታሰበ አደጋ ልትፈጥር እንደምትችል መገመት አያዳግትም። ሃላንድን ይዞ የኖርዌይን ጉዞ ይሄን ያህል ነው ብሎ መገደብ ሞኝነት ነው!

በብራዚል ብሔራዊ ቡድን እየደመቀ የሚገኘው ቪኒሸስ ጁኒየር…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው ኮከብ ቪኒሸስ ጁኒየር በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ ውድድር ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ቪኒሸስ ጁኒየር ሀገሩ ጥሎ ማለፉን እንድትቀላቀል ትልቁን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ብራዚል በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ከሞሮኮ ጋር አንድ አቻ በሆነ ውጤት ስትለያይ የአቻነቷን ግብ ያስቆጠረው ቪኒሸስ ጁኒየር ነበር፡፡
በሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ብራዚል ሄይቲን 3 ለ 0 ስታሸንፍ በጨዋታው ቪኒሸስ ጁኒየር አንድ ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡በምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ ብራዚል ስኮትላንድን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
ቪኒሸስ ጁኒየር በ2026 የዓለም ዋንጫ በሦስት የምድብ ጨዋታዎች አራት ግቦችን በማስቆጠር ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መካከል ይገኛል፡፡
በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ከሊዮኔል ሜሲ በአንድ ግብ በማነስ ከኪሊያን ምባፔ እና ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ እኩል አራት ግቦችን በማስቆጠር ለወርቅ ጫማው እየተፋለመ ነው፡፡
ቪኒሸስ ጁኒየር በዓለም ዋንጫ የምድብ እያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ አምስተኛው ብራዚላዊ ተጫዋች ሆኗል፡፡
ከዚህ ቀደም የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆኑት ጃይርዚንሆ (1970)፣ ሮማሪዮ (1994)፣ ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ እና ሪቫልዶ (በ2002) በእያንዳንዱ የምድብ ጨዋታ ግብ ማስቆጠራቸው ይታወሳል፡፡
ተጫዋቹ በሦስቱም የምድብ ጨዋታዎች ግብ ከማስቆጠር ባለፈ በእያንዳንዱ ጨዋታ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል።ቪኒ ሀገሩ ብራዚል ምድቧን በበላይነት እየመራች ወደ ጥሎ ማለፉ እንድትገባ የማይተካ ሚና ተጫውቷል፡፡
ከቀድሞ አሰልጣኙ ካርሎ አንቸሎቲ ጋር በብራዚል ብሔራዊ ቡድን የመገናኘት ዕድል ያገኘው ቪኒሸስ ጁኒየር በዓለም ዋንጫው ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡
ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ በስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ቪኒሸስ ጁኒየርን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡በአሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ሥር በሪያል ማድሪድ ቤት ምርጥ እንቅስቃሴ ካሳዩ ተጫዋቾች መካከል ቪኒሸስ ጁኒየር አንዱ ነው፡፡
ተጫዋቹ ከምድብ 3ኛ ዙር ጨዋታ በኋላ በሰጠው አስተያየት÷ ከአሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ጋር መስራት እንደሚወድ እና አንቸሎቲ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አሰልጣኞች መካከል ናቸው ሲል ተደምጧል።
ጊዜው ሲደርስ በብራዚል ብሔራዊ ቡድን እንደገና ምርጥ ብቃቴን እንደማሳይ እርግጠኛ ነበርኩ ብሏል።
በ2026 የዓለም ዋንጫ በምድብ 3ኛ ጨዋታ ለሀገሩ ብራዚል የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ኔይማር ጁኒየር በዚህ የዓለም ዋንጫ ቪኒሸስ ጁኒየር የእኛ ኮከብ በማለት አሞካሽቶታል፡፡
በዓለም ዋንጫው ጥሩ ጅማሮ ላይ የሚገኘው ቪኒሸስ ጁኒየር በቀጣይ በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተጠባቂ ናቸው፡፡

የልጅነት እንባ እና የድል መንገድ - ሮናልዶ ከትላንት እስከ ዛሬ
**********************
የ2004 አውሮፓ ዋንጫ ብዙ ትዝታዎች አሉት። የኦቶ ሪሃግሎቹ ግሪኮች ፖርቹጋሎችን በጥብቅ መከላከል በገዛ ሜዳቸው የአውሮፓ ዋንጫውን መንጠቃቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሊመጣ ብቅ እያለ ያለው አዲስ ኮከብ ትኩስ እንባ በሊዝበኑ ስታዲዮ ዳሉዝ ሲፈስ ትዝታው ዛሬም ርቆ ያልራቀ ቅርብ ነው።
