2 months ago
ኮሚኒቲ ሺልድ - የእንግሊዝ እግር ኳስ አዲሱን የውድድር ዘመን መጀመር የሚያበስር ዋዜማ
***********************
የክረምቱ የእግር ኳስ ዝምታ ተጠናቆ የፕሪማየር ሊጉ ትኩሳት ከመጀመሩ በፊት፣ የእንግሊዝ እግር ኳስ አዲሱን የውድድር ዘመን በይፋ የሚያበስርበት ታሪካዊው የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ነገ ይደረጋል።
ይህ ጨዋታ ለደጋፊዎች ተራ የዋንጫ ፍልሚያ ሳይሆን፣ “እግር ኳስ በይፋ ተመልሷል!” የሚል ታላቅ የዋዜማ በዓል ነው።
የ118 ዓመታት ታሪክ ያለው ኮሚኒቲ ሺልድ ፕሮፌሽናል እና አማተር ክለቦችን በማገናኘት ለበጎ አድራጎት ተግባራት የሚውል ገቢ ለመሰብሰብ በማሰብ ነበር የተጀመረው።
ኋላ ላይ፣ የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (FA) ሙሉ በሙሉ ተረክቦት የሊግ አሸናፊዎችን ከሳውዘርን ሊግ አሸናፊዎች ጋር ማፋለም ጀመረ።
እ.አ.አ. ከ1921 ጀምሮ ደግሞ የአንደኛው ሊግ አሸናፊ ከኤፍ ኤ ካፕ ባለድል ጋር የሚገናኝበትን ዘመናዊ ቅርፅ ያዘ።
ውድድሩ አሁን የሚጠራበትን "ኮሚኒቲ ሺልድ" የሚለውን ስም የያዘው እ.አ.አ በ2002 ሲሆን፤ የሊጉን ሻምፒዮን እና የኤፍ ኤ ዋንጫ አሸናፊን የሚያገናኝ ዓመታዊ ውድድር ሆኖ ቀጥሏል።
በመጀመሪያው ዓመት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ኪውፒአርን በማሸነፍ ታሪካዊውን ዋንጫ ወስዷል። ቀያይ ሰይጣናቱ ኮሚኒቲ ሺልድን 21 ጊዜ በማንሳትም ባለክብረወሰን ናቸው።
የፕሪሚየር ሊጉ ዋዜማ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ ውድድር በታላቁ ዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።
የ2026 ኮሚኒቲ ሽልድ በዌምብሌይ ስታዲየም የተያዙ የኮንሰርት መርሐ-ግብሮች በመኖራቸው ምክንያት ከተለመደው ድባብ ወጣ ብሎ በዌልስ ከተማ ካርዲፍ በሚገኘው ፕሪንሲፓሊቲ ስታዲየም ይካሄዳል።
በዚህ ታላቅ መድረክ የ2025/26 የፕሪማየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል ከኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ማንቸስተር ሲቲ ነገ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ይፋለማሉ።
አርሰናል በታሪኩ ለ18ኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ይጫወታል። መድፈኞቹ በ2023 ማንቸስተር ሲቲን በመለያ ምት 4 ለ 1 አሸንፈው ነበር 17ኛ ዋንጫቸውን ከፍ ያደረጉት።
ማንቸስተር ሲቲም በ2024 የምንጊዜም ተቀናቃኙን ማንቸስተር ዩናይትድን በመለያ ምት 7 ለ 6 ድል አድርጎ ሰባተኛውን ዋንጫ ወስዷል።
ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዙፋን የተቆናጠጠው አርሰናል እና ከአስር ዓመታት የፔፕ ጋርዲዮላ አብዮት በኋላ በአዲስ አሰልጣኝ ሊጉን የሚጀምረው ሲቲ፤ የመጀመሪያ ዋንጫቸውን ለማንሳት እና አዲሱን የውድድር ዘመን በድል አጅበው ለመጀመር ይፋለማሉ።
ኮሚኒቲ ሺልድ በመደበኛ የውድድር ደረጃ "የወዳጅነት" ተብሎ ቢመደብም፣ በደጋፊዎች ዘንድ ግን ልዩ የሆነ የክብር ቦታ አለው።
ከትኬት እና ከስፖንሰርሺፕ የሚገኘው ገቢ በሙሉ በመላው እንግሊዝ ለሚገኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ለማህበረሰብ የስፖርት ፕሮጀክቶች የሚከፋፈል በመሆኑ፣ የማህበረሰብ አለኝታነትን የሚያጎላ ታላቅ ውድድር ነው።
የክረምት እረፍት አብቅቶ ደጋፊዎችን አንድ ላይ በአንድ አጀንዳ የሚያሰበበው ይህ ጨዋታ፣ የአሰልጣኞች አዲስ ስልትና የአዲስ ፈራሚዎች ዝግጁነት የሚፈተሽበት፣ በቀጣይ ሳምንት ዓርብ ለሚጀመረው እና ለሚቀጥሉት 10 ወራት ለሚዘልቀው የፕሪሚየር ሊግ ማዕበል የመነሻ ደወል ወይም ዋዜማ ሆኖ ያገለግላል።
በአዲስ የሺዋስ
#englishfootball #communityshield #epl #manchestercityfc #arsenal #football #sports #ebcdotstream

Comments