5 days ago
ለመድፈኞቹ ደጋፊዎች መጥፎ ዜና !
በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ግሪክ ከ ኔዘርላንድስ ጋር ሲጫወቱ ፣ በአርሰናል ቤት ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ዞሊስ የጡንቻ ጉዳት አጋጥሞታል ።
#ዳጉ_ጆርናል

15 days ago
ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር ውሉን ለማደስ ተስማማ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም ተስማምቷል።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከክለቡ ጋር ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ ላለፉት በርካታ ወራት ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል።
አሁን ላይ ታዲያ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከመድፈኞቹ ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።
የአዲሱ ውል ትክክለኛ የጊዜ ርዝመት በይፋ ያልተገለጸ ቢሆንም አርቴታ ከፈረንጆቹ 2019 የጀመረው የስፔናዊው አሰልጣኝ የአርሰናል ቤት ቆይታ ቢያንስ እስከ 10ኛ ዓመቱ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።
ከአዲሱ ውል ጋር ተያይዞ የአርቴታ ደመወዝም ከፍተኛ ጭማሪ እንደሚያገኝ የተገለጸ ሲሆን አሁን በዓመት 10 ሚሊየን ፓውንድ የሚያገኘው አሰልጣኙ በአዲሱ ውል እስከ 5 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደርስ ተጨማሪ የጉርሻ ክፍያ በማግኘት የዓለማችን ውዱ ተከፋይ አሰልጣኝ ይሆናል ነው የተባለው።
አርቴታ በቅርቡ ስለ ውሉ ድርድር ሲናገር ÷ የአርሰናል ደጋፊዎች ስለ ወደፊቱ መጨነቅ እንደሌለባቸው እና እሱ በአርሰናል ቤት መቆየት እንደሚፈልግ ገልጿል።
አርቴታ በአርሰናል የሚኖረውን ቆይታ ማራዘሙ ክለቡ ከእሱ ጋር የጀመረውን የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ እንደሆነ የዘገበው ቢቢሲ ነው።
በአቤል ነዋይ

18 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) "ራያ ምንም ዕድል አልነበረውም!" 🧤❌ | በአንድ ቅጽበት የታየ ሁለት ፈጣን የመልሶ ማጥቃት ነበር! መጀመሪያ አርሰናሎች ነበሩ ጫና የፈጠሩት፤ ካይ ሀቨርትዝ መሀል ሜዳ ላይ ጥፋት ተሰርቶበትም ጨዋታው ቀጠለ። ኳሷ ወደ ማርቲን ኦዴጋርድ ደርሳ ቡካዮ ሳካ ሊመታት ሲሞክር ሳይሳካለት ቀረ።
ወዲያውኑ ግን ብራይተኖች በአንጻራዊው ሜዳ ኳሷን ነጥቀው በመሀል ሰነጠቁት! በዚህ ጊዜ የአርሰናል ተከላካዮች ወደ ኋላ በማፈግፈግ ለኮስቱላስ ሰፊ ክፍተት ሰጡት። እሱም የፍጹም ቅጣት ምቱ ጠርዝ ላይ ኳሷን አግኝቶ በግሩም ሁኔታ በግራ ማዕዘን በኩል ከመረብ አዋሀዳት! ዴቪድ ራያ ይህችን ኳስ ለማዳን ፈጽሞ ምንም ዕድል አልነበረውም!
የአርሰናል ተከላካዮች ስህተት ነው ወይስ የብራይተን ፈጣን የመልሶ ማጥቃት? መድፈኞቹ ከዕረፍት በኋላ ውጤቱን ይገለብጡት ይሆን?
⏱ እረፍት፡ ብራይተን 2 - 0 አርሰናል

23 days ago
አርሰናል ጥያቄ አለው
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሪው አርሰናል በሰንደርላንዱ ጨዋታ የተሰጠበትን አወዛጋቢ ፍፁም ቅጣት ምት ተከትሎ ከሊጉ የዳኞች ማህበር ጋር ወደ ውዝግብ ገብቷል።
የክሉቡ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት የዳኛውን ውሳኔ “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ በፅኑ የኮነኑ ሲሆን አሁን ላይ መድፈኞቹ የዳኞች ማህበር ሃላፊውን ሀዋርድ ዌብ አግኝተው ስለ ውሳኔው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።
በጨዋታው ላይ የተሰጠውን ያንን ፍፁም ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ በጥሩ ብቃት ያከሸፈው ቢሆንም የውሳኔው ትክክለኛነት ግን ክለቡን እስከ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር አሳስቧል።
አርሰናል የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ለመቀጠል በሚያደርገው ጉዞ ላይ መሰል የዳኝነት ውሳኔዎች ተፅዕኖ እንዳያሳድሩበት ያለው ስጋት አሁንም በስፖርቱ ዓለም ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቀጥሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ts

Sponsored by
Surafel
24 days ago
በስታዲየም ኦፍ ላይት የድራማ ምሽት፤ አርሰናል ሰንደርላንድን 2–0 አሸነፈ!
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ — ኢትዮጵያ
#ethiopia | ዳኛው የጨዋታውን ፍፃሜ የሚያበስረውን ፊሽካ ሲነፉ፣ በስታዲየም ኦፍ ላይት የነበረው ከፍተኛ ውጥረት በደስታና በሐዘን ስሜቶች ተቀይሮ ተጠናቀቀ።
አርሰናል ሰንደርላንድን 2–0 በማሸነፍ ሦስት ነጥብ ይዞ ከሜዳው ወጥቷል። የጨዋታው ታሪክ ግን በውጤቱ ብቻ የሚገለጽ አልነበረም፤ በተለይም የሁለተኛው አጋማሽ ክስተቶችና የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች እጅግ አስደማሚ የእግር ኳስ ምሽት ፈጥረዋል።
ሰንደርላንድ በገዛ ሜዳው ያሳየው የውጊያ መንፈስና ጠንካራ መከላከል ለአርሰናል ቀላል ጨዋታ እንዳልሆነ አሳይቷል።
በ55ኛው ደቂቃ ሰንደርላንድ የፍጹም ቅጣት ምት እድል አግኝቶ ነበር። ነገር ግን ኤንዞ ሌ ፌ ያገኘውን እድል ሳይጠቀምበት ቀረ። ይህም ለሰንደርላንድ አሳዛኝ የጨዋታ መታጠፊያ ነጥብ ሆነ።
ከዚያ አምስት ደቂቃዎች በኋላ፣ በ58ኛው ደቂቃ፣ ከተቀያሪ ወንበር የገባው ብሩኖ ጊማራኤስ ለአርሰናል የመሪነት ግብ አስቆጠረ። ይህች ግብ ጨዋታውን ወደ አርሰናል አቅጣጫ እንዲያዘነብል አድርጋለች።
ሰንደርላንድ እኩልነቱን ለማስመለስ ጫናውን ቢያሳድግም፣ አርሰናል መሪነቱን ጠብቆ ቆይቷል። የጨዋታው ድራማ ግን እስከ መጨረሻው ደቂቃ አልተቋረጠም።
በተጨማሪ ሰዓት 90+6ኛው ደቂቃ ሬይኒልዶ ማንዳቫ በቡካዮ ሳካ ላይ በሰራው ጥፋት ሁለተኛ ቢጫ ካርድ ተመልክቶ ከሜዳ ተባረረ።
ከዚያም በ90+8ኛው ደቂቃ ቡካዮ ሳካ ከፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ የአርሰናልን 2–0 ድል አረጋገጠች።
ይህም በስታዲየም ኦፍ ላይት የነበረውን ድራማ በድል ለአርሰናል፣ በተስፋ መቁረጥ ለሰንደርላንድ አጠናቀቀ።
የእግር ኳስ ዓለም እይታ
የጨዋታው ባህሪ በተለይ ሰንደርላንድ ያሳየውን ጠንካራ መከላከል፣ ያመከነውን የፍጹም ቅጣት ምት እና አርሰናል በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ያሳየውን ብቃት ያጎላል።
የቀድሞ ተጫዋቾችና የስፖርት ተንታኞች በጨዋታው ወቅት የተፈጠሩትን የመታጠፊያ ነጥቦች በመጠቆም፣ በትልቅ ደረጃ የሚገኝ ቡድን እድሎችን ሳይጠቀም ሲቀር መጨረሻ ላይ መቀጣት እንደሚችል ያስታውሳሉ።
ወዳጆቼ!
የእግር ኳስ ውበቱና አነጋጋሪነቱ ያለው እዚህ ላይ ነው። በአንድ ደቂቃ የድል ተስፋን ታጥቆ መታገል፣ በሚቀጥለው ደቂቃ ደግሞ የሽንፈትን መራራ ስሜት መቅመስ!
አርሰናል የጨዋታውን የመጨረሻ አጋጣሚዎች በሚገባ በመጠቀም የድል በሩን ከፍቶ፣ በስታዲየም ኦፍ ላይት አንድ የማይረሳ የድራማ ምሽት ጽፎ ወጥቷል።
ምንግዜም ድል ለመድፈኞቹ!
#arsenal #sunderland #premierleague #football #sports #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የአርሰናል የውድድር ዘመን ፍጹም እና እንከን የለሽ ጉዞ አሁንም ቀጥሏል። በስታዲየም ኦፍ ላይት በነበረው እጅግ ፈታኝ ምሽት፣ መድፈኞቹ በዴቪድ ራያ እና ብሩኖ ጊማሬሽ ሁለት አስማታዊ ቅጽበቶች ታግዘው ሰንደርላንድን በሜዳው ማንበርከክ ችለዋል።
ጨዋታው 55ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ የመድፈኞቹ ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳ ዳን ባላርድን በሳጥን ውስጥ በመጥለፉ ለሰንደርላንድ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጠ። የሰንደርላንዱ ኤንዞ ሉ ፊ ኳሷን ወደ መረብ ለማሳረፍ ቢሞክርም፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ኳሷን በሚገርም ብቃት ወደ ግራ ተወርውሮ አዳናት።
ይህ የራያ ድንቅ ማዳን የፈጠረው ትልቅ ትርጉም በስታዲየሙ የታየው ልክ ከ121 ሰከንዶች በኋላ ነበር። ከእረፍት መልስ ተቀይሮ የገባው ብሩኖ ጊማሬሽ ከ20 ያርድ ርቀት ላይ አስቆጥሮ ያሳረፋት ማራኪ ኳስ፣ የግብ አግዳሚውን ለቃ መረብ ላይ ስታርፍ የአርሰናል ደጋፊዎችን በደስታ አጥለቀለቀች። ይህች ግብ የክረምቱ ፈራሚ በአርሰናል ማልያ ያስቆጠራት የመጀመሪያ ግቡ ስትሆን፣ የቀድሞ ክለቡ ኒውካስል ዩናይትድ የዘላለም ጠላት በሆነው በሰንደርላንድ ላይ መቆጠሯ ደግሞ ለጊማሬሽ ድርብ ደስታ ሆናለች።
በጨዋታው ማጠናቀቂያ ሰከንዶች ላይም፣ ሬይኒልዶ ማንዳቫ በቡካዮ ሳካ ላይ በሰራው ጥፋት (እና በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ በተሰናበተበት ቅጽበት) የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳካ ወደ ግብነት ቀይሮ የአርሰናልን 2-0 አሸናፊነት አረጋግጧል።
በሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ ይህንን ድል ያገኙት በቀላሉ አልነበረም። በመጀመሪያው አጋማሽ 66% የኳስ ቁጥጥር ቢኖራቸውም፣ በሬጂስ ሉ ብሪስ ስልታዊ የሰንደርላንድ ተጫዋቾች ጥብቅ መከላከያ ተተብትበው ነበር። የአርሰናል የጥቃት ሞተር የሆነው ማርቲን ኦዴጋርድ፣ በቀድሞው መድፈኛ ግራኒት ዣካ ተጠፍሮ ከመዋሉም በላይ፤ ካይ ሃቨርትዝ ያገኛቸውን አጋጣሚዎች ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ከዚሁ ጭንቀት የተነሳም አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የቴክኒካል ክልላቸውን ጥሰው በመውጣታቸው የቢጫ ካርድ ሰለባ ሆነዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቤን ዋይት በእረፍት ሰዓት በጉዳት መውጣቱ ለአርሰናል ተጨማሪ ሥጋት ፈጥሮ ነበር።
የአርሰናል የፊት መስመር ተጫዋቾች በተቸገሩበት በዚህ ምሽት፣ የዴቪድ ራያ የግብ ዘብነት ቡድኑን ታድጓል። ስፔናዊው ግብ ጠባቂ በስድስት ጨዋታዎች ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ መረቡን ደፍሮ አስጠብቋል። አርሰናልም በሊጉ እስካሁን ያስተናገደው 9 ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ ብቻ ሲሆን፣ ይህም በሊጉ አነስተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህም አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ስድስት ለዜሮ በማሸነፍ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ተቀምጧል።
በአንጻሩ፣ ሰንደርላንድ ምንም እንኳን ለሊጉ ሻምፒዮን ጠንካራ ፉክክር ቢሰጥም እና ግራኒት ዣካ በሜዳ ላይ ድንቅ እንቅስቃሴ ቢያሳይም፣ በአርሰናል ላይ ያላቸው አስከፊ ታሪክ ግን ሊቀየር አልቻለም። ጥቋቁሮቹ ድመቶች ከአርሰናል ጋር ካደረጓቸው 30 የፕሪሚየር ሊግ ግንኙነቶች ማሸነፍ የቻሉት በአንዱ ብቻ ሲሆን፣ በ18ቱ ደግሞ ድል ርቋቸዋል።
አሁን ላይ በ4 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሰንደርላንድ፣ ይህንን ሽንፈት አራግፎ ከ53 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያደርገው የአውሮፓ ሊግ መድረክ የፊታችን ረቡዕ AZ አልክማርን ለማስተናገድ ዝግጅቱን ይጀምራል።

