ጋብሬል ማርቲኔሊ፣ በአርሰናል ቤት የተጻፈ የትጋት ታሪክ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሰናል የቅርብ ዓመታት የዳግም ግንባታ ጉዞ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል ጋብሬል ማርቲኔሊ አንዱ ነው። ወጣቱ ብራዚላዊ በፍጥነቱ፣ በጉልበቱ፣ ተከላካዮችን በአንድ ለአንድ ለመጋፈጥ ባለው ድፍረቱ እና ጎል ለማስቆጠር ባለው ክህሎት የመድፈኞቹ ደጋፊዎችን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
ጋብሬል ቴዎዶሮ ማርቲኔሊ ሲልቫ በፈረንጆቹ 2001 በብራዚል ሳኦ ፖሎ ግዛት ጉዋሩልዮስ ተወለደ።
የእግር ኳስ ህይወቱን በኮረንቲያንስ አካዳሚ በመጀመር በኋላም በኢቱዋኖ ቀጠለ። በኢቱዋኖ በዋናው ቡድን ዕድል ካገኘ በኋላ የብራዚላዊው ወጣት ችሎታ በአውሮፓ የተለያዩ ክለቦች ዓይን ውስጥ ገባ።
በመጨረሻም እ.ኤ.አ በ2019 አርሰናል፣ ተስፈኛውን ታዳጊ ተጫዋች ወደ ሰሜን ለንደን አመጣው። ማርቲኔሊ በአርሰናል ቤት የተሰጠውን ዕድል በፍጥነት በመጠቀም ለቡድኑ የሚያስፈልገው የግብ ስጋት ሆነ።
ማርቲኔሊ ወደ አርሰናል ሲመጣ ብዙዎች እንደ ተስፈኛ ወጣት ተጫዋች ብቻ ይመለከቱት ነበር። እሱ ግን የሰዎችን ግምት በፍጥነት ለወጠው። ፍጥነቱን በመጠቀም በግራ ክንፍ ተከላካዮችን መጫን፣ ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ መግባት እና ጎል ማስቆጠር የአጨዋወቱ ዋነኛ መለያዎች ሆኑ።
በተለይም በ2019/20 የውድድር ዘመን ያሳየው ብቃት የአርሰናል ደጋፊዎች በወጣቱ ላይ ትልቅ ተስፋ እንዲጥሉ አደረገ። እሱ በሜዳ ላይ የሚያሳየው ትጋትና የማይታክት ሩጫ ለቡድኑ አጨዋወት መለያ እየሆነ መጣ።
ለማርቲኔሊ የአርሰናል ቆይታ እጅግ የሚታወሰው የ2022/23 የውድድር ዘመን ነው። በዚያ ወቅት ተጫዋቹ በፕሪሚየር ሊጉ 36 ጨዋታዎች በመሳተፍ 15 ጎሎችን አስቆጠረ፤ በተጨማሪም 5 የግብ እድሎችን ፈጥሯል፡፡
ይህ የግል ብቃቱ ብቻ ሳይሆን አርሰናል እስከ መጨራሻው ሰዓት የሊጉ አሸናፊ ለመሆን ከፔፕ ጓርዲዮላው ማንቼስተር ሲቲ ጋር የተፋለመበት ወቅት ነበር። ማርቲኔሊ፣ ቡካዮ ሳካ እና ሌሎች ወጣት ተጫዋቾች የአርሰናልን የወደፊት ቡድን ምስል እንዲያሳይ አጨዋወት አሳይተዋል።
ማርቲኔሊን ከሌሎች የክንፍ ተጫዋቾች የሚለየው ነገር በኳስ ላይ ያለው ችሎታ ብቻ አይደለም። ኳስ ሲበላሽበት ወዲያውኑ መልሶ ለመንጠቅ የሚያደርገው ጥረት፣ ተከላካይን በፍጥነት ለመጫን ያለው ፍላጎት እና ከኳስ ውጭ የሚያደርጋቸው ሩጫዎቹ ናቸው።
የግራ ክንፍ ቦታውን በመያዝ ወደ ውስጥ በመግባት በቀኝ እግሩ ጎል ለመሞከር የሚያደርገው እንቅስቃሴም የተለመደ ነበር። በአርሰናል ቤት ቆይታው 41 ግችንና 24 ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበሉ የሚያሳየውም በቡድኑ የማጥቃት ሥርዓት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ተፅዕኖ ነው።
በመጨረሻዎቹ የአርሰናል ቆይታው የማርቲኔሊ የመጫወቻ ጊዜ እንደ ቀድሞው የተረጋጋ አልነበረም። የቡድኑ የማጥቃት አማራጮች መጨመር፣ የተጫዋቾች ውድድር እና ራሱ የማርቲኔሊከቡድኑ እኩል ማደግ አለመቻል በቋሚ 11 ውስጥ የመሰለፍ እድሉን አመነመነው፡፡
በ2025/26 የውድድር ዓመት 30 ጨዋታዎች ቢያደርግም በ11 ብቻ ነው በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ለመግባት የቻለው፡፡ በዚህም አንድ ግብና 4 የግብ እድሎችን ብቻ አስመዝግቧል።
በአጠቃላይ በአርሰናል ቆይታው 191 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በማድረግ 41 ግቦችና 24 የግብ እድሎችን በማስመዝገብ በመድፈኞቹ ቤት የራሱን ታሪክ አኑሯል፡፡
ብራዚላዊው አቦ ሸማኔ በተዘጋው የዝውውር መስኮት ወደ ሳዑዲው አል ሂላል እግር ኳስ ቡድን ተዛውሯል፡፡ ከአርሰናል መለየቱ ለብዙ የመድፈኞቹ ደጋፊዎች ቀላል የሆነ ዜና አልነበረም። በተለይም በቡድኑ ውስጥ ካሳለፈው ረጅም ጊዜ እና ከደጋፊዎች ጋር ከፈጠረው ትስስር አንፃር መሰናበቱ የአንድ ዘመን የታሪክ ምዕራፍ መዝጊያ ይመስላል።
ከአርሰናል ጋር ያሳለፋቸው ዓመታት ሲደመሩ ማርቲኔሊ በክለቡ ታሪክ ውስጥ የራሱን ምዕራፍ ጽፏል። ወደ ክለቡ የመጣው እንደ ወጣት ተስፈኛ ነበር፤ የወጣው ግን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆን ነው፡፡
ማርቲኔሊም ከአርሰናል የሚወጣው በፍጥነቱ ተከላካዮችን ሲያስጨንቅ፣ ግብ ሲያስቆጥር፣ በሜዳ ላይ ሲሮጥ እና የመድፈኞቹን ማልያ በኩራት ሲለብስ የታዩትን ትዝታዎች ትቶ ነው።
ከለንደን ወደ ሳዑዲ የተደረገው ጉዞ ለማርቲኔሊ አዲስ ምዕራፍ ቢሆንም፣ በአርሰናል የተጻፈው ታሪክ ሁሌም የእግር ኳስ ሕይወቱ አንድ ትልቅ ክፍል ሆኖ ይዘልቃል።
በአቤል ነዋይ

1 month ago