ኢትዮጵያ በሩሲያ የቪዛ ነፃ የጉዞ ሥርዓት ድርድር ውስጥ ተካታ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ
#ethiopia | የሩሲያ መንግሥት ከአፍሪካ አገራት ጋር ያለውን የዲፕሎማሲ፣ የንግድ እና የዜጎች የጉዞ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳለጥ በማሰብ፣ ከበርካታ የአህጉሪቱ አገራት ጋር ከቪዛ ነፃ የጉዞ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ውይይቶችን እያደረገ መሆኑን የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አሌክሲ ክሊሞቭ ለስፑትኒክ የዜና ወኪል እንደገለጹት፤ ሩሲያ ከቪዛ ነፃ የጉዞ ዕድልን ለማስፋፋት ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ጋር በድርድር ላይ ትገኛለች። ይሁን እንጂ ዳይሬክተሩ አክለውም፣ እስካሁን ድረስ በይፋ የተጠናቀቀ እና ፊርማ ያረፈበት የስምምነት ሰነድ አለመኖሩን አብራርተዋል።
ይህ የሩሲያ እንቅስቃሴ ሞስኮ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትስስር ለማሳደግ የምታደርገው ሰፋ ያለ ስትራቴጂ አካል መሆኑን የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ታዛቢዎች ይገልጻሉ።
በአሁኑ ወቅት ለሩሲያ ዜጎች ከቪዛ ነፃ የሆኑ የአፍሪካ አገራት አሁን ባለው መረጃ መሠረት 11 የአፍሪካ አገራት ለሩሲያ ዜጎች ከቪዛ ነፃ የመጓዝ ዕድልን ፈቅደዋል። እነዚህም አገራት የሚከተሉት ናቸው፡-
🇲🇦 ሞሮኮ
🇹🇳 ቱኒዚያ
🇳🇦 ናሚቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇧🇼 ቦትስዋና
🇦🇴 አንጎላ
🇲🇺 ሞሪሸስ
🇸🇨 ሲሼልስ
🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ
🇸🇹 ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
🇸🇿 ኤስዋቲኒ
Credit : spuntik
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago