Logo
Getu Temesgen
ከተስፋ ወደ ክብር፤ አርቴታ ያልጨረሰው ጉዞ

✍️ በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | የሰሜን ለንደን ቀይ ለባሾቹ አርሰናል በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ከታላላቅና ስኬታማ ክለቦች ተርታ ቢመደቡም፣ በአውሮፓ ትልቁ መድረክ ያላቸው ሕልም እስካሁን እውን አልሆነም።

“ባለትልቅ ጆሮው” በሚል ቅጽል የሚጠራውን የUEFA ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የማንሳት ሕልማቸው በ2006 በፍራንክ ራይካርድ ባርሴሎና ፊት ተገትቶ ቀርቷል። በቅርቡም በፓሪስ ሴን-ዠርመን ፊት የደረሰባቸው ሽንፈት ያንን የቆየ ቁጭት ዳግም ቀስቅሶታል።

ከክለቡ ታሪካዊ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ስንብት በኋላ የውጤት መንገዱን ያጣውን አርሰናል የተረከበው የፔፕ ጋርዲዮላ ደቀ መዝሙር ሚኬል አርቴታ፣ መድፈኞቹን በትዕግሥት እና በተከታታይ ሥራ ወደ ከፍታቸው መልሷል።

አርቴታ የረጅም ዓመታትን የዋንጫ ጥማት በማስታገስ ክለቡን እንደገና ከእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች ጋር በአንድ ደረጃ አስቀምጧል። አሁን ግን የቀረው አንድ ትልቅ ፈተና ብቻ ነው—የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ኢሚሬትስ ማምጣት።

በአለት የጠነከረ የተከላካይ ክፍል፣ በአውሮፓ ምርጥ ከሚባሉ የአማካይ ስብስቦች አንዱ እና በዝውውር መስኮቱ የተጨመሩ አዳዲስ ኃይሎችን ይዘው፣ መድፈኞቹ ለታላቅ የአውሮፓ ዘመቻ ዝግጁ ናቸው።

ያለፈው የቁጭት ስሜት ገና አልበረደም፤ የዘንድሮው ጉዞ ግን የታሪክ ጉዞ ሊሆን ይችላል?

ከቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊነት እጩዎች ቀዳሚዎቹ መካከል የሚጠቀሱት መድፈኞቹ፣ የአውሮፓ ዘመቻቸውን ከኔፕልስ ይጀምራሉ።

ጥያቄው አንድ ነው...

በመጨረሻ ባለትልቅ ጆሮውን ዋንጫ ወደ ኢሚሬትስ ያመጣሉ?

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.