ያን የዘመናዊ እግር ኳስ ህልው ትዝታ አስታከን ወደ ዛሬ እንዘልቃለን። ብዙ ውብ ትላንቶችን፣ ደማቅ ቀኖችን እና ውብ ምሽቶችን አልፎ እውን ወደሆነው ዛሬ እንመጣለን። ትዝታ ቢርቅም አያረጀምና፣ በዘመን መፈራረቅም አይደበዝዝምና ብትውስታ ጎዳና እንመላለሳለን።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዶስ ሳንቶስ አቪየሮ የሚባል ስም፣ በአባቱ መሻት የሮናልድ ሬገንን መጠሪያ እንዲጋራ የሆነ፣ በልጅነቱ አይጋፈጡትን ፈተና የተጋፈጠ፣ የሊዝበን ሰዎች በአፍላነቱ ሳይጠግቡ የተለዩት፣ የላንክ ሻየር ሰዎች ደግሞ ውብ ማለዳውን የተጋሩት፣ ውለታን የማይረሳው ዛሬም በስኬት ደጃፎች እየተመላለሰ ያለ ህያው ኮከብ ነው።
በሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና በማንቸስተር ዩናይትድ መልማዮች ዓይን ውስጥ ከገባባት ከዚያች የወዳጅነት ጨዋታ ዕለት አንስቶ ዘመናዊ እግር ኳስ ሌላ መልክ ነው የያዘው። ማንቸስተር ዩናይትድ ከዚህ ኮከብ ጋር በበርካታ ዋንጫዎች የተገመደ ብዙ የድል ቀናትን አልፏል።
ወደ ሎስ ብላንኮዎቹ ቅፅር ዘልቆም በነጩ መለያ ለሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥም በአውሮፓ መድረክም የሚደረገውን ሁሉ አድርጓል። ቱሪንም እጇን ዘርግታ ነው የተቀበለችው። እዚያም ስኬት ከእርሱ ጋር ነበረች።
በድኅረ ኮቪድ 19 የመጀመሪያ ወቅቶች ወደ ኦልድትራፎርድ ሲመለስ የቀዮቹ ደጋፊዎች ትዝታቸውን እንደሸከፉ ነበርና “እንኳን መጣህልን” ነበር ያሉት።
ሆኖም የማቸስተር ዩናይትድ ዳግም ምልሰቱ እንደ ትላንት ስል፣ እንደ ዕድሜውም በውጤት ብስል አልሆነም። ከኤሪክ ቴንሀግ ጋር የጋባበት መቃቃር ደግሞ ወደ መውጫው በር እንዲያማትር ዋነኛ ምክኒያት ሆነ።
ወደ መካከለኛው ምስራቅ ዘለቀ፤ በእግር ኳስ ብዙ መዋዕለ ንዋይ አፍስሳ ግዙፍ ለውጥ ወደ ሻተችው ሳዑዲ አረቢያ አቀና። ከሳምንታት በፊትም ለሦስት ዓመታት የተጠበቀውን የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮንነት ከክለቡ ዐል-ናስር ጋር አነሳ።
ሆኖም ጥያቄ ነበር። እነዚህን ሁሉ ቁጥራቸው የበረከቱ ስኬቶች ወደ ብሔራዊ ቡድን የሚተረጉማቸውስ መቼ ነው? የሚል።
በእርግጥ የ2016ቱን አውሮፓ ዋንጫ ሲያነሳ ይህ ጥያቄ በከፊል የተመለሰ መስሎ ነበር። የአውሮፓ ሀገራት ዋንጫ/ ኔሽንስ ሊግንም አንስቷል።
ግን ግዙፉ የዓለም ዋንጫስ? እግር ኳስ በታሪኩ ካስመለከታቸው ኮከቦች ለምሉዕነት አንድ መስፈርቱ ይኸው መድረክ ነውና፤ የእርሱስ ቀን አይመጣም ወይ? ተብሎ ተጠብቋል። እስካሁን ያ ቀን አልመጣም።
በእርግጥ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በተቆጠሩ ግቦች ከሊዮኔል ሜሲ እና ከኢራናዊው ዓሊ ዳይ በእጅጉ ርቋል። በዚህ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ደግሞ በመድረኩ ከተሳተፉ አንጋፋ ተጫዋቾች አንዱ ሆኖ ወደ አሜሪካ ምድር ሲዘልቅ ብዙ ጥበቃዎች ነበሩ። እነዛ ጥበቃዎች ግን በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያለግብ ሲለያዩ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ ያደረገ ሆነ። በርከት ያሉ ትችቶች እርሱም ሆነ የቡድን አጋሮቹ ላይ መሰንዘራቸው አልቀረም።
ቀን ጠብቆ በአሉታ ለተቹትም፣ በበጎ ለጠበቁትም ምላሽ ሰጥቷል። ኡዝቤኪስታንን 5 ለ 0 በረቱበት ጨዋታ ከመረብ ያሳረፋቸው እነዚያ ሁለት ግቦች ትችቶቹን አቅጣጫ ማስቀየሪያ ብቻ አልሆኑም። አዳዲስ ክብረ ወሰኖችንም አስከትለዋል።
ሮናልዶ ከካሜሩናዊው ሮጀር ሚላ በመቀጠል በመድረኩ ግብ ያስቆጠረ አንጋፋ ተጫዋች ተሰኝቷል፤ ከ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ እስከ 23ኛው የአሜሪካ ምድር ዓለም ዋንጫ በተሳተፈባቸው 6 ውድድሮች በሁሉም ግብ በማስቆጠር ደግሞ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
በጨዋታ ዘመኑ ያስቆጠራቸው ግቦችም 975 ደርሰዋል። በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ 145ኛ ግቡን በማስቆጠር ከተከታዩ ሊዮኔል ሜሲ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ 23 አስፍቷል።
በጨለማ ከመሰለው አስቸጋሪ ሳምንት በኋላ፣ ትችት ከበረከተባቸው ሰሞናት በኋላ “ተመልሰናል” ብሏል ሮናልዶ። በግል የሚመዘገቡ ክብረ ወሰኖች መልካም ቢሆኑም፤ ቀዳሚ ግቡ ግን ቡድኑን መርዳትና ለአሸናፊነት ማብቃት መሆኑን ነው የገለፀው።
ያ መንገድ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ዛሬም ቀጥሏል። እንደ ትላንቱ ባይሰላም ለተባለው ሁሉ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ አለ። የትችት ወጀብ ሳይገታው፣ የዕድሜ መግፋትም ሳይረታው እንደ ጥንቱ ስል ባይሆንም አለሁ እያለ ነው።
ዋይኒ ሩኒ የተናገው ይህን በሚገባ ይገልፃል።ሮናልዶ ትችትን ማስተናገድ፣ ለትችቱም አስፈላጊውን ተግባራዊ ምለሽ መስጠት በእግር ኳስ ዘመኑ ሁሉ የተጓዘበት እውነት ነው።
“ትዝታ አያረጅም” ሲባል በጎም ይሁን መጥፎ በአዕምሮ ጓዳ ደጋግሞ ስለሚመላለስ ነው። ሮናልዶ ግን ያለፈ ትዝታ፤ ያላለፈ ዛሬ ነው።
እነዚያ በፅናት የተጓዘባቸው ውጤታማ ዓመታት፣ ያንን የሊዝበን ሰታዲየም እንባ ይገልፃሉ። ያ የእልህ እና የቁጭት እንባ፤ ከዓመታት በኋላ ዛሬም ትኩስ ነው፣ አልቀዘቀዘም!
