Logo
FBC
አርሰናል ሰንደርላንድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ሰንደርላንድን 2 ለ ዐ አሸንፏል።

በስታዲየም ኦፍ ላይት በተደረገው ጨዋታ የመድፈኞቹን ግቦች ብሩኖ ጊማሬሽ እና ቡካዮ ሳካ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል።

ሰንደርላንድ ጨዋታውን መምራት የሚችልበትን ፍጹም ቅጣት ምት ኢንዞ ሊ ፊ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ሞዛምቢካዊው የሰንደርላንድ ተከላካይ ሬኒልዶ ማንዳቫ በጨዋታው መገባደጃ ላይ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.