የልጅነት እንባ እና የድል መንገድ - ሮናልዶ ከትላንት እስከ ዛሬ
**********************
የ2004 አውሮፓ ዋንጫ ብዙ ትዝታዎች አሉት። የኦቶ ሪሃግሎቹ ግሪኮች ፖርቹጋሎችን በጥብቅ መከላከል በገዛ ሜዳቸው የአውሮፓ ዋንጫውን መንጠቃቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሊመጣ ብቅ እያለ ያለው አዲስ ኮከብ ትኩስ እንባ በሊዝበኑ ስታዲዮ ዳሉዝ ሲፈስ ትዝታው ዛሬም ርቆ ያልራቀ ቅርብ ነው።
ያን የዘመናዊ እግር ኳስ ህልው ትዝታ አስታከን ወደ ዛሬ እንዘልቃለን። ብዙ ውብ ትላንቶችን፣ ደማቅ ቀኖችን እና ውብ ምሽቶችን አልፎ እውን ወደሆነው ዛሬ እንመጣለን። ትዝታ ቢርቅም አያረጀምና፣ በዘመን መፈራረቅም አይደበዝዝምና ብትውስታ ጎዳና እንመላለሳለን።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዶስ ሳንቶስ አቪየሮ የሚባል ስም፣ በአባቱ መሻት የሮናልድ ሬገንን መጠሪያ እንዲጋራ የሆነ፣ በልጅነቱ አይጋፈጡትን ፈተና የተጋፈጠ፣ የሊዝበን ሰዎች በአፍላነቱ ሳይጠግቡ የተለዩት፣ የላንክ ሻየር ሰዎች ደግሞ ውብ ማለዳውን የተጋሩት፣ ውለታን የማይረሳው ዛሬም በስኬት ደጃፎች እየተመላለሰ ያለ ህያው ኮከብ ነው።
በሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና በማንቸስተር ዩናይትድ መልማዮች ዓይን ውስጥ ከገባባት ከዚያች የወዳጅነት ጨዋታ ዕለት አንስቶ ዘመናዊ እግር ኳስ ሌላ መልክ ነው የያዘው። ማንቸስተር ዩናይትድ ከዚህ ኮከብ ጋር በበርካታ ዋንጫዎች የተገመደ ብዙ የድል ቀናትን አልፏል።
ወደ ሎስ ብላንኮዎቹ ቅፅር ዘልቆም በነጩ መለያ ለሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥም በአውሮፓ መድረክም የሚደረገውን ሁሉ አድርጓል። ቱሪንም እጇን ዘርግታ ነው የተቀበለችው። እዚያም ስኬት ከእርሱ ጋር ነበረች።
በድኅረ ኮቪድ 19 የመጀመሪያ ወቅቶች ወደ ኦልድትራፎርድ ሲመለስ የቀዮቹ ደጋፊዎች ትዝታቸውን እንደሸከፉ ነበርና “እንኳን መጣህልን” ነበር ያሉት።
ሆኖም የማቸስተር ዩናይትድ ዳግም ምልሰቱ እንደ ትላንት ስል፣ እንደ ዕድሜውም በውጤት ብስል አልሆነም። ከኤሪክ ቴንሀግ ጋር የጋባበት መቃቃር ደግሞ ወደ መውጫው በር እንዲያማትር ዋነኛ ምክኒያት ሆነ።
ወደ መካከለኛው ምስራቅ ዘለቀ፤ በእግር ኳስ ብዙ መዋዕለ ንዋይ አፍስሳ ግዙፍ ለውጥ ወደ ሻተችው ሳዑዲ አረቢያ አቀና። ከሳምንታት በፊትም ለሦስት ዓመታት የተጠበቀውን የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ሻምፒዮንነት ከክለቡ ዐል-ናስር ጋር አነሳ።
ሆኖም ጥያቄ ነበር። እነዚህን ሁሉ ቁጥራቸው የበረከቱ ስኬቶች ወደ ብሔራዊ ቡድን የሚተረጉማቸውስ መቼ ነው? የሚል።
በእርግጥ የ2016ቱን አውሮፓ ዋንጫ ሲያነሳ ይህ ጥያቄ በከፊል የተመለሰ መስሎ ነበር። የአውሮፓ ሀገራት ዋንጫ/ ኔሽንስ ሊግንም አንስቷል።
ግን ግዙፉ የዓለም ዋንጫስ? እግር ኳስ በታሪኩ ካስመለከታቸው ኮከቦች ለምሉዕነት አንድ መስፈርቱ ይኸው መድረክ ነውና፤ የእርሱስ ቀን አይመጣም ወይ? ተብሎ ተጠብቋል። እስካሁን ያ ቀን አልመጣም።
