13 days ago
ኤንድሪክ እንደ አንጀሊና ጆሊ
#ethiopia | የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ኤንደሪክ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የብራዚል አምባሳደር ሆኖ መሾሙን ተቋሙ አስታወቀ።
የ20 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ኤንድሪክ የህጻናትን መብት ለማስከበር እና በሀገሪቱ የዩኒሴፍን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ በብራዚል የዩኒሴፍ አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል።
የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና የሪያል ማድሪድ ተጫዋች የሆነው ኤንደሪክ ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ የህጻናት እና ታዳጊዎች መብትን ለማስከበር ከሌሎች የዩኒሴፍ አምባሳደሮች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተገልጿል።
ኤንድሪክ ያለው ተጽዕኖ እና የሚያሳየው አርአያነት ለዚህ የኃላፊነት ሚና ትክክለኛ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።
ዩኒሴፍ ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ በአለም ዙሪያ አምባሳደሮችን ሲሾም ቆይቷል።
እነዚህ አምባሳደሮች የሚመረጡት በስራቸው በሰፊው የሚታወቁ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና የህጻናትንና የወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያላቸው በመሆናቸው ነው።
በተለይም መልካም ምሳሌ መሆን የሚችሉ አርቲስቶች አትሌቶች እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ለዚህ ቦታ በተለያዩ ጊዜያት ይሾማሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #endricknamedunicef #ambassadorinbrazil #usaangelinajolie

Comments