Logo
Getu Temesgen
አርሰናል አዲሱን ጆርጂያዊ የ17 ዓመት ኮከብ አስፈረመ
#ethiopia | ​የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የ17 ዓመቱን ጆርጂያዊ አንድሪያ ባርቲሽቪሊን ማስፈረሙን አረጋግጧል።

ወጣቱ ተጫዋች ትናንት የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቀ በኋላ በሎንዶን ኮልኒ የስልጠና ማዕከል በመገኘት ኮንትራቱን በይፋ ፈርሟል።

​በአውሮፓ እግር ኳስ ቀጣዩ ትልቅ ኮከብ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ወጣት ከሰኔ 2027 ጀምሮ በይፋ የመድፈኞቹን ማሊያ ለብሶ መጫወት የሚጀምር ይሆናል።

አርሰናል የወደፊት የቡድኑን የፊት መስመር እና አማካኝ ክፍል ለማጠናከር ያደረገው ይህ ዝውውር ክለቡ ለወጣት ሃያላን የሚሰጠውን ትልቅ ትኩረት እና ረጅም የእቅድ የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.