Logo
Getu Temesgen
አንድ የቻይና ባንክ ለቢሾፍቱው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል መግባቱ ተገለፀ
#ethiopia | 🛬 ለሜጋ ፕሮጀክቱ ግንባታ የግማሽ ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅርቦት መገኘቱን ያረጋገጡት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የባንኩን ስም በይፋ ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው በሞሮኮ፤ ራባት እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ጎን ለጎን ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ ቁርጠኝነት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

"በሁሉም የዓለም ክፍሎች ማለትም በመካከለኛው ምስራቅ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ካሉ ከበርካታ የፋይናንስ ተቋማት ጋር እየተነጋገርን ነው፤ ከአበዳሪ ተቋማት እያገኘን ያለነው ምላሽም አዎንታዊ ነው" ሲሉ አስረድተዋል፡፡

🛫 በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባው አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ የመሬት ግዢን፣ መልሶ ማቋቋምን እና የፋይናንስ ወጪዎችን ጨምሮ 12.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስወጣ ተገምቷል።

💼 ከአጠቃላይ ወጪው ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ያህሉ ደግሞ በግሉ ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦት ይሸፈናል ተብሎ ይጠበቃል።
#spuntik

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.