2 months ago
ዳሸን ባንክ አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ የቴክኖሎጂ አድማሱን በማስፋት እስከ 6 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኝ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድርን ጨምሮ አራት አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው ደመቅ ያለ ስነ-ሥርዓት ላይ በይፋ አስጀምሯል።
ባንኩ ያስጀመራቸው እነዚህ አገልግሎቶች የደንበኞችን የባንክ አጠቃቀም ዘመናዊና ምቹ ለማድረግ የታለሙ ሲሆኑ፣ በተለይም የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ሱፐር አፕ የሚሰሩት የቲክቶክ ቪዲዮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝና በደጋፊዎች ድምፅ ሲታጀብ ቀዳሚ ለሚወጡት የ3 ሚሊዮን፣ የ2 ሚሊዮን እና የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማቶችን በቅደም ተከተል የሚያበረክት ይሆናል።
ከሽልማቱ ጎን ለጎን ባንኩ የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም ደንበኞች ባሉበት ሆነው በስልካቸው ብቻ የባንክ ሒሳብ እንዲከፍቱ የሚያስችለውን የዲጂታል ኦን-ቦርዲንግ አገልግሎት አስተዋውቋል፤ ይህም በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ አሰራር ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚህ በተጨማሪ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ለሌሎች በማስተዋወቅ የማበረታቻ ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችለው የዳሸን ስታር ሪፈራል ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ሌላው በዕለቱ ይፋ የተደረገው ትልቅ አገልግሎት ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የቀረበው የዳሸን ቨርቹዋል ካርድ ሲሆን፣ ይህ አገልግሎት ደንበኞች እንደ አማዞን፣ አሊባባ እና ኔትፍሊክስ ባሉ ዓለም አቀፍ የንግድ ድረ-ገጾች ላይ ክፍያዎችን በቀላሉ እንዲፈፅሙና ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን ሐዋላ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራውና ከ250 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ያስተናገደው የዳሸን ሱፐር አፕ፣ ከነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች በተጨማሪ እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው የዕድል ጨዋታ በማቅረብ የደንበኞቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#dashenbank #dashensuperapp #digitalbanking #ethiopianbanking #tiktokchallenge #virtualcard #mastercard #digitalonboarding #faydaid #techinnovation

በአዋሽ ሬሚት ያለ እንግልት ገንዘብ ይላኩ
ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሁን ገንዘብ መላክ ቀላል ሆኗል!
በቪዛ (Visa) ወይም በማስተርካርድ (MasterCard) በመጠቀም፦
👉በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ አዋሽብር -ፕሮ ዋሌት ፈጣን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የገንዘብ ዝውውር ያድርጉ።
የአዋሽ ሬሚት መተግበሪያ አውርደው ይጠቀሙ!
ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች 👉 https://play.google.com/st...
ለ IOS ተጠቃሚዎች👉 https://apps.apple.com/us/...

3 months ago
ላኪፔይ በAI የታገዘና በድምፅ የሚሰራውን መተግበሪያ በይፋ አስመረቀ
#fastmereja | የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል የተባለለት ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) የተጠቀመ አዲስ መተግበሪያውን ዛሬ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስመርቋል። ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዚህ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ፣ ተቋሙ "ራስ" የተሰኘውንና በድምፅ ትዕዛዝ የሚሰራ የAI ረዳት ማስተዋወቁ የዕለቱ ደማቅ ክስተት ሆኗል።
የላኪፔይ አዲሱ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ታሪክ ፈርቀዳጅ የተባለለትን አገልግሎት ይዞ ቀርቧል። ደንበኞች በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች በድምፃቸው ብቻ በማዘዝ የተለያዩ የክፍያና የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይህ አሰራር በተለይ መተግበሪያዎችን ለመጫን ለሚቸገሩ ወይም ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ አካታችነትን የሚያረጋግጥ ነው።
በዚሁ መተግበሪያ አጠቃቀም ላይ የኦሮሚያ ባንክ ቀዳሚ ስትራቴጂካዊ አጋር በመሆን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ላኪፔይ "ላንዲ ግሎባል" ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል። ይህም ደንበኞች በቪዛ (Visa) እና በማስተርካርድ (MasterCard) አማካኝነት ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን በቅልጥፍና እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል።
መተግበሪያው ከገንዘብ ዝውውር ባለፈ የሚከተሉትን አዳዲስ አገልግሎቶች አካትቷል፦ የህንጻ አስተዳደር እና የአከራይ ተከራይ ማገናኛ ማህደር። የንግድ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ጋር በቪዲዮ ተገናኝተው የገበያ ተደራሽነታቸውን የሚያሰፉበት ነፃ የቪዲዮ ግንኙነት አገልግሎት።
ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ በየካቲት ወር 2025 (እ.ኤ.አ) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት አከናዋኝ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል። ተቋሙ አሁን ላይ ይዞት የቀረበው የAI ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ይበልጥ እንደሚያቀጣጥለው ይጠበቃል።
#ቢዝነስ #ሳይ_ቴክ

