የ1998 የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኑ ዚዳን…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር ከውድድሩ ጋር ሁሌም ስማቸው ከሚነሳ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ዚነዲን ዚዳን፡፡
ዚነዲን ዚዳን በዓለም እግር ኳስ ምርጥ ብቃታቸውን ማሳየት ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው፡፡
ከምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ዚነዲን ዚዳን በጨዋታ እይታው፣ በኳስ ቁጥጥሩ፣ በሚያቀብላቸው ኳሶች እና በሚያስቆጥራቸው አስደናቂ ግቦች በልዩነት ይታወቃል፡፡
በሀገሩ ክለቦች እግር ኳስን መጫወት የጀመረው ዚዳን ወደ ጣሊያን በማምራት በጁቬንቱስ አስደናቂ ጊዜን ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ በፈረንጆቹ 1996 ወደ ጁቬንቱስ ያቀናው ዚዳን የጣሊያን ሴሪ ኤን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
በጁቬንቱስ ቤት በመድመቅ ራሱን ለዓለም እግር ኳስ በደንብ ያስተዋወቀው ዚነዲን ዚዳን በፈረንጆቹ 2001 በ77 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በወቅቱ የተጫዋቾች ዝውውር ክብረ ወሰን በሆነ ክፍያ ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል፡፡
በወቅቱ የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪ ለዚዳን የከፈለው የዝውውር ሒሳብ ለ8 ዓመታት በተጫዋቾች ዝውውር ታሪክ የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የስፔን ላሊጋን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡ በፈረንጆቹ 2002 በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ለሪያል ማድሪድ ባየር ሊቨርኩሰን ላይ በግራ እግሩ ያስቆጠራት ግብ በእግር ኳስ ታሪክ ከታዩ ምርጥ ግቦች መካከል አንዷ ሆና በታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍራለች፡፡
ከሪያል ማድሪድ ወርቃማው ስብስብ መካከል አንዱ የሆነው ዚዳን በሎስብላንኮቹ ቤት ከፈርናንዶ ሄሮ፣ ሮቤርቶ ካርሎስ፣ ሉዊስ ፊጎ፣ ክላውድ ማኬሌሌ፣ ጉቲ፣ ራውል እና ሮናልዶ ናዛሪዮ ጋር ተጫውቷል፡፡
የፈረንሳይ ዋናውን ብሔራዊ ቡድን ከፈረንጆቹ 1994 እስከ 2006 ያገለገለው ዚነዲን ዚዳን 108 ጨዋታዎችን አድርጎ 31 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
በፈረንጆቹ 1998 ሀገሩ ፈረንሳይ ባዘጋጀቸው የዓለም ዋንጫ ውድድር ከሀገሩ ጋር በመድረኩ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡
ፈረንሳይ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1998 የዓለም ዋንጫን ስታሳካ ትልቁን አስተዋጽኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ዚዳን ነበር፡፡ከዚያ በኋላ ፈረንሳይ በ2018 በድጋሚ በመድረኩ ሻምፒዮን መሆኗ አይዘነጋም፡፡
ዚነዲን ዚዳን ከሀገሩ ጋር የዓለም ዋንጫን ባሳካበት ዓመት የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ነበር፡፡በ2006ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር በፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን መሪ ያደረገች ግብ በፍጹም ቅጣት ምት በአስደናቂ ሁኔታ ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
በጨዋታው ፈረንሳይን መሪ ያደረገችዋን ግብ ያስቆጠረው ዚዳን የጣሊያንን የአቻነት ግብ ያስቆጠረውን ማርኮ ማቴራዚን በመምታቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ አይዘነጋም፡፡
በወቅቱ ሀገሩ ፈረንሳይ በመለያ ምት ተሸንፋ ዋንጫውን በጣሊያን የተነጠቀች ሲሆን÷ ዚዳን ማቴራዚ ላይ በሰራው ድርጊት መነጋገሪያ ነበር፡፡
አሁንም ዚዳን የዓለም ዋንጫ በመጣ ቁጥር በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተበት ማቴራዚን የመታበት አጋጣሚ ከውድድሩ ጋር አብሮ ይነሳል፡፡
በአሰልጣኝነት ከሪያል ማድሪድ ጋር የተሳኩ ጊዜያትን ያሳለፈው ዚዳን በቀጣይ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

2 months ago