ጨዋታው አልቋል - ሰንደርላንድ 0 - 2 አርሰናል | እጅግ ማራኪ ጨዋታ ነበር፤ ጥቁሮቹ ድመቶች እስከፍጻሜው ደቂቃ ድረስ ከቶ አልደከሙም፣ አልተልፈሰፈሱም! ግን ድንቅ ዕድሎችን ፈጥረው ሳይጠቀሙበት ቀርተው ጎል ቢስተናገድባቸውም፣ እስከ መጨረሻው ግን ተዋግተዋል። መድፈኞቹ ካገቡ በኋላ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነበር፤ ሮቢን ሮፍስ ቢነካትም ኳሷ ከቁጥጥሩ ውጪ ሆና መረብ ላይ አርፋለች።
ለአርሰናል ግን በእርግጥም ከባድ... እጅግ ከባድ ምሽት ነበር! ሰንደርላንዶች ጽናትን አሳይተዋል፤ አርሰናል ግን ከነሱ በላይ በመጽናት እና ታግሶ በመጫወት አሸናፊ ሆኖ ወጥቷል።
በአጠቃላይ እጅግ ድንቅ ጨዋታ ነበር! አርሰናሎች በStadium of Light የተደረገውን ይህንን ግዙፍ ፈተና በድል አጠናቀው ፍጹም ድንቅ የውድድር ዘመን ጅምራቸው በዚህ መልኩ ቀጥሏል!

አርሰናል ሰንደርላንድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ሰንደርላንድን 2 ለ ዐ አሸንፏል።
በስታዲየም ኦፍ ላይት በተደረገው ጨዋታ የመድፈኞቹን ግቦች ብሩኖ ጊማሬሽ እና ቡካዮ ሳካ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል።
ሰንደርላንድ ጨዋታውን መምራት የሚችልበትን ፍጹም ቅጣት ምት ኢንዞ ሊ ፊ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ሞዛምቢካዊው የሰንደርላንድ ተከላካይ ሬኒልዶ ማንዳቫ በጨዋታው መገባደጃ ላይ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

27 days ago
⚽ አንድ ግብ፣ አንድ ድል፣ ሦስት ነጥብ!
ናፖሊ 0–1 አርሰናል
✍️ በአለባቸው ደሳለኝ አበሻ — ኢትዮጵያ
ግን ከ1–0 ውጤት በስተጀርባ ያለው ታሪክ ምንድነው?
#ethiopia | በውጤት ሰሌዳው ላይ የተቀመጠው አንድ ግብ፣ አንድ ድልና ሦስት ነጥብ ብቻ ነው። ነገር ግን በናፖሊ ሜዳ የተከናወነውን 90 ደቂቃ ሙሉ በሙሉ ለመግለጽ 1–0 በቂ ነው?
መልሱ አይደለም።
ከመጀመሪያው ፊሽካ ጀምሮ አርሰናል ኳሱን በመቆጣጠር ጨዋታውን ለመምራት ተነሳ። ናፖሊ ግን በጥብቅ መከላከያ ወደኋላ ተሰብስቦ ክፍተት ላለመስጠት መረጠ።
የጨዋታው ዋና ስዕልም እዚህ ላይ ተገነባ፦
አርሰናል ይገነባል፣ ናፖሊ ይጠብቃል።
አርሰናል ይጫናል፣ ናፖሊ ክፍተት ሲያገኝ መልሶ ለማጥቃት ይሞክራል።
የሚኬል አርቴታ 4-2-3-1 አሰላለፍም በዚህ የጨዋታ ስዕል ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የመሀል አማካዮቹ ሚዛኑን ሲጠብቁ፣ ከፊታቸው የነበሩት ሦስት አማካዮች የናፖሊን የመከላከያ መዋቅር ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለመክፈት ሞክረዋል።
⏱️ 75ኛው ደቂቃ…
ኳሱ ወደ ማርቲን ኦዴጋርድ ደረሰች። ኖርዌያዊው አማካይ ለማሰብ ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም። ኃይለኛ ምት፣ ኳሷ ከምሰሶው ጋር ተገናኘች፣ ከዚያም መረቡን አንቀጠቀጠች!
ናፖሊ 0–1 አርሰናል! 🔴⚪
የግቡ ውበት ግን በኦዴጋርድ ምት ብቻ አልነበረም።
🔥 29 ተከታታይ ፓሶች!
አርሰናል በትዕግስት ኳሷን አንሸራሸረ፣ ተጫዋቾቹ ቦታ ቀያየሩ፣ ናፖሊም ኳሷን ለመከተል ሲሞክር የመከላከያ መዋቅሩ መፈረካከስ ጀመረ። ከዚያ የመጨረሻው ንክኪ መጣ።
ኦዴጋርድ — አንድ ምት።
አንድ ግብ።
አንድ ድል።
ሦስት ነጥብ።
📊 ከ26 የጎል ሙከራዎች 1 ግብ
አርሰናል 26 የጎል ሙከራዎችን አድርጓል፤ የተጠበቀው የጎል መጠንም 4.05 xG ደርሷል።
ይህም አርሰናል ጨዋታውን በቁጥጥሩ ስር ከማድረጉ በተጨማሪ በተደጋጋሚ የጎል ዕድሎችን መፍጠሩን ያሳያል።
ስለዚህ 1–0 የሚለው ውጤት የጨዋታውን ሙሉ ታሪክ አይናገርም።
⭐ የምሽቱ ሰው — ማርቲን ኦዴጋርድ
የድሉ ፊርማ የሆነውን ግብ ብቻ አላስቆጠረም። 6 የጎል ዕድሎችን ፈጥሯል፤ የናፖሊን የመከላከያ መስመር ለመስበር በሚያግዙ ፓሶችም ቀዳሚ ነበር።
ይህም ኦዴጋርድ የቀድሞ ቅርጹን በማስታወስ ወደ መድረኩ እየተመለሰ መሆኑን ያሳየ ነበር።
የTNT Sports ተንታኝ ጆ ኮል ውጤቱን ብቻ እንዳንመለከት በማሳሰብ ይህን አስደናቂ የአውሮፓ የሜዳ ውጭ አፈጻጸም አድንቆታል። የቀድሞው የአርሰናል ተከላካይ ማርቲን ኪዎንም የመድፈኞቹን ጽናት አድንቆ ቡድኑ ያለመታከት እንደተጫወተ ገልጿል።
🏆 የዚህ ድል እውነተኛ ትርጉም
አርሰናል በናፖሊ ሜዳ ያሳየው ነገር የአንድ ተጫዋች ብቃት ብቻ አልነበረም።
የቡድን ሥራ፣ የተረጋጋ አሰራር፣ የተደራጀ ጨዋታ፣ የኳስ ቁጥጥር፣ የዕድል ፈጠራ እና በጥቂት የጎል ልዩነት እንኳን ውጤትን የማስጠበቅ ብቃት።
እነዚህ ሁሉ በአንድ ላይ ሲጣመሩ፣ አርሰናል በቻምፒዮንስ ሊጉ የጀመረው ጉዞ ጥሩ መልዕክት ይዞ መሆኑን ያሳያል።
ናፖሊ 0–1 አርሰናል።
አንድ ግብ ተቆጠረ።
ሦስት ነጥብ ወደ ኪስ ገባ።
ግን ከውጤቱ በላይ የሚናገር አፈጻጸም ቀረ።
የድሉ ግብ የኦዴጋርድ ነበር።
የድሉ ታሪክ ግን የአርሰናል ነው። 🔴⚪

ከተስፋ ወደ ክብር፤ አርቴታ ያልጨረሰው ጉዞ
✍️ በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | የሰሜን ለንደን ቀይ ለባሾቹ አርሰናል በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ከታላላቅና ስኬታማ ክለቦች ተርታ ቢመደቡም፣ በአውሮፓ ትልቁ መድረክ ያላቸው ሕልም እስካሁን እውን አልሆነም።
“ባለትልቅ ጆሮው” በሚል ቅጽል የሚጠራውን የUEFA ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የማንሳት ሕልማቸው በ2006 በፍራንክ ራይካርድ ባርሴሎና ፊት ተገትቶ ቀርቷል። በቅርቡም በፓሪስ ሴን-ዠርመን ፊት የደረሰባቸው ሽንፈት ያንን የቆየ ቁጭት ዳግም ቀስቅሶታል።
ከክለቡ ታሪካዊ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ስንብት በኋላ የውጤት መንገዱን ያጣውን አርሰናል የተረከበው የፔፕ ጋርዲዮላ ደቀ መዝሙር ሚኬል አርቴታ፣ መድፈኞቹን በትዕግሥት እና በተከታታይ ሥራ ወደ ከፍታቸው መልሷል።
አርቴታ የረጅም ዓመታትን የዋንጫ ጥማት በማስታገስ ክለቡን እንደገና ከእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች ጋር በአንድ ደረጃ አስቀምጧል። አሁን ግን የቀረው አንድ ትልቅ ፈተና ብቻ ነው—የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ኢሚሬትስ ማምጣት።
በአለት የጠነከረ የተከላካይ ክፍል፣ በአውሮፓ ምርጥ ከሚባሉ የአማካይ ስብስቦች አንዱ እና በዝውውር መስኮቱ የተጨመሩ አዳዲስ ኃይሎችን ይዘው፣ መድፈኞቹ ለታላቅ የአውሮፓ ዘመቻ ዝግጁ ናቸው።
ያለፈው የቁጭት ስሜት ገና አልበረደም፤ የዘንድሮው ጉዞ ግን የታሪክ ጉዞ ሊሆን ይችላል?
ከቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊነት እጩዎች ቀዳሚዎቹ መካከል የሚጠቀሱት መድፈኞቹ፣ የአውሮፓ ዘመቻቸውን ከኔፕልስ ይጀምራሉ።
ጥያቄው አንድ ነው...
በመጨረሻ ባለትልቅ ጆሮውን ዋንጫ ወደ ኢሚሬትስ ያመጣሉ?