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #sports #ronaldo #football

2 months ago
የ1998 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኑ ዚዳን…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ከውድድሩ ጋር ሁሌም ስማቸው ከሚነሳ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ዚነዲን ዚዳን፡፡
ዚነዲን ዚዳን በዓለም እግር ኳስ ምርጥ ብቃታቸውን ማሳየት ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡
ከምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ዚነዲን ዚዳን በጨዋታ እይታው፣ በኳስ ቁጥጥሩ፣ በሚያቀብላቸው ኳሶች እና በሚያስቆጥራቸው አስደናቂ ግቦች በልዩነት ይታወቃል፡፡
በሀገሩ ክለቦች እግር ኳስን መጫወት የጀመረው ዚዳን ወደ ጣሊያን በማምራት በጁቬንቱስ አስደናቂ ጊዜን ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ በፈረንጆቹ 1996 ወደ ጁቬንቱስ ያቀናው ዚዳን የጣሊያን ሴሪ ኤን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
በጁቬንቱስ ቤት በመድመቅ ራሱን ለዓለም እግር ኳስ በደንብ ያስተዋወቀው ዚነዲን ዚዳን በፈረንጆቹ 2001 በ77 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በወቅቱ የተጫዋቾች ዝውውር ክብረ ወሰን በሆነ ክፍያ ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል፡፡
በወቅቱ የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪ ለዚዳን የከፈለው የዝውውር ሒሳብ ለ8 ዓመታት በተጫዋቾች ዝውውር ታሪክ የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የስፔን ላሊጋን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡ በፈረንጆቹ 2002 በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለሪያል ማድሪድ ባየር ሊቨርኩሰን ላይ በግራ እግሩ ያስቆጠራት ግብ በእግር ኳስ ታሪክ ከታዩ ምርጥ ግቦች መካከል አንዷ ሆና በታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍራለች፡፡
ከሪያል ማድሪድ ወርቃማው ስብስብ መካከል አንዱ የሆነው ዚዳን በሎስብላንኮቹ ቤት ከፈርናንዶ ሄሮ፣ ሮቤርቶ ካርሎስ፣ ሉዊስ ፊጎ፣ ክላውድ ማኬሌሌ፣ ጉቲ፣ ራውል እና ሮናልዶ ናዛሪዮ ጋር ተጫውቷል፡፡
የፈረንሳይ ዋናውን ብሔራዊ ቡድን ከፈረንጆቹ 1994 እስከ 2006 ያገለገለው ዚነዲን ዚዳን 108 ጨዋታዎችን አድርጎ 31 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
በፈረንጆቹ 1998 ሀገሩ ፈረንሳይ ባዘጋጀቸው የዓለም ዋንጫ ውድድር ከሀገሩ ጋር በመድረኩ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡
ፈረንሳይ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1998 የዓለም ዋንጫን ስታሳካ ትልቁን አስተዋጽኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ዚዳን ነበር፡፡ከዚያ በኋላ ፈረንሳይ በ2018 በድጋሚ በመድረኩ ሻምፒዮን መሆኗ አይዘነጋም፡፡
ዚነዲን ዚዳን ከሀገሩ ጋር የዓለም ዋንጫን ባሳካበት ዓመት የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ነበር፡፡በ2006ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር በፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን መሪ ያደረገች ግብ በፍጹም ቅጣት ምት በአስደናቂ ሁኔታ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
በጨዋታው ፈረንሳይን መሪ ያደረገችዋን ግብ ያስቆጠረው ዚዳን የጣሊያንን የአቻነት ግብ ያስቆጠረውን ማርኮ ማቴራዚን በመምታቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ አይዘነጋም፡፡
በወቅቱ ሀገሩ ፈረንሳይ በመለያ ምት ተሸንፋ ዋንጫውን በጣሊያን የተነጠቀች ሲሆን÷ ዚዳን ማቴራዚ ላይ በሰራው ድርጊት መነጋገሪያ ነበር፡፡
አሁንም ዚዳን የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተበት ማቴራዚን የመታበት አጋጣሚ ከውድድሩ ጋር አብሮ ይነሳል፡፡
በአሰልጣኝነት ከሪያል ማድሪድ ጋር የተሳኩ ጊዜያትን ያሳለፈው ዚዳን በቀጣይ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሪያል ማድሪድ በርናርዶ ሲልቫን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ፖርቹጋላዊውን አማካይ በርናርዶ ሲልቫ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ባለፉት ዓመታት በማንቼስተር ሲቲ ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈው ሲልቫ በነጻ ዝውውር ነው ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው፡፡
ተጫዋቹ እስከ ፈረንጆቹ 2028 የሚያቆየውን የሁለት ዓመት ኮንትራት ውል መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡
ሪያል ማድሪድ የቀድሞ አሰልጣኙን ጆዜ ሞሪኒሆን ጨምሮ ኮናቴ፣ ኩኩሬላ እና ደምፍሪስን ወደ ቡድኑ መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የካርሎ አንቸሎቲ የጋዜጣዊ መግለጫ ሊጠናቀቅ ሲል.. ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ሁሌም በሚታወቁበት የሰከነ እና ጥልቅ በሆነ መንገድ ማንም ሊያነሳው ያልደፈረውን ጉዳይ አንስተው መናገር ጀመሩ። በግንቦት ወር መገባደጃ ላይ ብራዚል ከፓናማ ጋር ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አስቀድሞ፣ አዲሱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አንቸሎቲ እንዲህ አሉ፡...
