Logo
Getu Temesgen
🇪🇹 ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
#ethiopia | ሀገሪቱ ጉባዔውን ለማስተናገድ ልምዱም አቅሙም እንዳላት የገለፁት በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ፤ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

🌱 የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያግዙ ተግባራዊ ሥራዎችን ያከናወነችው ኢትዮጵያ፤ ጉባኤውን ለማስተናገድ ፍላጎቱም ዝግጁነቱም አላት ብለዋል፡፡

አምባሳደር ልዑልሰገድ ለማሳያነትም፦

✅ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳካበትች፣
✅ የላቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዳላት፣
✅ ከ160 በላይ ለሆኑ የዲፕሎማሲ ተቋማት ጽህፈት ቤቶች መቀመጫ እንደሆነች አንስተዋል፡፡

🇧🇷 አምባሳደሩ ጥያቄውን ያቀረቡት በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው 30ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ነው፡፡
#spuntik

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.