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ባለፈው የውድድር ዘመን የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የደረሰባቸውን ልብ ሰባሪ ሽንፈት ለማከም ዳግም ወደ አውሮፓ መድረክ የተመለሱት መድፈኞቹ፣ በጣልያኗ ውብ ከተማ ኔፕልስ እጅግ ፈታኝና ትዕግስት አስጨራሽ ምሽት አሳልፈዋል። በናፖሊ ሜዳ የተደረገው ይህ ፍልሚያ አርሰናል ወደ ጎል ባደረጋቸው 26 ሙከራዎች ታጅቦ የነበረ ቢሆንም (ይህም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በቻምፒዮንስ ሊጉ ከፍተኛው የሙከራ ቁጥራቸው ነው)፣ ኳስ እና መረብን ማገናኘት ግን እጅግ አዳጋች ሆኖባቸው ቆይቷል።
መድፈኞቹ ያገኟቸውን ወርቃማ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በማባከን ጨዋታውን በአቻ ውጤት ሊያጠናቅቁ ከጫፍ ደርሰው ነበር። ሚኬል ሜሪኖ ከጥር ወር ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት የተሰለፈበትን አጋጣሚ በጎል ለማጀብ ያገኘውን ድንቅ የጭንቅላት ኳስ የናፖሊው ግብ ጠባቂ አሌክስ ሜሬት በቀላሉ ይዞበታል። ቡካዮ ሳካ የግብ ማግባት እድሉን ወደ ሰማይ ሲሰደው፣ ፒዬሮ ሂንካፒ ከስድስት ያርድ ክልል ውስጥ ያገኘውን ኳስ በግምት አባክኖታል። ጨዋታው ያለ ግብ ሊጠናቀቅ ነው ተብሎ ሲታሰብ፣ መድፈኞቹ የሚያስቆጭ ነጥብ ሊጥሉ መሆኑ ስጋት ፈጥሮ ነበር።
ከዚህም ባለፈ ናፖሊዎች አደጋ መፍጠራቸው አልቀረም። በ2023 ከማንችስተር ሲቲ ጋር የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ የነበረው ኬቨን ዴብሩይነ ከርቀት የመታውን ኃይለኛ ኳስ የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ሲተፋው፣ ቤን ኋይት ፈጥኖ ደርሶ ኳሷን በማራቅ አርሰናልን ከድንገተኛ አደጋ ታድጓል።
ሆኖም ይህ ሁሉ ብስጭት እና የልብ ትርታ በአንድ የካፒቴኑ አስማት ተቀየረ። ማርቲን ኦዴጋርድ ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጪ አስደናቂ ኳስ አስቆጥሮ ወደ ስታዲየሙ ያቀኑትን 1,500 የአርሰናል ደጋፊዎችን በደስታ አጥለቅልቋል። ይህች የድል ግብ ኦዴጋርድ የኮምዩኒቲ ሺልዱን ጨምሮ በአምስት ጨዋታዎች ያስቆጠራት አራተኛው ጎል ስትሆን፣ የውድድር ዘመኑን ድንቅ ጅማሮ በድጋሚ አረጋግጣለች። የጨዋታው ማጠናቀቂያ ፊሽካ ሲነፋ ፒዬሮ ሂንካፒ በጉልበቱ ተንበርክኮ እጆቹን መሬት በመምታት የነበረበትን ከፍተኛ ጭንቀትና ጥልቅ እፎይታ ገልጿል።
ከጨዋታው በኋላ ታላላቅ የዘመኑ የእግር ኳስ ጠበብት ስለ ካፒቴኑ ውዳሴያቸውን አዝንበዋል። የቀድሞው የቼልሲ እና የእንግሊዝ አማካይ ጆ ኮል "በአርሰናል ሁሉም ነገር በኦዴጋርድ በኩል ነው የሚያልፈው፤ በቆመበት ቦታ ክፍተትን መፍጠር የሚችል አስደናቂ ተጫዋች ነው። ብቃቱ ጣሪያ ላይ ደርሷል፤ እሱን ሜዳ ላይ ሲጫወት መመልከት እጅግ ማራኪ ነው" ሲል አሞካሽቶታል። በተመሳሳይ የቀድሞው የመድፈኞቹ ተከላካይ ማርቲን ኪዮን "ኦዴጋርድ ለቡድኑ ልዩ ጣዕም (Icing on the cake) ነው። ከርቀት መትቶ ጎል ሲያስቆጥር ማየቴ ያስገርማል፤ አሁን እውነተኛውን እና የተሟላውን ተጫዋች ሆኖ አይተነዋል" በማለት አድናቆቱን ችሮታል።
ባለፈው ዓመት በምድብ ድልድሉ ስምንቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ አስገራሚ ጉዞ ያደረገው አርሰናል፣ እነሆ ዘንድሮም በአውሮፓ መድረክ ዳግም ግስጋሴውን በካፒቴኑ የጀግንነት ጥበብ ከጣሊያን ምድር ጀምሯል።

1 month ago
28" Arsenal 1 Vs 1 Chealse
ለንደን ቀይ ወይስ ሰማያዊ?
#ethiopia | መላው የእግር ኳስ አፍቃሪ ዓይኑን ኤምሬትስ ላይ ጥሏል።
አርሰናል እና ቼልሲ በታላቁ ደርቢ ጨዋታ በኤምሬትስ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል።
መድፈኞቹ በሜዳቸው ኤምሬትስ በሚያደርጉት በዚህ ወሳኝ ጨዋታ ሦስቱን ነጥብ በመውሰድ የዋንጫ ፉክክራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ሙሉ ዝግጅት አድርገዋል።
ሰማያዊዎቹ ደግሞ የለንደን የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ እና ጠንካራ ተፎካካሪነታቸውን ለማሳየት ወደ ሜዳ ገብተዋል።
የሁለቱም ቡድኖች ወጣት እና ክህሎት ያላቸው አጥቂዎች የሚያደርጉት ፈጣን እንቅስቃሴ የጨዋታው ዋነኛ ማዕከል ሆኗል።
የለንደን ንጉሥ ማን ይሆን?
መድፈኞቹ በሜዳቸው ይደሰታሉ ወይስ ሰማያዊዎቹ ያልተጠበቀ ድል ያስመዘግባሉ?
መልሱን አብረን የምናየው ይሆናል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #arsenal #chelsea #londonderby #premierleague #footballnews

216ኛው የለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ቼልሲ
ሁለቱ የባስክ ግዛት ተወላጆች እና አብሮ አደጎቹ ሚኬል አርቴታ እና ዣቢ አሎንስ በዓለም ትልቁ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ትልልቅ ክለቦችን ይዘው ተፋጠዋል።
እግር ኳስን በተወለዱበት አካባቢ በሚገኝው የአንቲጎኩ አካዳሚ የጀመሩት እና ለ6 ዓመት በዚሁ አካዳሚ አብረው የተጫውቱት አርቴታ እና አሎንሶ ለሪያል ሶሴዳድ ዋናው ቡድንም ተጫውተው አሳልፈዋል።
በባየር ሊቨርኩሰን ድንቅ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ በማድሪድ የተወሰን ጊዜ የቆየው ዣቢ አሎንሶ በቼልሲ ራሱን ለትልቁ ፈተና አዘጋጅቷል።
በሊጉ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ያሸነፈው አሎንሶ፤ የመጀመሪያ ትልቁን ፈተና ዛሬ ይጋፈጣል። ምሽት 12፡30 በኤምሬትስ ከሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ አርሰናልም የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ያሸነፈ ሲሆን በአሸናፊነቱ ለመቀጥል በለንደን ደርቢ ጠንካራ የፊት መስመር ካለው ቼልሲ ይገናኛል።
በኤምሬስት የሚደረገው ጨዋታ 7 ግቦችን ያስቆጠረው የቼልሲ የፊት መስመር ምንም ግብ ካልተቆጠረበት የአርሰናል ተከላካይ የሚያደርጉት ትንቅንቅ በመሆኑ ጨዋታውን እንዲጠበቅ የሚያደርግው ሲሆን በሌላ በኩል ሁለቱ ስፔናዊያን ታክቲሺያን ጨዋታውን እንዴትባለ መልኩ ይወጡታል የሚለው የሚጠበቅ ነው።
አርሰናል ከቼልሲ በተገናኝባቸው ያልፉት 9 ጨዋታዎች በአንዱም ያልተሸነፍ ሲሆን 6ቱን አሸንፏል።
በጨዋታው በመድፈኞቹ በኩል ዩሪየን እና ዊሊያም ሳሊባ አሁንም ከጉዳቱ ያልተመለሱ ተጨዋቾች ሲሆኑ፤ ኤዝሪ ኮንሳ በመድፍኞቹ ማልያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት ሊጀምር ይችላል ተብሏል።
ሞይሰስ ካይሴዶ የመሰለፉ ነገር ያልተረጋገጥ ሲሆን ጆርዳን ሄንደርሰን እና ፓሊስትራ አሁንም በጉዳት ከስብስቡ ውጪ ናቸው።
Seledadotio