አዋሽ ባንክ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ
#ethiopia | አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን በይፋ ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ባንኩ ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ይፋ ያደረጋቸው መተግበሪያዎች
👉 “አዋሽ ሬሚት”፣
👉 “አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ” እና
👉 “አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት” የተሰኙ መተግበሪያዎችን ማስተዋወቁን ገልጿል።
ባንኩ እነዚህን የዲጂታል አገልግሎቶች በዝርዝር እንደሚከተለው አብራርቷል፡-
1. አዋሽ ሬሚት (Awash Remit)
ይህ መተግበሪያ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣንና ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው። ደንበኞች የቪዛ (Visa) ወይም የማስተር ካርድ (MasterCard) በመጠቀም በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ አካውንት፣ ወደ አዋሽ ብር ፕሮ ዋሌት ወይም በቅርንጫፎች በኩል የሚከፈል ገንዘብ በቀላሉ መላክ ይችላሉ።
2. አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ (Awash e-Ticketing)
ይህ አገልግሎት ኮንሰርቶችን ጨምሮ ማንኛውንም ሁነት (Event) የሚያዘጋጁ አካላት ትኬቶቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ነው። የወረቀት ትኬቶችን በQR ኮድ በመተካት ለአዘጋጆችም ሆነ ለታዳሚዎች ምቹ፣ ግልጽና ደህንነቱ የተጠበቀ አሠራርን ይፈጥራል። አገልግሎቱ ለኮንፈረንሶች፣ ለስፖርታዊ ኩነቶችና ለሃይማኖታዊ ስብሰባዎች እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።
3. አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት (Awash e-Property Management)
ይህ መተግበሪያ የህንጻ ባለቤቶችና ተከራዮች ግንኙነትን በዲጂታል መንገድ የሚያቀላጥፍ ነው። የቤት ኪራይ አሰባሰብን፣ የፋይናንስ ክትትልንና የውል ስምምነቶችን በዘመናዊ መልኩ ለማስተዳደር ይረዳል። በተጨማሪም የሚከራዩ ክፍሎችን፣ የንግድ ቦታዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በዝርዝር ለመለየትና ለማስተዳደር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።
ባንኩ በመግለጫው እንዳመለከተው፣ ከሐምሌ እስከ ታኅሣሥ 2025 ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የተከናወነው የገንዘብ ልውውጥ መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጿል።
ይህም ባንኩ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ የተመዘገበ ውጤት መሆኑ ተጠቅሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#awashbank #digitalbanking #fintechethiopia #awashremit #eticketing #propertymanagement #ethiopiabanking #digitaltransformation #financialinnovation #cashlessethiopia

አዋሽ ባንክ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ስራ አስጀመረ
#fastmereja I አዋሽ ባንክ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋት የነደፋቸውን ሦስት አዳዲስ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ባንኩ ስራ ያስጀመራቸው ሦስቱ መተግበሪያዎች አዋሽ ረሚት (Awash Remit)፣ አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ (Awash E-Ticketing) እና አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት (Awash E-Property Management) የተሰኙ ናቸው።
አዋሽ ረሚት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በቀጥታ፣ በፍጥነትና በደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ገንዘብ እንዲልኩ የሚያስችል ነው። ደንበኞች በቪዛ (Visa) ወይም በማስተር ካርድ (MasterCard) በመጠቀም በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ አዋሽ ብር ፕሮ (Awash Birr Pro) ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ ኮንሰርቶችን፣ ስፖርታዊ ኩነቶችንና የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያዘጋጁ አካላት ቲኬቶችን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ ያስችላል። መተግበሪያው የወረቀት ቲኬቶችን በዲጂታል ኮድ (QR Code) የሚተካ በመሆኑ ለአዘጋጆችም ሆነ ለታዳሚዎች ከፍተኛ ምቾት ይሰጣል።
አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት የህንፃ ባለቤቶችና ተከራዮች የኪራይ ውልን፣ የክፍያ ሁኔታንና የፋይናንስ ክትትልን በዲጂታል መንገድ እንዲያከናውኑ የተዘጋጀ ነው። መተግበሪያው የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ቦታዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር ይረዳል።
አዋሽ ባንክ በመግለጫው እንዳመለከተው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሐምሌ እስከ ታኅሣሥ 2025 ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በባንኩ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የተከናወነው የገንዘብ ዝውውር መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገልጿል።
ባንኩ በቀጣይም የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ ተጨማሪ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ለማልማት እየሰራ መሆኑን ገልጾ፣ ህብረተሰቡ እነዚህን አዳዲስ አገልግሎቶች እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።

Sponsored by
Surafel
4 months ago
አንበሳ የሌለበት የ"አንበሳ ባንክ" አዲሱ ሎጎ
ከግርማ ሞገስ ወደ ጥቁር ጭረት
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለ18 ዓመታት በግርማ ሞገስ ሲያገሳ የነበረው "አንበሳ" ትላንት ሌሊት ድንገት ድምፁን አጥፍቷል።
ዛሬ ጠዋት ስንነቃ ያገኘነው ግን ያንን የሚያውