Logo
FBC
ሪያል ማድሪድ ከዳኒ ሴባዮስ ጋር ተለያየ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሪያል ማድሪድ ከስፔናዊው ተጫዋች ዳኒ ሴባዮስ ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል።

ዳኒ ሴባዮስ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በሪያል ማድሪድ ለሰባት የውድድር ዘመናት ቆይቷል።

የ29 ዓመቱ ተጫዋች ለሪያል ማድሪድ 215 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን 16 ዋንጫዎችን አሳክቷል።

ክለቡ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ዳኒ ሴባዮስ በሎስብላንኮቹ ቤት በነበረው ቆይታ ላሳየዉ ቁርጠኝነት እና ትጋት ምስጋናውን አቅርቦ ሪያል ማድሪድ ሁልጊዜም የእሱ ቤት መሆኑን ገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከሌላኛው ስፔናዊ ተጫዋች ዳኒ ካርቫሀል ጋር መለያየቱ ይታወሳል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.