አርሰናል አዲሱን ጆርጂያዊ የ17 ዓመት ኮከብ አስፈረመ
#ethiopia | የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የ17 ዓመቱን ጆርጂያዊ አንድሪያ ባርቲሽቪሊን ማስፈረሙን አረጋግጧል።
ወጣቱ ተጫዋች ትናንት የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቀ በኋላ በሎንዶን ኮልኒ የስልጠና ማዕከል በመገኘት ኮንትራቱን በይፋ ፈርሟል።
በአውሮፓ እግር ኳስ ቀጣዩ ትልቅ ኮከብ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ወጣት ከሰኔ 2027 ጀምሮ በይፋ የመድፈኞቹን ማሊያ ለብሶ መጫወት የሚጀምር ይሆናል።
አርሰናል የወደፊት የቡድኑን የፊት መስመር እና አማካኝ ክፍል ለማጠናከር ያደረገው ይህ ዝውውር ክለቡ ለወጣት ሃያላን የሚሰጠውን ትልቅ ትኩረት እና ረጅም የእቅድ የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ጋብሬል ማርቲኔሊ፣ በአርሰናል ቤት የተጻፈ የትጋት ታሪክ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሰናል የቅርብ ዓመታት የዳግም ግንባታ ጉዞ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል ጋብሬል ማርቲኔሊ አንዱ ነው። ወጣቱ ብራዚላዊ በፍጥነቱ፣ በጉልበቱ፣ ተከላካዮችን በአንድ ለአንድ ለመጋፈጥ ባለው ድፍረቱ እና ጎል ለማስቆጠር ባለው ክህሎት የመድፈኞቹ ደጋፊዎችን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
ጋብሬል ቴዎዶሮ ማርቲኔሊ ሲልቫ በፈረንጆቹ 2001 በብራዚል ሳኦ ፖሎ ግዛት ጉዋሩልዮስ ተወለደ።
የእግር ኳስ ህይወቱን በኮረንቲያንስ አካዳሚ በመጀመር በኋላም በኢቱዋኖ ቀጠለ። በኢቱዋኖ በዋናው ቡድን ዕድል ካገኘ በኋላ የብራዚላዊው ወጣት ችሎታ በአውሮፓ የተለያዩ ክለቦች ዓይን ውስጥ ገባ።
በመጨረሻም እ.ኤ.አ በ2019 አርሰናል፣ ተስፈኛውን ታዳጊ ተጫዋች ወደ ሰሜን ለንደን አመጣው። ማርቲኔሊ በአርሰናል ቤት የተሰጠውን ዕድል በፍጥነት በመጠቀም ለቡድኑ የሚያስፈልገው የግብ ስጋት ሆነ።
ማርቲኔሊ ወደ አርሰናል ሲመጣ ብዙዎች እንደ ተስፈኛ ወጣት ተጫዋች ብቻ ይመለከቱት ነበር። እሱ ግን የሰዎችን ግምት በፍጥነት ለወጠው። ፍጥነቱን በመጠቀም በግራ ክንፍ ተከላካዮችን መጫን፣ ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ መግባት እና ጎል ማስቆጠር የአጨዋወቱ ዋነኛ መለያዎች ሆኑ።
በተለይም በ2019/20 የውድድር ዘመን ያሳየው ብቃት የአርሰናል ደጋፊዎች በወጣቱ ላይ ትልቅ ተስፋ እንዲጥሉ አደረገ። እሱ በሜዳ ላይ የሚያሳየው ትጋትና የማይታክት ሩጫ ለቡድኑ አጨዋወት መለያ እየሆነ መጣ።
ለማርቲኔሊ የአርሰናል ቆይታ እጅግ የሚታወሰው የ2022/23 የውድድር ዘመን ነው። በዚያ ወቅት ተጫዋቹ በፕሪሚየር ሊጉ 36 ጨዋታዎች በመሳተፍ 15 ጎሎችን አስቆጠረ፤ በተጨማሪም 5 የግብ እድሎችን ፈጥሯል፡፡
ይህ የግል ብቃቱ ብቻ ሳይሆን አርሰናል እስከ መጨራሻው ሰዓት የሊጉ አሸናፊ ለመሆን ከፔፕ ጓርዲዮላው ማንቼስተር ሲቲ ጋር የተፋለመበት ወቅት ነበር። ማርቲኔሊ፣ ቡካዮ ሳካ እና ሌሎች ወጣት ተጫዋቾች የአርሰናልን የወደፊት ቡድን ምስል እንዲያሳይ አጨዋወት አሳይተዋል።
ማርቲኔሊን ከሌሎች የክንፍ ተጫዋቾች የሚለየው ነገር በኳስ ላይ ያለው ችሎታ ብቻ አይደለም። ኳስ ሲበላሽበት ወዲያውኑ መልሶ ለመንጠቅ የሚያደርገው ጥረት፣ ተከላካይን በፍጥነት ለመጫን ያለው ፍላጎት እና ከኳስ ውጭ የሚያደርጋቸው ሩጫዎቹ ናቸው።
የግራ ክንፍ ቦታውን በመያዝ ወደ ውስጥ በመግባት በቀኝ እግሩ ጎል ለመሞከር የሚያደርገው እንቅስቃሴም የተለመደ ነበር። በአርሰናል ቤት ቆይታው 41 ግችንና 24 ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበሉ የሚያሳየውም በቡድኑ የማጥቃት ሥርዓት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ተፅዕኖ ነው።
በመጨረሻዎቹ የአርሰናል ቆይታው የማርቲኔሊ የመጫወቻ ጊዜ እንደ ቀድሞው የተረጋጋ አልነበረም። የቡድኑ የማጥቃት አማራጮች መጨመር፣ የተጫዋቾች ውድድር እና ራሱ የማርቲኔሊከቡድኑ እኩል ማደግ አለመቻል በቋሚ 11 ውስጥ የመሰለፍ እድሉን አመነመነው፡፡
በ2025/26 የውድድር ዓመት 30 ጨዋታዎች ቢያደርግም በ11 ብቻ ነው በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ለመግባት የቻለው፡፡ በዚህም አንድ ግብና 4 የግብ እድሎችን ብቻ አስመዝግቧል።
በአጠቃላይ በአርሰናል ቆይታው 191 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በማድረግ 41 ግቦችና 24 የግብ እድሎችን በማስመዝገብ በመድፈኞቹ ቤት የራሱን ታሪክ አኑሯል፡፡
ብራዚላዊው አቦ ሸማኔ በተዘጋው የዝውውር መስኮት ወደ ሳዑዲው አል ሂላል እግር ኳስ ቡድን ተዛውሯል፡፡ ከአርሰናል መለየቱ ለብዙ የመድፈኞቹ ደጋፊዎች ቀላል የሆነ ዜና አልነበረም። በተለይም በቡድኑ ውስጥ ካሳለፈው ረጅም ጊዜ እና ከደጋፊዎች ጋር ከፈጠረው ትስስር አንፃር መሰናበቱ የአንድ ዘመን የታሪክ ምዕራፍ መዝጊያ ይመስላል።
ከአርሰናል ጋር ያሳለፋቸው ዓመታት ሲደመሩ ማርቲኔሊ በክለቡ ታሪክ ውስጥ የራሱን ምዕራፍ ጽፏል። ወደ ክለቡ የመጣው እንደ ወጣት ተስፈኛ ነበር፤ የወጣው ግን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆን ነው፡፡
ማርቲኔሊም ከአርሰናል የሚወጣው በፍጥነቱ ተከላካዮችን ሲያስጨንቅ፣ ግብ ሲያስቆጥር፣ በሜዳ ላይ ሲሮጥ እና የመድፈኞቹን ማልያ በኩራት ሲለብስ የታዩትን ትዝታዎች ትቶ ነው።
ከለንደን ወደ ሳዑዲ የተደረገው ጉዞ ለማርቲኔሊ አዲስ ምዕራፍ ቢሆንም፣ በአርሰናል የተጻፈው ታሪክ ሁሌም የእግር ኳስ ሕይወቱ አንድ ትልቅ ክፍል ሆኖ ይዘልቃል።

"አስቶን ቪላ በርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን በማጣቱ አሁንም እንደ አዲስ ራሱን እየገነባ የሚገኝ ቡድን ነው። ለአርሰናል ግን ይህ የዛሬው ድል ተራ ማሸነፍ አይደለም፤ ተጋጣሚን ወደ ግብ ምንም ዓይነት ሙከራ እንዳያደርግ ሙሉ በሙሉ አፍኖ በማስቀረት ያገኘው ግዙፍ እና 'መልዕክት አዘል' ድል ነው!
"መድፈኞቹ በሚገርም ሁኔታ ትዕግስተኞች፣ ንቁ እና በስልት የበሰሉ ነበሩ። ጨዋታውን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በቁጥጥራቸው ስር አድርገውት ነበር። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታም ቡድኑ እያሳየ ባለው ጠንካራ እና የማይዋዥቅ አቋም ልቡ በደስታ እንደሚሞላ አያጠራጥርም።"
- ጋሪ ኔቪል

መድፈኞቹ በፕሪሚየር ሊጉ የጀመሩትን ግብ የማስቆጠር አስፈሪ ጉዞ አጠናክረው ቀጥለዋል! መድፈኞቹ በሊጉ ባደረጓቸው ያለፉት 18 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ የተጋጣሚን መረብ ሳያናውጡ የወጡበት ጊዜ የለም።
ይህ አስደናቂ ስኬትም ክለቡ ከነሐሴ 2018 (እ.ኤ.አ) እስከ ጥር 2019 ድረስ በ20 ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ካስቆጠረበት ጊዜ ወዲህ፣ በውድድሩ ያስመዘገበው እጅግ ረጅሙ እና አስገራሚው የግብ ማስቆጠር ሪከርድ ሆኖ በታሪክ ማህደሩ ሰፍሮለታል።