"ሰዎች አሁን ላይ ብራዚል ኮከብ ተጫዋች የላትም ሲሉ እሰማለሁ። ምናልባት እውነት ሊሆን ይችላል። እንደ ፔሌ፣ ሮማሪዮ ወይም ሮናልዶ አይነት ተጫዋች ላይኖረን ይችላል፤ ነገር ግን የጋራ ኃላፊነት ስሜት ሊኖረን ይችላል፣ ያ ደግሞ እጅግ ኃይለኛ መሳሪያ ነው።"
ይህ የአንቸሎቲ ንግግር የብዙዎችን ቀልብ የሳበው፣ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ቪኒሽየስ ጁኒየር እስካሁን ድረስ የብሔራዊ ቡድኑ የማይነካ መሪ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ... በተግባር ግን ያ ባለመሆኑ ነው። በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በክሮኤሺያ በመለያ ምት ተሸንፈው ከወጡ ከአራት ዓመታት በኋላም.... በ25 ዓመቱ አጥቂ ላይ አሁንም በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ይህ ጥርጣሬ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ለማሳየት... በመጋቢት ወር ብራዚል በፈረንሳይ 2ለ1 መሸነፏን ተከትሎ፣ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ "ቪኒሽየስ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ መካተት ይገባዋል ወይ?" የሚል የከረረ ክርክር እስከመክፈት ደርሷል። በክለብ ደረጃ ለቪኒሽየስ እጅግ ስኬታማ ጊዜያትን ያመጣው እና ትልቅ ተጽዕኖ የፈጠረው አንቸሎቲ ብሔራዊ ቡድኑን ቢረከብም፣ "ቪኒሽየስ በሪያል ማድሪድ የሚያሳየውን ድንቅ አቋም ለምን በብሔራዊ ቡድን መድገም አቃተው?" የሚለው ጥያቄ አሁንም እንደ ጥላ እየተከተለው ነው።
በእርግጥም ቪኒሽየስ በዚህ የዓለም ዋንጫ ዑደት ውስጥ በብሔራዊ ቡድኑ ብዙ የግብ ተሳትፎ ያደረገ ተጫዋች ነው፤ ሆኖም በ28 ጨዋታዎች 7 ግቦችን እና 6 አሲስቶችን ብቻ ማስመዝገቡ ለሱ ደረጃ አነስተኛ ነው። በ2018 እና 2022 የዓለም ዋንጫዎች የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ክሌበር ዣቪየር ይህንን ሲያብራራ "በክለብ ደረጃ የምታሳየውን አቋም በብሔራዊ ቡድን መድገም እጅግ ከባድ ነው። ክለብ ውስጥ የተለየ ልምምድ፣ የተለየ የጨዋታ መንገድ እና የዕለት ተዕለት ቆይታ አለ። ግልጹ ምሳሌ የሜሲ እና የአርጀንቲና ጉዳይ ነው። ሜሲ ሁሌም ይተች ነበር፣ ሊሳካለት የቻለው በ2022 ነው። ምክንያቱም አርጀንቲና ቡድን መገንባት ስለቻለች ነው። ለተጫዋች ተገቢውን መዋቅር መፍጠር ወሳኝ ነው" ይላል።
ቪኒሽየስም ይህንን እውነታ አይክድም። በቅርቡ ለካዜ ቲቪ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ፣ "በክለብ ውስጥ በየሶስት ቀኑ አዲስ ዕድል አለ። ከ10 ጨዋታዎች ሁለቱን መጥፎ ብጫወት ማንም ብዙ አያወራም። በብሔራዊ ቡድን ግን በአንድ ጨዋታ እና በሌላኛው መካከል ያለው ጊዜ ረጅም ነው፤ ጫናውም ሁልጊዜ ከፍተኛ ነው። ሰዎች ሁሌም በምርጥ አቋሜ ላይ እንድገኝ ይጠብቃሉ። ነገር ግን ወደ ዓለም ዋንጫ ሄጄ አራት ወይም አምስት ግቦችን አግብቼ ሻምፒዮን ብንሆን፣ ታሪኩ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። ያኔ መጥፎ በተጫወትኩባቸው ጨዋታዎች ላይ እንኳን ለዓለም ዋንጫ እየተዘጋጀሁ እንደነበር አድርገው ያወራሉ" ብሏል።
ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን መጫወት ለቪኒሽየስ ቀላል ሆኖ አያውቅም። አንድ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንዳሉት፣ የ2024 የባሎን ዶር ሁለተኛ ደረጃን የያዘው ቪኒሽየስ፣ "ሁሌም ዋናው ተዋናይ የመሆን ከፍተኛ ጉጉት" ያጠቃዋል። ቪኒሽየስ በሙያ ዘመኑ ሁሉ የለመደውም ይሄንኑ የዋና ተዋናይነት ቦታ ነው።
ወደ ሁለተኛው የዓለም ዋንጫው ሲያቀና... ቪኒሽየስ 14 የንግድ ስምምነቶች ያሉት ሲሆን፣ ይህ ከማንኛውም ብራዚላዊ ተጫዋች የላቀ ነው። ከሜዳ ውጪ ይህ ሁሉ ስኬት ቢኖረውም፣ አሁንም ድረስ ኔማር ከብራዚል እግር ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ጋር ያለውን አይነት ጥልቅ ስሜታዊ ቁርኝት እና ፍቅር ማግኘት አልቻለም። ይህ ሁኔታ እጅግ አስገራሚ ነው፤ አንደኛው (ኔማር) ኮከብነቱ እያለፈ ቢሆንም አሁንም በህዝቡ ልብ ውስጥ አለ፤ ሌላኛው (ቪኒሽየስ) ደግሞ በብቃቱ ጣሪያ ላይ ቢሆንም ያንን የህዝብ ፍቅር አላገኘም።
የግብይት ባለሙያ እና የቀድሞው የኔማር አማካሪ ኤድዋርዶ ሙሳ ይህንን ሲያብራራ፣ "ቪኒሽየስ በብራዚል ደጋፊዎች ይወደዳል፤ ነገር ግን እንደ ኔማር አይደለም። ኔማር አስቀድሞ በብሔራዊ ቡድኑ ግልጽ የሆነ ታሪክ (Legacy) ሰርቷል፤ የዘመናት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ቪኒሽየስ ግን በሪያል ማድሪድ ያሳየውን ብቃት በብሔራዊ ቡድን ገና አላሳየም። ሌላው ነጥብ፣ ኔማር በሳንቶስ ቆይታው ብራዚላውያን በየሳምንቱ አስደናቂ ብቃቱን ይመለከቱ ነበር። ቪኒሽየስ ግን በፍላሜንጎ ቋሚ ተሰላፊ እንኳ ሳይሆን ነው በልጅነቱ ሀገር ለቆ የወጣው" ይላል።