በእርግጥ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በተቆጠሩ ግቦች ከሊዮኔል ሜሲ እና ከኢራናዊው ዓሊ ዳይ በእጅጉ ርቋል። በዚህ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ደግሞ በመድረኩ ከተሳተፉ አንጋፋ ተጫዋቾች አንዱ ሆኖ ወደ አሜሪካ ምድር ሲዘልቅ ብዙ ጥበቃዎች ነበሩ። እነዛ ጥበቃዎች ግን በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያለግብ ሲለያዩ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ ያደረገ ሆነ። በርከት ያሉ ትችቶች እርሱም ሆነ የቡድን አጋሮቹ ላይ መሰንዘራቸው አልቀረም።
ቀን ጠብቆ በአሉታ ለተቹትም፣ በበጎ ለጠበቁትም ምላሽ ሰጥቷል። ኡዝቤኪስታንን 5 ለ 0 በረቱበት ጨዋታ ከመረብ ያሳረፋቸው እነዚያ ሁለት ግቦች ትችቶቹን አቅጣጫ ማስቀየሪያ ብቻ አልሆኑም። አዳዲስ ክብረ ወሰኖችንም አስከትለዋል።
ሮናልዶ ከካሜሩናዊው ሮጀር ሚላ በመቀጠል በመድረኩ ግብ ያስቆጠረ አንጋፋ ተጫዋች ተሰኝቷል፤ ከ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ እስከ 23ኛው የአሜሪካ ምድር ዓለም ዋንጫ በተሳተፈባቸው 6 ውድድሮች በሁሉም ግብ በማስቆጠር ደግሞ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
በጨዋታ ዘመኑ ያስቆጠራቸው ግቦችም 975 ደርሰዋል። በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ 145ኛ ግቡን በማስቆጠር ከተከታዩ ሊዮኔል ሜሲ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ 23 አስፍቷል።
በጨለማ ከመሰለው አስቸጋሪ ሳምንት በኋላ፣ ትችት ከበረከተባቸው ሰሞናት በኋላ “ተመልሰናል” ብሏል ሮናልዶ። በግል የሚመዘገቡ ክብረ ወሰኖች መልካም ቢሆኑም፤ ቀዳሚ ግቡ ግን ቡድኑን መርዳትና ለአሸናፊነት ማብቃት መሆኑን ነው የገለፀው።
ያ መንገድ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ዛሬም ቀጥሏል። እንደ ትላንቱ ባይሰላም ለተባለው ሁሉ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ አለ። የትችት ወጀብ ሳይገታው፣ የዕድሜ መግፋትም ሳይረታው እንደ ጥንቱ ስል ባይሆንም አለሁ እያለ ነው።
ዋይኒ ሩኒ የተናገው ይህን በሚገባ ይገልፃል።ሮናልዶ ትችትን ማስተናገድ፣ ለትችቱም አስፈላጊውን ተግባራዊ ምለሽ መስጠት በእግር ኳስ ዘመኑ ሁሉ የተጓዘበት እውነት ነው።
“ትዝታ አያረጅም” ሲባል በጎም ይሁን መጥፎ በአዕምሮ ጓዳ ደጋግሞ ስለሚመላለስ ነው። ሮናልዶ ግን ያለፈ ትዝታ፤ ያላለፈ ዛሬ ነው።
እነዚያ በፅናት የተጓዘባቸው ውጤታማ ዓመታት፣ ያንን የሊዝበን ሰታዲየም እንባ ይገልፃሉ። ያ የእልህ እና የቁጭት እንባ፤ ከዓመታት በኋላ ዛሬም ትኩስ ነው፣ አልቀዘቀዘም!
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #sports #ronaldo #football

1 month ago