ለመድፈኞቹ ተስፋን የፈነጠቀው ክሪስቶስ ዞሊስ…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግሪካዊው የ24 ዓመት የመስመር ተጫዋች ክሪስቶስ ዞሊስ በአርሰናል የጀመረው አዲስ የእግር ኳስ ምዕራፍ በጥሩ አጀማመር ተውቧል።
ተጫዋቹ በ2026/27 የፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ አርሰናል ኮቨንትሪ ሲቲን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ ለቡካዮ ሳካ የግብ እድል በመፍጠር ትኩረት ስቧል።
ዞሊስ የእግር ኳስ ሕይወቱን በግሪኩ ፓኦክ አካዳሚ አጎልብቶ ወደ ዋናው ቡድን በመድረስ በወጣትነቱ ራሱን ማሳየት ጀመረ። በፓኦክ ቆይታው በሁሉም ውድድሮች በ57 ጨዋታዎች 17 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
የፓኦክ ብቃቱ ድንበር ተሻግሮ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አቅሙን ለማሳየት መንገድ ከፍቶለታል፡፡
በፈረንጆቹ 2021 ወደ ኖርዊች ሲቲ ተዛወረ። ሆኖም በእንግሊዝ ያሳለፈው የመጀመሪያ ጊዜ ቀላል አልነበረም፤ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የመሰለፍ በቂ እድል ባለማግኘቱ በውሰት ወደ ኤፍሲ ቴዌንቴ እና ፎርቱና ዱሰልዶርፍ አመራ፡፡
ዞሊስ በፎርቱና ዱሰልዶርፍ ያሳለፈው የ2023/24 የውድድር ዘመን የሕይወቱ አስፈላጊ የለውጥ ወቅት ነበር። ለቡድኑ በ30 ጨዋታዎች የተሰለፈ ሲሆን፤ 22 ግቦች እና 6 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማስመዝገብ ግብ አስቆጣሪነቱንና የፈጠራ ችሎታውን አሳየ።
በፈረንጆቹ 2024 ወደ ቤልጂየሙ ክለብ፤ ክለብ ብሩዥ በመዛወር በመጀመሪያው የውድድር ዘመን 16 የሊግ ግቦችን እና 9 የግብ እድሎችን የፈጠረው ዞሊስ በ2025/26 የውድድር ዘመን በቤልጂየም ሊግ 36 ጨዋታዎች ላይ 17 ግቦችን እና 23 የግብ እድሎችን በመፍጠር 40 የግብ አስተዋፅዖዎችን አስመዝግቧል።
አርሰናል ዞሊስን ሲያስፈርም በግራ መስመር በኩል የነበረበትን ክፍተት በተለይም ፍጥነት፣ የግብ አስተዋጽኦ እና የፈጠራ ችሎታው የላቀ ተጫዋቸን በማምጣት ቦታውን ለማጠናከር በማሰብ ነው፡፡
ተጫዋቹ በብሩዥ ያሳየው የግብና የግብ እድሎችን የመፍጠር ቁጥር እንዲሁም በአውሮፓ ውድድሮች ያገኘው ልምድ ለአርሰናል ተመራጭ አድርጎታል።
ክሪስቶስ ዞሊስ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ጨዋታዎች፣ በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ እንዲሁም በሊጉ በኮቨንትሪ ላይ ያሳየው ብቃት ተጫዋቹ በመድፈኖቹ ቤት አጀማማሩን አሳምሮለታል፡፡
በጨዋታው ከሳካ ጋር የፈጠረው ግንኙነት እና በግራ መስመር ያሳየው እንቅስቃሴ የአርሰናል የማጥቃት መስመር ተጨማሪ ኃይል እንዳገኘ ያመላክታል።
ፍጥነት፣ አካላዊ ብቃት፣ ብሃት እዲሁም የላቀ ውሳኔ አሰጣጡ ከቡድኑ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አድናቆትን አስገኝቶለታል፡፡
ነገር ግን የዞሊስን በአርሰናል የሚኖረውን ስኬት በአንድ ጨዋታ ብቻ መመዘን አይቻልም። ፕሪሚየር ሊግ ከቤልጂየም ሊግ በተለየ መልኩ ፈጣን፣ አካላዊ እና በትንሽ ስህተት የሚቀጣ ውድድር ነው። ስለዚህ ዞሊስ በብሩዥ ያሳየውን የግብ አምራችነት ብቃት በእንግሊዝ ማስቀጠል ዋናው ፈተና ይሆናል።
የክሪስቶስ ዞሊስ የእግር ኳስ ጉዞ በአንድ ሌሊት የተፈጠረ ስኬት አይደለም። ከግሪክ ወጣት አካዳሚ ተጫዋችነት ተነስቶ በፓኦክ፣ ኖርዊች፣ ቴዌንቴ፣ ዱሰልዶርፍ እና ክለብ ብሩዥ በኩል አልፎ ዛሬ አርሰናል ደርሷል።
የእርሱ ታሪክ ችሎታ ብቻ ሳይሆን ከአስቸጋሪ ወቅቶች በኋላ መመለስና ራስን እንደገና ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑንም የሚያሳይ ነው።
ዞሊስ ለግሪክ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ድረስ 32 ጨዋታዎችን አድርጎ 9 ግቦችን አስቆጥሯል።
ከፓኦክ የተነሳው እና በብሩዥ የፈነጠቀው የግሪክ ተስፈኛ አሁን በአርሰናል ታሪክ ውስጥ የራሱን ስም ለመጻፍ በር ተከፍቶለታል።
የመጀመሪያው ጨዋታ ጥሩ ምልክት ሰጥቷል፤ ቀጣዩ ፈተና ግን ይህንን ብቃት በተከታታይ ጨዋታዎች ማረጋገጥ ነው።

2 months ago
ሀል ሲቲ ከማንቸስተር ዩናይትድ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥለው ይደረጋሉ።
ሊጉ ትናንት ምሽት አርሰናል ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሲጀመር፤ መድፈኞቹ 3 ለ ዐ አሸንፈዋል።
ዛሬ ቀን 8 ሰዓት ከ30 ማንቸስተር ከሜዳው ውጭ ተጉዞ አዲስ አዳጊውን ሀል ሲቲ በመግጠም የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።
ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ ኢፕስዊች ታውን ከሰንደርላንድ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ ቀን 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
በዕለቱ የመጨረሻ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐር ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ይገናኛሉ።
የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ
ፌስቡክ https://web.facebook.com/f...
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ባለፈው የውድድር ዘመን የ22 ዓመታቱን የዋንጫ ጥማት ያረካው የሚኬል አርቴታው ስብስብ፣ ዘንድሮም ክብሩን ለማስጠበቅ ቀዳሚ ግምቱ እንደሚሰጠው በሜዳ ላይ በተግባር አሳይቷል። በኤምሬትስ ስታዲየም አዲስ አዳጊውን እና ፍራንክ ላምፓርድ የሚያሰለጥነውን ኮቨንትሪ ሲቲን ያስተናገደው አርሰናል፣ 3 ለ 0 በሆነ አሳማኝ ውጤት አሸንፏል።
ገና ከጅምሩ ፍጹም ብልጫ የወሰዱት መድፈኞቹ፣ በ15ኛው ደቂቃ ላይ አዲሱ ፈራሚ ሪካርዶ ካላፊዮሪ ያሻገረለትን ኳስ ካይ ሃቨርትዝ መረብ ላይ በማሳረፍ ቀዳሚ አድርጓቸዋል። (ሃቨርትዝ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል!)። ከስምንት ደቂቃዎች በኋላም የኮቨንትሪው ግብ ጠባቂ ካርል ረሽዎርዝ የግሪካዊውን ክሪስቶስ ዞሊስን ሙከራ ሲመልስበት፣ ኳሷን ያገኘው ቡካዮ ሳካ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮታል። በሁለተኛው አጋማሽ 4ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ ከቤን ኋይት የተቀበለውን ኳስ አስቆጥሮ የአርሰናልን ፍጹም የበላይነት እና የጨዋታውን ውጤት አረጋግጧል።
አርሰናል በጉዳት ምክንያት አዲሱን ፈራሚ ብሩኖ ጊማሬስን ባያሰልፍም (እንዲሁም ቪክቶር ጂዮከሬስ በተቀያሪ ወንበር ላይ ቢቀመጥም)፣ ሌላኛው አዲስ ፈራሚ ክሪስቶስ ዞሊስ ግን በፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታው ላይ ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ አምሽቷል። በግራ መስመር ተሰልፎ እረፍት የነሳው ዞሊስ፣ ኳሶችን በመቀማትና ዕድሎችን በመፍጠር ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ግቦች መቆጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በሌላ በኩል ሪካርዶ ካላፊዮሪ በግራ መስመር የማያቋርጥ የኃይል ምንጭ ሆኖ ያመሸ ሲሆን፤ ጋብሬል ማጋልሄስም የዊሊያም ሳሊባን አለመኖር ሳያሳብቅ የኋላ ክፍሉን በጽናት መርቷል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ለደጋፊዎች የተዋወቀው አዲሱ ፈራሚ ኤዝሪ ኮንሳም በቀጣይ ከጋብሬል ጋር የሚኖረው ጥምረት በጉጉት ይጠበቃል።
ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ፣ የሊጉ ፉክክር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በገሃድ አይቷል። በክረምቱ የዝውውር መስኮት 130 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጡት እና በክለቡ የሪከርድ ዋጋ (£23m) የተገዛውን ካሌብ ይሬንኪን ጨምሮ አምስት አዳዲስ ፈራሚዎችን ያሰለፉት የፍራንክ ላምፓርድ ልጆች፣ በጨዋታው ላይ ኢላማውን የጠበቀ አንድ ኳስ ብቻ ነው መሞከር የቻሉት። ላምፓርድ እንደ ተጫዋች 3 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ቢያነሳም፣ ለተጫዋቾቹ ግን ሊጉ ፈጽሞ አዲስ እና ፈታኝ ሆኖባቸዋል።
በቀጣይ መድፈኛው ሰኞ፣ ኦገስት 31 (20:00 BST) ከ አስቶን ቪላ ጋር ከሜዳው ውጪ ይጫወታል። ኮቨንትሪ ሲቲ በበኩሉ ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 በካራባዎ ካፕ ሁለተኛ ዙር ከ ፕሊማውዝ አርጋይል ጋር ከተጫወተ በኋላ፤ ቀጣዩን የሊግ ጨዋታውን ከሌላኛው አዲስ አዳጊ ሀል ሲቲ ጋር በሜዳው (ቅዳሜ፣ ኦገስት 29) ያደርጋል። ኮቨንትሪ በቀጣዩ ወር ከማንቸስተር ሲቲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ከባድ ጨዋታዎች ስለሚጠብቁት የሀል ሲቲው ጨዋታ እጅግ ወሳኝ ይሆንበታል።

አርሰናል ኮቨንትሪ ሲቲን 3 ለ ዐ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል አዲስ አዳጊውን ኮቨንትሪ ሲቲ 3 ለ ዐ በማሸነፍ የ2026/27 የውድድር ዓመትን በድል ጀምሯል።
የመድፈኞቹን ግቦች ካይ ሀቨርት፣ ሳካ እና ኦዴጋርድ ከመረብ አሳርፈዋል።
የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ
ፌስቡክ https://web.facebook.com/f...
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል አዲስ አዳጊውን ኮቨንትሪ ሲቲ 3 ለ ዐ በማሸነፍ የ2026/27 የውድድር ዓመትን በድል ጀምሯል።
የመድፈኞቹን ግቦች ካይ ሀቨርት፣ ሳካ እና ኦዴጋርድ ከመረብ አሳርፈዋል።
የፋና ስፖርት የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾችን ይወዳጁ
ፌስቡክ https://web.facebook.com/f...
ቴሌግራም ?? https://t.me/FMCSport
2 months ago
አርሰናል ከ ኮቨንትሪ ሲቲ - የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ጨዋታ
***********************
በመጀመሪያው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ሻምፒዮኑ አርሰናል አዲስ አዳጊውን ኮቨንትሪ ሲቲን በኢሚሬትስ ያስተናግዳል።
በፕሪሚየር ሊጉ ከ22 ዓመታት በኋላ ሻምፒዮን የሆነው አርሰናል ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ሁሉንም የመክፈቻ ጨዋታዎቹን በድል ጀምሯል። በተለይም መድፈኞቹ ወደ ሊጉ አዲስ ከሚመጡ ቡድኖች ጋር በሜዳቸው ባደረጓቸው ያለፉት 45 ጨዋታዎች ሽንፈት አለማስተናገዳቸው ለዛሬው ጨዋታ ትልቅ የሞራል የበላይነት ይሰጣቸዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ ምሽት በጨዋታው ቡድናቸውን ለድል ካበቁ ከፔፕ ጋርዲዮላ፣ ከጆዜ ሞሪንሆ፣ከየርገን ክሎፕ እና ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በመቀጠል በታሪክ በ249 ጨዋታዎች 150 የፕሪሚየር ሊግ ድሎችን ያስመዘገቡ አምስተኛው አሰልጣኝ በመሆን ስማቸውን በታሪክ መዝገብ ላይ ያሰፍራሉ።
በተቃራኒው እንግዶቹ ኮቨንትሪ ሲቲዎች ከ25 ዓመታት ረጅም የሊጉ ቆይታ በኋላ ወደ ታላቁ መድረክ ተመልሰዋል። ይህ ረጅም ቆይታ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ በአንድ ቡድን የተመዘገበ ከፍተኛው ጊዜ ነው።
በቀድሞ የቼልሲ ኮከብ ፍራንክ ላምፓርድ የሚመሩት ኮቨንትሪዎች፣ ምንም እንኳን በ1993 የውድድር ዘመን መክፈቻ አርሰናልን በሜዳው 3 ለ 0 ያሸነፉበት ትዝታ ቢኖራቸውም፣ ከዚያ በኋላ ባደረጓቸው 14 የሊግ ግንኙነቶች ግን ማሸነፍ የቻሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
አርሰናል ወሳኞቹን ተከላካዮች ዊሊያም ሳሊባን እና ዩሪየን ቲምበርን በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የማያገኝ ሲሆን፣ በኮቬንትሪ በኩል ደግሞ ሀጂ ራይት በተመሳሳይ ምክንያት እንደማይሰለፍ ታውቋል።
ዛሬ በሚደረገው በዚህ የመክፈቻ ጨዋታ፣ አርሰናል አሸንፎ ይወጣ ይሆን? ወይስ ኮቨንትሪ? ግምታችሁን አጋሩን።
በዘረንቶስ ሰለሞን
#arsenal #coventrycity #premierleague #epl #arteta #lampard #football #matchday #ebcdotstream

