የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ እና የሶማሊያ መሪዎች በቀጣናዊ ሰላምና በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ተጽእኖዎች ዙሪያ መከሩ
#ethiopia | 🇪🇹🇩🇯🇸🇴 የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጊሌ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ረቡዕ ምሽት በጅቡቲ የሀራሞስ መኖሪያ ቤት የሦስትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት፣ በኢኮኖሚ ውህደት ሂደት፣ ለሦስቱም ሀገራት የጋራ ፍላጎት ባላቸው ጉዳዮች እና በአካባቢው ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ትኩረት ተሰጥቶበታል።
በተጨማሪም፣ ውይይቱ በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ስላለው ግጭት እና በክልሉ ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖና ጉዳት ላይ አተኩሯል ሲሉ የጁቡቲ ፕሬዝዳንት ጊሌ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።
👉 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን፣ የብልጽና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ረድዋን ሁሴን ሌሎች ባለሥልጣናት ተካተውበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#spuntik #getutemesgen #getu #ጌጡ

5 months ago