Logo
Getu Temesgen
"ስምምነቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ይፈፀማል" - ሻሪፍ

እንደተባለው የሚሆን ከሆነ፣ የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር በአንድ ቀን ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተገልጿል።

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሻሪፍ በገለጻቸው፣ "የኤሌክትሮኒክ ፊርማ በሰዓታት ውስጥ ይካሄዳል" ብለዋል።

ሻፊፍ በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት "ስምምነቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ይፈፀማል" ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

"ዩናይትድስቴትስ እና ኢራን በስምምነቱ የተካተቱ ሀሳቦችን ተቀብለዋል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ስምምነቱ እንዲሳካ ሁለቱም ሀገራት ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

ሻሪፍ በትናንትናው እለት በሰጡት አስተያየት ዋሽንግተን እና ቴህራን በፅሁፍ ደረጃ መስማማታቸውን ተናግረዋል ያለው ቲቃህ ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #spuntik # #cnn #aljazeera

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.