ጋላታሳራይ ቪክቶር ኦሲሜንን ለአርሰናል አልሸጥም ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጠ
የቱርኩ ግዙፍ ክለብ ጋላታሳራይ፣ የፊት መስመር አጥቂ ፍለጋ ላይ ለሚገኘው አርሰናል ቪክቶር ኦሲሜንን በምንም ዓይነት ሁኔታ የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው አስታወቀ።
መድፈኞቹ ባለፈው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 21 ጎሎችንቢያስቆጥርም ወጥ የሆነ አቋም ለማሳየት የተቸገረውን ቪክቶር ዮከሬስን የሚፎካከር ሌላ አጥቂ ለማስፈረም ይፈልጋሉ። በተጨማሪም ጋብሬል ሱስ ክለቡን ለመልቀቅ በመቃረቡ፣ ክለቡ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን ለማስከበርና በቻምፒየንስ ሊግ ስኬታማ ለመሆን የፊት መስመሩን ማጠናከር ግዴታ ሆኖበታል።
አርሰናልቀደም ሲል የዋና ኢላማው ያደረገውን አትሌቲኮ ማድሪድ አልቫሬዝን የማስፈረም እቅዱ መደናቀፉን ተከትሎ (አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድና ባርሴሎና የቀረቡለትን ጥያቄዎች ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ)፣ ፊቱን ወደ ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦሲሜን አዙሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋላታሳራይም በበኩሉ የአርሰናሎቹን ገብርኤል ማርቲኔሊ እና ኢታን ንዋኔሪን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ዕድሜው 27 የደረሰው ኦሲሜን ከናፖሊ ከተዛወረ ወዲህ በቱርክ በነበረው ቆይታ በ74 ጨዋታዎች 59 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን፣ በክለብ እስካሁን 175 ጎሎችን አዝንቧል።
ስለ መጪው እድሉ ተጠይቆም "በዝውውር ወቅት ወሬዎች ሁልጊዜ አሉ፤ ትኩረቴ በስራዬ ላይ ነው፣ ወደፊት የሚሆነውን አብረን እናያለን" ሲል መውጣቱን አልሸሸገም።
ነገር ግን የጋላታሳራዩ ፕሬዚዳንት ዱርሱን ኦዝቤክ ለቅርብሰዎቻቸው እንደተናገሩት "ለጋላታሳራይ ጥቅም የሌለውን ማንኛውንም ዝውውር አልቀበልም። ዋጋው ምንም ያህል ይሁን ምን ኦሲሜንን አልሸጥም" ብለዋል። ክለቡ ቀደም ሲል ከሳውዲው አል ሂላል የቀረበለትን የ130 ሚሊዮን ዩሮ (€130m) ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል።
ሆኖም የጋላታሳራይ አቋም ቢጠነክርም፣ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተጫዋቹን ለማስፈረም ቁርጠኛ እንደሆነና ኦሲሜንን ከጁሊያን አልቫሬዝ ይልቅ በቀላሉ ማግኘት የሚቻል እንደሆነ አድርጎ እንደሚመለከተው ተገልጻል።

ማን ያሸንፋል?!
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ለኮሚኒቲ ሺልድ ክብር ይፋለማሉ
#ethiopia | የእንግሊዝ የእግር ኳስ የውድድር ዘመን መክፈቻ የሆነው የኮሚኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል።
ይህ ውድድር የፕሪሚየር ሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊዎችን የሚያገናኝ ሲሆን አንድ ክለብ ሁለቱንም ዋንጫዎች ካነሳ በሊጉ ሁለተኛ የወጣው ቡድን ይሳተፋል።
በዚህ መሠረት የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል የኤፍ ኤ ካፕ ባለድሉን ማንችስተር ሲቲን የሚገጥም ይሆናል።
ይህ ጨዋታ የዋንጫ ፍልሚያ ቢሆንም በእንግሊዝ እግር ኳስ የሚሰጠው ግምት አነስተኛ ነው። አንዳንዶች እንደ ጠንካራ የወዳጅነት ጨዋታ የሚቆጥሩት ሲሆን ዋንጫውም እንደ ዋና ዋና ውድድሮች አይታሰብም። ይህም ሆኖ ክለቦች ዋንጫውን ለማንሳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።
ዛሬ አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በ104ኛው የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ የሚያደርጉት ፍልሚያ ዋና ዓላማ ጋሻ መሰሉን ዋንጫ ማሸነፍ ነው።
ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በማንሳት ለዚህ ጨዋታ የበቃው አርሰናል የኮሚኒቲ ሺልድን 17 ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በዚህ ዘርፍ የሚበለጠው 21 ጊዜ ካሸነፈው ማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ነው። መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ ይህን ዋንጫ ያነሱት ማንችስተር ሲቲን በመለያ ምት በማሸነፍ ነበር።
በሌላ በኩል ማንችስተር ሲቲ ዋንጫውን ሰባት ጊዜ ያነሰ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈው በ2024 ማንችስተር ዩናይትድን በመለያ ምት አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል።
በዛሬው ጨዋታ በአርሰናል በኩል ቡካዮ ሳካ፣ ዴክላን ራይስ፣ ማርቲን ዙቢሜንዲ እና አዲሱ ፈራሚ ብሩኖ ጊማሬሽ ይሰለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በማንችስተር ሲቲ በኩል ደግሞ ኧርሊንግ ሀላንድ እና አዲሱ ፈራሚ ኤሊዮት አንደርሰን የመጫወት ዕድል ያላቸው ሲሆን አማካዩ ሮድሪ ግን ይሰለፋል ተብሎ አይጠበቅም።
በካርዲፍ ሚሊኒየም ስታዲየም የሚካሄደው ይህ ጨዋታ ምሽት 11:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል።
#arsenal #mancity #communityshield #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

አርሰናል ከ ማንቸስተር ሲቲ - የኮሚዩኒቲ ሺልድ አሸናፊን የሚለየው ፍልሚያ
*************************
የ2026 የኢንግሊዝ ኮሚዩኒቲ ሺልድ ዓመታዊ የዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል። የኢንግሊዝ እግር ኳስ የውድድር ዘመን መክፈቻ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ መርሐ-ግብር፣ የቀደመውን የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን አርሰናልን ከኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ማንቸስተር ሲቲ አገናኝቷል።
ይህ ታሪካዊ ጨዋታ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከለንደን ውጭ በዌልስ ካርዲፍ በሚገኘውና 74,500 ተመልካቾችን በሚይዘው ፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም ይካሄዳል።
የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን የሚኬል አርቴታው አርሰናል፣ በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ወቅት ከጂሮና እና ኤምኬ ዶንስ ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በድል ቢያጠናቅቅም፣ ከሪያል ቤቲስና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሽንፈት ገጥሞታል።
ሆኖም ባለፈው ረቡዕ ከጣሊያኑ ክለብ ኮሞ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመለያ ምት በማሸነፍ ለዚህ የዋንጫ ፍልሚያ መልካም ስንቅ ሰንቋል።
የአርሰናሉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ለመድፈኞቹ ስጋት ሆኗል።
ለማንቸስተር ሲቲ ይህ ጨዋታ የፔፕ ጋርዲዮላ ስኬታማ ዘመን አብቅቶ ከአዲሱ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ጋር የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው።
ሲቲ በቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት ጨዋታዎች ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ከኬ ሊግ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች የ3 ለ 1 ተከታታይ ድል አስመዝግቧል።
በሁለቱ ቡድኖች የቅርብ ጊዜ ግንኙነት ማንቸስተር ሲቲ የበላይነት አለው። ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ሲቲ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ፣ አርሰናል አንድ ጊዜ ባለ ድል ሆኗል። በተቀሩት ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡
የኮሚዩኒቲ ሺልድ ዋንጫን አርሰናል 17 ጊዜ፣ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ 7 ጊዜ አንስተዋል። በ2023 አርሰናል ሲቲን በመለያ ምት አሸንፎ ዋንጫውን ማንሳቱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
ዛሬ 11:00 ሰዓት በሚጀምረው በዚህ ጨዋታ ማን የዓመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ ያነሳ ይሆን? ግምታችሁን አጋሩን።
በዘረንቶስ ሰለሞን
#communityshield #arsenal #mancityfc #premierleague #epl #facup #football #sports #ebcdotstream

