አርሰናል ጥያቄ አለው
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሪው አርሰናል በሰንደርላንዱ ጨዋታ የተሰጠበትን አወዛጋቢ ፍፁም ቅጣት ምት ተከትሎ ከሊጉ የዳኞች ማህበር ጋር ወደ ውዝግብ ገብቷል።
የክሉቡ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት የዳኛውን ውሳኔ “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ በፅኑ የኮነኑ ሲሆን አሁን ላይ መድፈኞቹ የዳኞች ማህበር ሃላፊውን ሀዋርድ ዌብ አግኝተው ስለ ውሳኔው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።
በጨዋታው ላይ የተሰጠውን ያንን ፍፁም ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ በጥሩ ብቃት ያከሸፈው ቢሆንም የውሳኔው ትክክለኛነት ግን ክለቡን እስከ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር አሳስቧል።
አርሰናል የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ለመቀጠል በሚያደርገው ጉዞ ላይ መሰል የዳኝነት ውሳኔዎች ተፅዕኖ እንዳያሳድሩበት ያለው ስጋት አሁንም በስፖርቱ ዓለም ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቀጥሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ts

23 days ago