ዳታፎልሃ የተሰኘው የብራዚል የምርምር ተቋም ባወጣው መረጃ፣ አሁንም 53 በመቶ የሚሆኑ ደጋፊዎች አንጋፋው ኔማር በዓለም ዋንጫው ስኳድ ውስጥ መካተቱን ይደግፋሉ።
"አሁን ሁሉም የሚያወራው ስለእኔ ነው"
የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቪኒሽየስን የብሔራዊ ቡድኑ ማዕከል ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርጓል። ባለፈው መጋቢት ወር ሮድሪጎ በጉዳት ከዓለም ዋንጫው ውጪ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ዝነኛዋን ቁጥር 10 ማልያ ለቪኒሽየስ ሰጥተውት ነበር። ዓላማው ግልጽ ነበር... ቪኒሽየስ የብራዚል ፊት እንዲሆን ማድረግ። ነገር ግን ኔማር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ሲመለስ፣ የ34 ዓመቱ የሳንቶስ አጥቂ ዳግም የቁጥር 10 ማልያውን ተረክቧል።
ምንም እንኳን ኔማር ማልያውን ቢወስድም፣...በቅርብ ጊዜያት እያስተናገደው ያለው ተደጋጋሚ የአካል ብቃት ችግር ቀድሞ ይጣልበት የነበረውን ተስፋ አደብዝዞታል። አሁን የብዙዎች አይን ያረፈው ቪኒሽየስ ላይ ነው። ብራዚል 6ኛዋን የዓለም ዋንጫ ለማንሳት በምታደርገው ጉዞ ላይ ቪኒሽየስ የጥርጣሬ ደመናን ገፎ ደምቆ መውጣት ይኖርበታል።
ቪኒሽየስም ለዚህ የትኩረት ማዕከልነት ዝግጁ መሆኑን ይናገራል። "አሁን ሁሉም የሚያወራው ስለእኔ ነው፤ ምክንያቱም በሪያል ማድሪድ አምስት ወይም ስድስት ምርጥ የውድድር ዘመናትን አሳልፌያለሁ፣ ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች ተርታም ተሰልፌያለሁ። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ተጨማሪ ኃላፊነት ያመጣል። እኔም የምፈልገው ይሄንኑ ኃላፊነት ነው። አቅሜ የት ድረስ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ምክንያቱም የኔ ጣሪያ ሁሌም በጣም ከፍተኛ ነው" በማለት ቆራጥነቱን አሳይቷል። ይህ የዓለም ዋንጫ ቪኒሽየስ የብራዚል ደጋፊዎችን ልብ ሙሉ በሙሉ የሚያሸንፍበት ይሆን? ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል።

ከሞት አፋፍ የተመለሰው የአለም ዋንጫው የመክፈቻ ጨዋታ የሜክሲኮ ጀግና ራኡል ሂሚኔዝ
#ethiopia | ሜክሲኳዊው ኢንተርናሽናል ከስድስት አመት በፊት በህዳር ወር 2020 በጭንቅላቱ ላይ ከባድ የሚባል አደጋን በጨዋታ ላይ አስተናግዶ ነበር።
የ35 አመቱ አጥቂ ከስድስት አመት በኋላ በአለም ዋንጫው የመክፈቻ ጨዋታ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል። የቀድሞ የዎልቭስ አጥቂ በፉልሀም ቤት ስኬታማ ቆይታን ካደረገ በኋላ የኮንትራት ውል ቆይታው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ሻምፒየን ሺፕ የወረደውን የቀድሞ ክለቡ ተቀላቅሏል።
ሂሚኔዝ ደቡብ አፍሪካ ላይ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል በ125 የብሄራዊ ቡድኑ ጨዋታ 46ኛው ነች። ከቀድሞ የማንችስትር ዩናይትድ አጥቂ ሀቪዬር ሄርናንዴዝ 52 በመቀጠል የምንግዜውም የሀገሩ ከፍተኛ አስቆጣሪነት ቦታ ላይ ተቀምጧል።
በአለም ዋንጫው በ2014 አንድ 2018 ሁለት እና 2018 ሶስት ጊዜ ከተጠባባቂ ወንበር ሲጀመር በ2026 ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረኩ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ መጀመር ችሏል።
የእግር ኳስ ህይወቱን የቀየረው አጋጣሚ
ለሜክሲኮው ክለብ አሜሪካ ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ቤንፊካ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ በውሰት ውል በ2018-19 ዎልቭስን ተቀላቅሎ ቡድኑ ሰባተኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ቦታን ይዞ ባጠናቀቀበት አመት 13 የፕሪምየር ሊግ ጎሎችን አስቆጠረ።
በ2019-20 17 ጎሎችን አስቆጠረ። ይህን ተከትሎም ዎልቭስ 30 ሚሊየን ፓውንድ የክለቡን ሪከርድ የዝውውር ዋጋ በማውጣት በቋሚነት አስፈረመው።
ህይወቱን የቀየረው አጋጣሚ በህዳር 29 2020 ተፈጠረ። ከአርሰናል ጋር በኤምሬትስ በነበረ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ከዴቪድ ልዊዝ ጋር መጋጨቱን ተከትሎ ሂሚኔዝ ራሱን ስቶ ወደቀ።
