Logo
SeledaPost
216ኛው የለንደን ደርቢ አርሰናል ከ ቼልሲ

ሁለቱ የባስክ ግዛት ተወላጆች እና አብሮ አደጎቹ ሚኬል አርቴታ እና ዣቢ አሎንስ በዓለም ትልቁ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ትልልቅ ክለቦችን ይዘው ተፋጠዋል።

እግር ኳስን በተወለዱበት አካባቢ በሚገኝው የአንቲጎኩ አካዳሚ የጀመሩት እና ለ6 ዓመት በዚሁ አካዳሚ አብረው የተጫውቱት አርቴታ እና አሎንሶ ለሪያል ሶሴዳድ ዋናው ቡድንም ተጫውተው አሳልፈዋል።

በባየር ሊቨርኩሰን ድንቅ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ በማድሪድ የተወሰን ጊዜ የቆየው ዣቢ አሎንሶ በቼልሲ ራሱን ለትልቁ ፈተና አዘጋጅቷል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ያሸነፈው አሎንሶ፤ የመጀመሪያ ትልቁን ፈተና ዛሬ ይጋፈጣል። ምሽት 12፡30 በኤምሬትስ ከሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ አርሰናልም የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ያሸነፈ ሲሆን በአሸናፊነቱ ለመቀጥል በለንደን ደርቢ ጠንካራ የፊት መስመር ካለው ቼልሲ ይገናኛል።

በኤምሬስት የሚደረገው ጨዋታ 7 ግቦችን ያስቆጠረው የቼልሲ የፊት መስመር ምንም ግብ ካልተቆጠረበት የአርሰናል ተከላካይ የሚያደርጉት ትንቅንቅ በመሆኑ ጨዋታውን እንዲጠበቅ የሚያደርግው ሲሆን በሌላ በኩል ሁለቱ ስፔናዊያን ታክቲሺያን ጨዋታውን እንዴትባለ መልኩ ይወጡታል የሚለው የሚጠበቅ ነው።

አርሰናል ከቼልሲ በተገናኝባቸው ያልፉት 9 ጨዋታዎች በአንዱም ያልተሸነፍ ሲሆን 6ቱን አሸንፏል።

በጨዋታው በመድፈኞቹ በኩል ዩሪየን እና ዊሊያም ሳሊባ አሁንም ከጉዳቱ ያልተመለሱ ተጨዋቾች ሲሆኑ፤ ኤዝሪ ኮንሳ በመድፍኞቹ ማልያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቋሚነት ሊጀምር ይችላል ተብሏል።

ሞይሰስ ካይሴዶ የመሰለፉ ነገር ያልተረጋገጥ ሲሆን ጆርዳን ሄንደርሰን እና ፓሊስትራ አሁንም በጉዳት ከስብስቡ ውጪ ናቸው።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.