ኮሚኒቲ ሺልድ - የእንግሊዝ እግር ኳስ አዲሱን የውድድር ዘመን መጀመር የሚያበስር ዋዜማ
***********************
የክረምቱ የእግር ኳስ ዝምታ ተጠናቆ የፕሪማየር ሊጉ ትኩሳት ከመጀመሩ በፊት፣ የእንግሊዝ እግር ኳስ አዲሱን የውድድር ዘመን በይፋ የሚያበስርበት ታሪካዊው የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ነገ ይደረጋል።
ይህ ጨዋታ ለደጋፊዎች ተራ የዋንጫ ፍልሚያ ሳይሆን፣ “እግር ኳስ በይፋ ተመልሷል!” የሚል ታላቅ የዋዜማ በዓል ነው።
የ118 ዓመታት ታሪክ ያለው ኮሚኒቲ ሺልድ ፕሮፌሽናል እና አማተር ክለቦችን በማገናኘት ለበጎ አድራጎት ተግባራት የሚውል ገቢ ለመሰብሰብ በማሰብ ነበር የተጀመረው።
ኋላ ላይ፣ የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (FA) ሙሉ በሙሉ ተረክቦት የሊግ አሸናፊዎችን ከሳውዘርን ሊግ አሸናፊዎች ጋር ማፋለም ጀመረ።
እ.አ.አ. ከ1921 ጀምሮ ደግሞ የአንደኛው ሊግ አሸናፊ ከኤፍ ኤ ካፕ ባለድል ጋር የሚገናኝበትን ዘመናዊ ቅርፅ ያዘ።
ውድድሩ አሁን የሚጠራበትን "ኮሚኒቲ ሺልድ" የሚለውን ስም የያዘው እ.አ.አ በ2002 ሲሆን፤ የሊጉን ሻምፒዮን እና የኤፍ ኤ ዋንጫ አሸናፊን የሚያገናኝ ዓመታዊ ውድድር ሆኖ ቀጥሏል።
በመጀመሪያው ዓመት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ኪውፒአርን በማሸነፍ ታሪካዊውን ዋንጫ ወስዷል። ቀያይ ሰይጣናቱ ኮሚኒቲ ሺልድን 21 ጊዜ በማንሳትም ባለክብረወሰን ናቸው።
የፕሪሚየር ሊጉ ዋዜማ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ ውድድር በታላቁ ዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።
የ2026 ኮሚኒቲ ሽልድ በዌምብሌይ ስታዲየም የተያዙ የኮንሰርት መርሐ-ግብሮች በመኖራቸው ምክንያት ከተለመደው ድባብ ወጣ ብሎ በዌልስ ከተማ ካርዲፍ በሚገኘው ፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም ይካሄዳል።
በዚህ ታላቅ መድረክ የ2025/26 የፕሪማየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል ከኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ማንቸስተር ሲቲ ነገ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ይፋለማሉ።
አርሰናል በታሪኩ ለ18ኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ይጫወታል። መድፈኞቹ በ2023 ማንቸስተር ሲቲን በመለያ ምት 4 ለ 1 አሸንፈው ነበር 17ኛ ዋንጫቸውን ከፍ ያደረጉት።
ማንቸስተር ሲቲም በ2024 የምንጊዜም ተቀናቃኙን ማንቸስተር ዩናይትድን በመለያ ምት 7 ለ 6 ድል አድርጎ ሰባተኛውን ዋንጫ ወስዷል።
ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዙፋን የተቆናጠጠው አርሰናል እና ከአስር ዓመታት የፔፕ ጋርዲዮላ አብዮት በኋላ በአዲስ አሰልጣኝ ሊጉን የሚጀምረው ሲቲ፤ የመጀመሪያ ዋንጫቸውን ለማንሳት እና አዲሱን የውድድር ዘመን በድል አጅበው ለመጀመር ይፋለማሉ።
ኮሚኒቲ ሺልድ በመደበኛ የውድድር ደረጃ "የወዳጅነት" ተብሎ ቢመደብም፣ በደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ የሆነ የክብር ቦታ አለው።
ከትኬት እና ከስፖንሰርሺፕ የሚገኘው ገቢ በሙሉ በመላው እንግሊዝ ለሚገኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ለማህበረሰብ የስፖርት ፕሮጀክቶች የሚከፋፈል በመሆኑ፣ የማህበረሰብ አለኝታነትን የሚያጎላ ታላቅ ውድድር ነው።
የክረምት እረፍት አብቅቶ ደጋፊዎችን አንድ ላይ በአንድ አጀንዳ የሚያሰበበው ይህ ጨዋታ፣ የአሰልጣኞች አዲስ ስልትና የአዲስ ፈራሚዎች ዝግጁነት የሚፈተሽበት፣ በቀጣይ ሳምንት ዓርብ ለሚጀመረው እና ለሚቀጥሉት 10 ወራት ለሚዘልቀው የፕሪሚየር ሊግ ማዕበል የመነሻ ደወል ወይም ዋዜማ ሆኖ ያገለግላል።
በአዲስ የሺዋስ
#englishfootball #communityshield #epl #manchestercityfc #arsenal #football #sports #ebcdotstream

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ከ22 ዓመታት የፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ጥማት በኋላ ባለፈው የውድድር ዘመን የሊጉን ክብር ያነሳው እንዲሁም በሻምፒዮንስ ሊጉ የፍጻሜ ተፋላሚ የነበረው አርሰናል፣ ገና የድሉን ሻምፓኝ ጠጥቶ አልጨረሰም። በፓሪስ ሴንት ዠርመን (በፍጻሜው የተነጠቀው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ቁስል፣ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑን ወደ "ተለየ ማዕዘን" እንዲያሸጋግር ገፋፍቶታል። ለዚህ ታላቅ የዝውውር ምዕራፍ ደግሞ የተመረጠው የ28 ዓመቱ ብራዚላዊ እና የኒውካስል ዩናይትዱ አንበል ብሩኖ ጊማሬስ ነው። ክለቡ ይህንን ድንቅ አማካይ በ75 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም የመሀል ሜዳውን በማይታመን ሁኔታ አጠናክሯል።
ብሩኖ ጊማሬስ ኒውካስል ዩናይትድን መልቀቅ ለእርሱ "በህይወቱ ካሳለፋቸው እጅግ ከባድ ውሳኔዎች አንዱ" እንደነበር አልሸሸገም። በስፔን ላ ማንጋ ከሚገኘው የኒውካስል የልምምድ ካምፕ ውስጥ ንብረቶቹን ሰብስቦ ወደ ኤምሬትስ ስታዲየም ሲያመራ ስሜቱ ተረብሾ ነበር። "ኒውካስል ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው፣ ነገር ግን በህይወቴ አዲስ ነገር መሞከር ፈለግሁ። ታሪክ መስራት እና ዋንጫዎችን ማሸነፍ እሻለሁ፣ ለዚህ ደግሞ ትክክለኛው ቦታ ላይ እንደምገኝ ይሰማኛል" በማለት የ4 ዓመት ኮንትራቱን (ተጨማሪ የ12 ወራት አማራጭን ያካተተ) በደስታ ፈርሟል።
ጊማሬስ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ የመጣው በጥር 2022 ቡድኑ በመውረድ ስጋት ውስጥ በነበረበት ፈታኝ ጊዜ ነበር። ሆኖም በኤዲ ሃው ስር ቡድኑን ታድጎ፣ በ2023 እና 2025 የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እንዲያገኝ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ባለፈው የ2025 የካራባዎ ካፕ ፍጻሜ ሊቨርፑልን በማሸነፍ፣ ከሰባት አስርት ዓመታት በኋላ ለኒውካስል ትልቅ የሀገር ውስጥ ዋንጫ ያነሳ የመጀመሪያው አንበል በመሆን በክለቡ ታሪክ ደማቅ አሻራ አሳርፏል።
አርቴታ ጊማሬስን ለምን ፈለገው? መድፈኞቹ ባለፈው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 63 ጨዋታዎችን አድርገዋል። ይህ አድካሚ ጉዞ በተለይ በመሀል ሜዳው ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሮ ነበር። ባለፈው ክረምት 250 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጎም፣ እንደ ክርስቲያን ኖርጋርድ ያሉ ተጫዋቾች (በሊጉ 7 ጨዋታዎች ብቻ ተሰልፎ ወደ ኤቨርተን ሊያመራ የተቃረበው) የአርቴታን እምነት ማግኘት አልቻሉም። በዚህም ምክንያት የማርቲን ዙቢሜንዲ እና የዴክላን ራይስ ጫንቃ እጅግ ከብዶ ነበር። ራይስ ከማንም በላይ ብዙ ደቂቃዎችን በመጫወቱ የቋንጃ (hamstring) ጉዳት እያስተናገደ እንግሊዝን በዓለም ዋንጫው እስከ ግማሽ ፍጻሜ አድርሶ ተመልሷል።
ጊማሬስ ይህንን ክፍተት ለመድፈን ወደር የማይገኝለት ሞተር ነው። በአርሰናል ተጫዋቾች ዘንድ ቀድሞውኑ አቀባበል ተደርጎለታል። የሀገሩ ልጅ የሆነው ገብርኤል እና ዴክላን ራይስ የጽሁፍ መልዕክት ልከውለታል። ከዚህ ቀደም በሜዳ ላይ በተደጋጋሚ ሲጋጩ የነበረው ራይስ፣ "እባክህ ና፣ ከእንግዲህ ጸብ የለም፣ አሁን ጓደኛማቾች ነን" የሚል አዝናኝ መልዕክት ልኮለታል። የጊማሬስ ጠንካራ አካላዊ ብቃት መድፈኞቹን በእጅጉ ማርኮታል፤ ከ2022 ጀምሮ ያመለጠው 16 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ብቻ ነው።
ይህ ኮከብ በሌለበት የኒውካስል የማሸነፍ ምጣኔ ከ50.7% ወደ 12.5% ማሽቆልቆሉ፣ ባለፈው የውድድር ዘመን በ9 ግቦች የክለቡ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆኑ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆኖ 998 ኳሶችን ማቀበል መቻሉ የአርቴታን ትኩረት ስቦታል። በተጨማሪም ተከላካይ ሰንጣቂ ኳሶችን በማቀበል በሊጉ ከሚገኙ ምርጥ 5 ተጫዋቾች አንዱ ነው።
አሁን አርሰናል የህክምና ክፍሉን በአዲስ መልክ አዋቅሮ፤ ራይስን፣ ዙቢሜንዲን፣ አንበሉ ማርቲን ኦዴጋርድን፣ ኤቤሬቺ ኤዜን፣ ሚኬል ሜሪኖን፣ ማይልስ ሉዊስ-ስኬሊን፣ ኢታን ኑዋኔሪን፣ እና አዲሱን ፈራሚ ብሩኖ ጊማሬስን ያጣመረ እጅግ አስፈሪ የመሀል ሜዳ ስብስብ ገንብቷል። በአመራር ብቃቱ "አነቃቂ" ተብሎ የሚሞገሰው ጊማሬስ ኦዴጋርድን በማገዝ የኤምሬትሱን ክለብ ወደ ፈለገው "አዲስ ከፍታ" ያሸጋግረው ይሆን? በብዙዎች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኗል!