ለደቂቃዎች የቡድን አጋሮቹ አሰልጣኙ እና ቤተሰቦቹ በህይወት አለ ወይ ? የሚለው ጉዳይ አስጨንቋቸው ሲመለከቱ ነበር። ሜዳ ላይ ኦክስጅን ተደርጎለት መትረፍ ቻለ።
የማገገም ሂደቱ አዝጋሚ ነበር።ለስድስት ወራት ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን ለስምንት ወራት ደግሞ ጨዋታን ማድረግ አልቻለም።በመስከረም ወር ከጉዳቱ በኋላ የመጀመሪያ ጎሉን ዎልቭስ ተጋጣሚው ሳውዛምፕተንን አንድ ለዜሮ ሲረታ ማስቆጠር ቻለ።
እንደ ኤን ቢ ሲ ዘገባ በ2023 ፉልሀምን ተቀላቅሎ የሶስት አመት ቆይታን በማርኮስ ሲልቫ ቡድን ውስጥ አድርጓል።

በ2014 ዓለም ዋንጫ የደመቀው ጀምስ ሮድሪጌዝ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውና በየአራት ዓመቱ የሚደረገው ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ ዓለም ዋንጫ ሁሌም አዳዲስ ክስተቶችን እያስመለከተ ያልፋል፡፡
የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር አዳዲስ ኮከቦችን እና በመድረኩ ድንገት ልዩነት ፈጥረው የእግር ኳስ ቤተሰብን ቀልብ የሚስቡ ተጫዋቾችን መመልከት የተለመደ ነው፡፡
ከመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ውድድር ጀምሮ እስከ ኳታሩ የዓለም ዋንጫ ድረስ የተለያዩ አስደናቂ ኮከቦች በመድረኩ መታየታቸው አይዘነጋም፡፡
በፈረንጆቹ 2014 ብራዚል ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ውድድር ደግሞ የመድረኩ ክስተት እና አስገራሚ ኮከብ ሆኖ ብቅ ያለው ኮሎምቢያዊው ተጫዋች ጀምስ ሮድሪጌዝ ነበር፡፡
በወቅቱ በመድረኩ ኮሎምቢያዊው የ22 ዓመቱ ተጫዋች ጀምስ ሮድሪጌዝ ሜዳ ላይ በሚያሳየው እንቅስቃሴ የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ችሏል፡፡
ብራዚል ባዘጋጀችው መድረክ ጀርመን ዋንጫውን ጀምስ ግን የሁሉንም ልብ ነበር ያሸነፈው፡፡
በወቅቱ ተስፋዎች ሁሉ ልማደኛው የግብ አዳኝ ራዳሜል ፋልካኦ ላይ ቢሆንም እሱ መጎዳቱን ተከትሎ ኮሎምቢያ ከምድብ ታልፋለች ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡
ኮሎምቢያ ግን አንድ የሚያሻግራት እና እግሮቹ እጅግ አስፈሪ የ22 ዓመት ወጣት ኮከብ ድንገት አገኘች፡፡
ብራዚላዊያን በደገሱት የ2014 የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ እንደ ጀምስ ሮድሪጌዝ የነገሰ ተጫዋች ማግኘት ከባድ ነበር፡፡
የእርሱን ያህል ግቦችን ያስቆጠረ፣ የእርሱን ያህል ለብሔራዊ ቡድኑ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ፣ በአስደናቂ እንቅስቃሴ እና በውብ ግቦች ተመልካቾችን ያዝናና አልነበረም።
በመድረኩ ስድስት ግቦችን ያስቆጠረው ወጣቱ ተጫዋች ከስድስቱ በኡራጓይ መረብ ላይ ያረፈችው ግብ የኮሎምቢያ እና የጀምስ መታሰቢያ ብቻ ሳትሆን ዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ከምርጦቹ አንዷ ሆና ተመዝግባለች፡፡
ጀምስ ሮድሪጌዝ ኡራጓይ ላይ ባስቆጠራት አስደናቂ ግብ ምርጥ ግብ በመባል የፑሽካሽ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ጀምስ ለኮሎምቢያ ባደረጋቸው እያንዳንዱ ጨዋታዎች ምርጥ ብቃቱን በማሳየት ሀገሩን ለሩብ ፍጻሜ አብቅቷል፡፡
ጀምስ ሮድሪጌዝ በዓለም ዋንጫው ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የውድድሩን የወርቅ ጫማ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ከዓለም ዋንጫው ጎን ለጎን ገና ከውድድሩ ሳይመለስ እርሱን ለማስፈረም በርካታ ታላላቅ ክለቦች ፍላጎት ማሳየታቸው አይዘነጋም፡፡
የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ይህንን የኮሎምቢያ ወጣት እና በዓለም ዋንጫው የተለያዩ ሀገራት ደጋፊዎች ልብ ውስጥ የቀረውን ጥበበኛ ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡
በወቅቱ ዓለም ላይ ያሉ በርካታ ክለቦች እሱን ለማስፈረም ቢፈልጉም ሪያል ማድሪድ የግሉ አደረገው፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ከዓለም ዋንጫው በብራዚል ተሸንፎ ሲሰናበት የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ጀምስ በማቅናት አጽናንተውታል፡፡
ትልቅ ደረጃ ይደርሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጀምስ ሮድሪጌዝ እንደተጠበቀው ሳይሆን መቅረቱ ይታወቃል፡፡
በወንድማኝ ጸጋዬ

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ቀያይ ሰይጣኖቹ ለፕሪሚየር ሊጉ ባስገቡት የዘንድሮ የተጫዋቾች ዝርዝር መሰረት በኦልድ ትራፎርድ ግርማ ሞገስ ነበራቸው የተባሉ ተጫዋቾች የማንቸስተር ቆይታቸው ማብቃቱ በይፋ ተረጋግጧል። ከነዚህም መካከል ዋነኛው እንግሊዛዊው የክንፍ ተጫዋች ጃዶን ሳንቾ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ ከ73 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ካዝናውን አራቁቶ ያመጣው ይህ ኮከብ፣ ከክለቡ ጋር የነበረው ቆይታ እጅግ አሳዛኝ እና ኪሳራ የበዛበት ሆኖ አልፏል። አቋሙን ማግኘት ተስኖት ከቀድሞ አሰልጣኞች ጋር ጭምር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቶ የነበረው ሳንቾ.. በመጨረሻም የክለቡን በር ለዘለቄታው ዘግቶ ወጥቷል። ከእሱ ጋርም ብራዚላዊው አንጋፋ አማካይ ካሴሚሮ እና ታይረል ማላሲያ ስንብታቸው ተረጋግጧል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ባወጣው ይፋዊ የመሰናበቻ መግለጫ "ጃዶን ሳንቾ በ2021 ወደ ኦልድ ትራፎርድ ከመጣ በኋላ የ2023ቱን የካራባኦ ካፕ ካነሳው ስብስብ አንዱ ነበር። ወደ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በውሰት ከመመለሱ፣ እንዲሁም በቼልሲ እና አስቶን ቪላ ጊዜያዊ ቆይታዎችን ከማድረጉ በፊት ለክለቡ 83 ጨዋታዎችን አድርጓል። ክለባችን ካሴሚሮ፣ ታይረል እና ጃዶን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመሰገነ፣ ለቀጣይ የእግር ኳስ ህይወታቸው መልካሙን ሁሉ ይመኛል" ብሏል።
የማንቸስተር ዩናይትድ ማልያ ከብዶት የታየው የ26 ዓመቱ አጥቂ፣ በአምስት ዓመት የዩናይትድ ቆይታው በሁሉም ውድድሮች ማግባት የቻለው 12 ጎሎችን እና 6 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ብቻ ነው። ይህ ደካማ አቋሙ የቀድሞ የክለቡን ተጫዋቾች ሳይቀር አበሳጭቷል። በተለይም ሉዊስ ሳሃ፣ ሳንቾን "በማንቸስተር ዩናይትድ ታሪክ እጅግ አሳዛኙ ፈራሚ" ሲል ከባድ ትችት ሰንዝሮበታል።
ሳሃ በቁጭት ስሜት ሲናገር... "ከመምጣቱ በፊት በቦሩሲያ ዶርትሙንድ ያሳየው አስገራሚ ብቃት እና የነበረው ተሰጥኦ ታላቅ ተስፋ ሰጥቶን ነበር፤ እንግሊዝ መጥቶ ያ ሁሉ መጥፋቱ ግን እንቆቅልሽ ሆኖብኛል። እኔ እግር ኳስ ተጫዋች በመሆኔ እድለኛ ነበርኩ፣ ግን በጉዳት ብዙ ጊዜ አሳልፌያለሁ። በእሱ ዕድሜ እና ተሰጥኦ የሱን ያህል ጨዋታዎችን መጫወት ብችል ምንኛ መታደል ነበር... አስገራሚ ነገሮችን ማድረግ የሚችል ልጅ ነው፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ ችሎታው እና የተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ሲባክኑ ማየት በእጅጉ ያሳዝናል" ብሏል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቢቸገርም በጀርመን ምድር ግን ሳንቾ አሁንም ትልቅ ከበሬታ እና ስም አለው። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ፣ ተጫዋቹ ከ2021 ጀምሮ የጠፋበትን የእግር ኳስ ህይወቱን ዳግም ለማንሰራራት ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ለማምራት በሩን ክፍት አድርጓል። የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ኒኮ ኮቫችም ለዚህ ዝውውር አረንጓዴ መብራት አብርተዋል እየተባለ ይገኛል።
ሳንቾ የህይወቱን ምርጥ ጊዜ ያሳለፈው በዚሁ በሲግናል ኢዱና ፓርክ ሲሆን.. በመጀመሪያ ቆይታው በ137 ጨዋታዎች በ114 ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበረው። በ2024 በውሰት ተመልሶ ክለቡን እስከ ዌምብሌዩ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ማድረሱም አይዘነጋም። ወደ ቡንደስሊጋው መመለሱ፣ ከ2021 ጀምሮ ለተለየው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ዳግም እንዲጠራ የሚያስችለውን መተማመን ሊሰጠው ይችላል።
የፋይናንስ መዛግብቱን ለማስተካከል እና አዲስ ጠንካራ ስብስብ ለመገንባት ቆርጦ የተነሳው ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋዮቹን እያጸዳ ይገኛል። ከሳንቾ በተጨማሪ አንጋፋው ብራዚላዊ አማካይ ካሴሚሮ እና የግራ መስመር ተከላካዩ ታይረል ማላሲያ በኮንትራት መጠናቀቅ ምክንያት ተሰናብተዋል። ከሪያል ማድሪድ መጥቶ በአራት የውድድር ዘመናት ቆይታው የካራባኦ ካፕ እና የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን ያነሳው ካሴሚሮ፤ እንዲሁም ከ2022 የፌይኖርድ ዝውውሩ በኋላ በጉዳት እየታመሰ 50 ጨዋታዎችን ብቻ ማድረግ የቻለው ማላሲያ የክለቡን በር ዘግተው ወጥተዋል።
አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ የስፖርት አመራር እነዚህን ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ ተጫዋቾች ማሰናበቱ፣ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት አዳዲስ እና ወጣት ደም ለማስገባት በደመወዝ በጀቱ ላይ ሰፊ የፋይናንስ ነጻነትን ፈጥሮለታል። አሁን የሁሉም አይን ዩናይትድ ይህንን ክፍተት በማን እንደሚተካው ላይ አርፏል!

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሪያል ማድሪድ ለአትሌቲኮ ማድሪዱ አጥቂ ጁሊያን አልቫሬዝ ያቀረበው 150 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ፣ ከተቀናቃኙ ባርሴሎና ጋር ከፍተኛ የዝውውር ፍልሚያ ውስጥ ገብቷል። እስከ 2030 በሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንትነት ዳግም የተመረጡት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በአንድ ተጫዋች ላይ የ150 ሚሊዮን ዩሮ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ቀደም ብለው ፍንጭ ሰጥተው ነበር። በዛሬው ዕለት ደግሞ ሎስ ብላንኮዎቹ ይህንኑ የዝውውር ጥያቄ የአርሰናል እና ፒኤስጂ ኢላማ ለሆነው ጁሊያን አልቫሬዝ ማቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ ይህን የሪያል ማድሪድ ጥያቄ ወዲያውኑ ውድቅ ያደረገው ሲሆን፣ አልቫሬዝን በተመለከተ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማያደርግ አስታውቋል። ሪያል ማድሪድ ባወጣው መግለጫ አትሌቲኮ ማድሪድ ለቀረበለት ጥያቄ ምስጋና ቢያቀርብም፣ ተጫዋቹ ያለበትን 500 ሚሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ በመጥቀስ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ አትሌቲኮ ማድሪድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልእክት ሪያል ማድሪድ ላይ በማሾፍ፣ "ለቀረበው ጥያቄ ምንም ዓይነት ምስጋና የለንም፤ ከባርሴሎና በላይ ስላሳቃችሁን ግን እናመሰግናለን" ብሏል። አትሌቲኮ ከዚህ ቀደም ባርሴሎና ያቀረበውን 100 ሚሊዮን ዩሮ ጥያቄም "የውሸት ዜና እና ንቀት" በሚል ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ የዝውውር ውዝግብ የተፈጠረው ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ባላቸው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው። ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና ለቀድሞው የስፔን ዳኞች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ሆዜ ማሪያ ኤንሪኬዝ ነግሬይራ ከፈጸመው ክፍያ ጋር በተያያዘ (የነግሬይራ ጉዳይ) የስፖርታዊ ቅጣት እንዲጣልበት እና ከአውሮፓ ውድድሮች እንዲታገድ ዩኤፋን ጠይቋል። ባርሴሎና በበኩሉ ከ2001 እስከ 2018 የተፈጸመው ከ7 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ክፍያ ለዳኞች ትንተና እና የቴክኒክ ምክር መሆኑን በመግለጽ፣ ሪያል ማድሪድ ስማችንን ለማጥፋት የሚያደርገው ጥረት ነው ሲል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።

ሪያል ማድሪድ ዩሊያን አልቫሬዝን ለማስፈረም ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሪያል ማድሪድ አርጀንቲናዊውን ተጫዋች ዩሊያን አልቫሬዝ ለማስፈረም ለአትሌቲኮ ማድሪድ ያቀረበው የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል፡፡
ሪያል ማድሪድ የ26 ዓመቱን የፊት መስመር ተጫዋች ከከተማ ተቀናቃኙ ለማስፈረም የ150 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ በይፋ አቅርቧል፡፡
የሪያል ማድሪድ ፕሬዚዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት በ150 ሚሊየን ዩሮ ኮከብ ተጫዋች እንደሚያስፈርሙ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
አልቫሬዝ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ በአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያቆይ ውል ያለው ሲሆን፥ አትሌቲኮ ለተጫዋቹ የቀረበለትን የዝውውር ሂሳብ ውድቅ ማድረጉ ተመላክቷል፡፡
ሌላኛው የስፔን ክለብ ባርሴሎና በተመሳሳይ አርጀንቲናዊውን ተጫዋች ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

Comments