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው አርሰናል፣ በአየርላንዷ ዱብሊን ከተማ ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ያልተጠበቀ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ የተጫዋቾቹ ስሜት በእጅጉ መጎዳቱን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገለጹ።
መድፈኞቹ ባልተለመደ ሁኔታ የመከላከያ ክፍላቸው ክፉኛ ተዳክሞ በታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ ሶስት ግቦችን ለማስተናገድ ተገደዋል። ምንም እንኳን ቤቲሶች የኳስ ቁጥጥሩን ለአርሰናል አሳልፈው ቢሰጡም፣ እጅግ አደገኛ በሆኑ ሙከራዎች እና ዒላማቸውን በጠበቁ ኳሶች የአርቴታን ልጆች ብልጫ ወስደውባቸዋል።
ከመጀመሪያው አጋማሽ መጥፎ አቋም በኋላ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ስለነበረው ድባብ የተጠየቁት አርቴታ "በጣም ተበሳጭተዋል፣ ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፉት። በንዴት ጦፈዋል፤ ግን ይሄ ጥሩ ነው። እኛም የምንፈልገው ይሄንን ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
አርቴታ አክለውም "ዋናው ነገር ማሸነፍ ነበር፣ ግን አልቻልንም፤ ስለዚህ በውጤቱ ማዘናችን አይቀርም። ሆኖም መጥፎ ውጤት ማምጣት ለቀጣይ የተሻለ ስራ የድል ረሃብን ስለሚፈጥር አንዳንድ ጊዜ ጠቃሚ ነው" ብለዋል።
የዓለም ዋንጫ ተሳትፎን ተከትሎ ዴክላን ራይስ፣ ኤቤሬቺ ኤዜ፣ ኖኒ ማዱኤኬ እና ቡካዮ ሳካ አሁንም ስብስቡን አልተቀላቀሉም። የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ ሚኬል ሜሪኖ፣ ዴቪድ ራያ እና ማርቲን ዙቢሜንዲም እንዲሁ አልተመለሱም። አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ ግን ከኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ተሳትፎው መልስ ግላዊ ልምምድ ጀምሯል።
ይሁን እንጂ አርሰናል እነዚህ ቁልፍ ተጫዋቾች ባይኖሩትም በቋሚ አሰላለፉ አራት ዓለም አቀፍ ተከላካዮችን፣ እንዲሁም ኢታን ኑዋኔሪ፣ ካይ ሃቨርትዝ፣ አዲሱ ፈራሚ ክሪስቶስ ዞሊስ እና ማክስ ዶውማንን በአማካይ ስፍራ፣ ቪክቶር ጊዮከረስን ደግሞ በአጥቂ መስመር አሰልፎ ነበር።
ባለፈው ሳምንት ጂሮናን 4-1 ባሸነፈበት አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገባው አርሰናል፣ በጨዋታው መባቻ ጊዮከረስ ያገኘውን ግሩም አጋጣሚ የቤቲሱ ግብ ጠባቂ አልቫሮ ቫሌስ በእግሩ መልሶበታል። ሆኖም በ9ኛው ደቂቃ ላይ አርሰናሎች ጠንካራ ከሆኑበት የማዕዘን ምት ቤቲሶች ቀዳሚውን ግብ አግኝተዋል። ተቀያሪው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በፓብሎ ፎርናልስ የተመታውን ኳስ በአግባቡ ባለማንበቡ፣ ሮድሪጎ ሪኬልሜ ያለምንም ከልካይ ኳሷን መረብ ላይ አሳርፏል።
በአማካይ ስፍራ የተሰለፈው ወጣቱ ማይልስ ሉዊስ-ስኬሊ ከሌሎች የተሻለ እንቅስቃሴ ያሳየ ሲሆን፣ ሪካርዶ ካላፊዮሪ ወደ ፊት በሚሄድበት ጊዜ ቦታውን እየሸፈነ ድንቅ ስራ ሰርቷል። የግሪኩ ክንፍ ተጫዋች ዞሊስ የግብ ጠባቂውን ስህተት ተጠቅሞ አቻ የሚያደርግበትን ኳስ ቢያገኝም ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጥቶበታል።
ከ20 ዓመታት በኋላ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ የተመለሰው ሪያል ቤቲስ፣ በአርሰናል ስህተቶች ላይ በሚገባ ተጫውቷል። በ26ኛው ደቂቃ ኬፓ የሰራውን ደካማ የኳስ አወጣጥ ስህተት ተጠቅሞ ኔልሰን ዴኦሳ ከ25 ያርድ ርቀት ላይ አስደናቂ ግብ አስቆጥሯል። በ32ኛው ደቂቃ ዞሊስ ያሻገረውን ኳስ ፒዬሮ ሂንካፒ በጭንቅላቱ በመግጨት ለአርሰናል አንድ ግብ ቢመልስም፣ በ43ኛው ደቂቃ ላይ ካይ ሃቨርትዝ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ ፓብሎ ፎርናልስ የቤቲስን ሶስተኛ ግብ ከመረብ አዋህዷል።
በሁለተኛው አጋማሽ አርቴታ ጋብሪኤል ማርቲኔሊን እና ጋብሪኤል ማጋልሃስን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾችን ቀይረው አስገብተዋል። የ16 ዓመቱ ተከላካይ ማርሊ ሳልሞን እና የ19 ዓመቱ ሉዊ ኮፕሊም የመሰለፍ እድል ቢያገኙም፣ ኮፕሊ ገብቶ በሰባት ደቂቃ ውስጥ በደረሰበት የጉልበት ጉዳት ለመውጣት ተገዷል። በቅያሪዎች ብዛት የጨዋታው ምት የቀዘቀዘ ሲሆን፣ ጋብሪኤል ጄሱስ የተሻለ ሙከራ ቢያደርግም፣ አርቴታ በሜዳው ዳርቻ በብስጭት ሲንጎራደዱ ታይተዋል፤ መድፈኞቹም ያጡትን ክፍተት ማጥበብ ሳይችሉ ጨዋታው ተጠናቋል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ክሪስቶስ ቶሊስ ለመድፈኞቹ ባደረገው የመጀመሪያ የቅድመ-ውድድር ዘመን ጨዋታ ግብ በማስቆጠር፣ የአርሰናል ደጋፊዎች በቀጣዩ የውድድር ዘመን ከእርሱ ምን ሊጠብቁ እንደሚችሉ አስደሳች ፍንጭ ሰጥቷል። አርሰናል የስፔኑን ክለብ ጅሮናን 4 ለ 1 ባሸነፈበት በዚህ የመክፈቻ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ፣ አዲሱ ፈራሚ ድንቅ እንቅስቃሴ አሳይቷል። ወደ ቤሺክታሽ ያቀናውን ሊያንድሮ ትሮሳርድን ለመተካት ከቤልጂየሙ ክለብ ክለብ ብሩጅ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ወደ ሰሜን ለንደን ያመራው የ24 ዓመቱ ግሪካዊው ኢንተርናሽናል፣ በ30ኛው ደቂቃ ላይ አርናው ማርቲኔዝን በሚያምር ሁኔታ በማለፍ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ተከላካይ ታክኮ መረብ ላይ አርፏል።
ከዚህች ግብ 14 ደቂቃዎች አስቀድሞ የሚኬል አርቴታውን ስብስብ ቀዳሚ ያደረገችውን የመጀመሪያ ግብ ያስቆጠረው ጀርመናዊው አጥቂ ካይ ሃቨርትዝ ነበር። የ16 ዓመቱ ታዳጊ ማክስ ዶውማን ተከላካዮችን ሰንጥቆ ያቀበለውን ማራኪ ኳስ፣ ሃቨርትዝ ከጅሮናው ግብ ጠባቂ ፓውሎ ጋዛኒጋ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ በእርጋታ ወደ ግብነት ቀይሮታል።
ከእረፍት መልስ በ49ኛው ደቂቃ ላይ የጅሮናው ማርቲኔዝ ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ ከፍ ብሎ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር የግብ ልዩነቱን ማጥበብ ቢችልም፣ ደስታቸው ግን ከሶስት ደቂቃዎች በላይ አልዘለቀም። ድንቁ ታዳጊ ዶውማን ወዲያውኑ የአርሰናልን የሁለት ግብ መሪነት መልሶ አረጋግጧል። የጎል ዝናቡ በዚህ ያላበቃ ሲሆን፣ ገብርኤል ጄሱስ በአምስት ደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ሌላ ግብ ከመረብ በማዋሃድ መድፈኞቹን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸናፊ ማድረግ ችሏል።
አርቴታ በስፔኑ ግጥሚያ ጠንካራ ቋሚ አሰላለፍ ይዘው ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን፣ ከዓለም ዋንጫ ተሳትፎ የተመለሱት ቪክቶር ጂዮክሬስ፣ ሃቨርትዝ እና ፒዬሮ ሂንካፒ እያንዳንዳቸው ለ30 ደቂቃዎች ያህል በሜዳ ላይ አሳልፈዋል። አርሰናል ሁለተኛውን የቅድመ-ውድድር ዘመን የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ደብሊን የሚያመራ ሲሆን፣ በቀጣዩ ኦገስት 5 በአቪቫ ስታዲየም ከሪያል ቤቲስ ጋር ይፋለማል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሪያል ማድሪድ ቤት ድባቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቷል። ክለቡ የዓለም እግር ኳስ ፈርጥ እና የቡድኑ ዋልታ በሆነው ቪኒሽየስ ዙሪያ እያደረገ ያለው የኮንትራት ድርድር አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ፣ የ26 ዓመቱ ኮከብ በስፔን ዋና ከተማ ስላለው የረጅም ጊዜ ቆይታው ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ የወደቀበት ወቅት ላይ ይገኛል። የኮንትራት ማራዘሚያው ሒደት አለመሳካቱ፣ የቤርናባው የበላይ ጠባቂዎች ሁኔታውን እያስተናገዱበት ባለው መንገድ ላይ ጠንካራ ትችቶች እንዲሰነዘሩባቸው በሩን ወለል አድርጎ ከፍቷል።
ይህን ጠንካራ ትችት የሰነዘረው የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና ቫለንሲያ ግብ ጠባቂ ሳንቲያጎ ካኒዛሬስ ነው። በካዴና ኮፔ የ'ትዬምፖ ዴ ሁዌጎ' ፕሮግራም ላይ በሰጠው አስተያየት፣ ሎስ ብላንኮዎቹ በቪኒሽየስ ዙሪያ ያላቸውን የትርክት ቁጥጥር እንዳጡ በግልጽ ተናግሯል። ቪኒሽየስ አሁን ባለው ኮንትራት መሰረት በሚቀጥለው ክረምት በነጻ ሊለቅ ስለሚችል፣ ክለቡ የፋይናንስ እና የስፖርታዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ቀድሞ ጠንካራ አቋም መውሰድ ነበረበት ብሏል።
ካኒዛሬስ ቁጣውን ሲገልጽ፣ "ሪያል ማድሪድ ለሁሉም ነገር ይዘገያል። ተጫዋቹ የፈረመው ስምምነት የለውም የሚባለው እውነት ከሆነ፣ ማድሪድ አሁኑኑ እሱን የመሸጥ ግዴታ አለበት። ተጫዋቹን ኮንትራቱን ጨርሶ እንዲወጣ በማድረግ ከመቶ ሚሊዮን ዩሮ በላይ ማጣት አይቻልም፤ ግን ይህ የሚሆን ይመስለኛል። ይህ ይቅር የማይባል የአመራር ስህተት ነው" በማለት የክለቡን ቦርድ ክፉኛ ወቅሷል።
ማድሪዶች በዚህ የኮንትራት ውዝግብ ውስጥ እያሉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሀያል ክለብ አርሰናል ይህንን ውጥንቅጥ ለመጠቀም አድፍጦ እየጠበቀ ይገኛል። መድፈኞቹ ለብራዚላዊው ኮከብ እውነተኛ ፈላጊ ሆነው ብቅ ያሉ ሲሆን፣ የሚኬል አርቴታው ስብስብ ይህንን ፈጣን የክንፍ ተጫዋች ወደ ለንደን ለማምጣት ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑን ከእንግሊዝ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቪኒሽየስ አሁን ባለው ክለቡ ተገቢው ክብር እንዳልተሰጠው ከተሰማው፣ የፕሪሚየር ሊጉ ማራኪነት እና ሊቀርብለት የሚችለው ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ ከስፔን ሊያባብለው የሚችልበት አቅም አለው። ይሁን እንጂ፣ ማድሪዶች አሁንም ቢሆን ቪኒሽየስን በአዲስ ኮንትራት እንደሚያስሩት ሙሉ በሙሉ በራስ መተማመን እንዳላቸው ተዘግቧል።
ይህንን የተወሳሰበ የዝውውር ሒደት ይበልጥ እንዲወሳሰብ የሚያደርገው ደግሞ ክለቡ አዲስ ተሰጥኦን ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት፣ በተለይም የያን ዲዮማንዴ እምቅ ዝውውር ነው። አንዳንድ የስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት፣ ወጣቱን ኮከብ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ማድሪድ ከቪኒሽየስ ውጪ ላለው ህይወት ቀድሞ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳይ የቅድመ-ጥንቃቄ እርምጃ ነው። ምንም እንኳን ይህ ግምት ቢኖርም፣ አዲሱ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ ብራዚላዊውን ኢንተርናሽናል የአዲሱ ፕሮጀክታቸው ቁልፍ አካል አድርገው ለማቆየት ቆርጠው መነሳታቸው ተነግሯል።

Comments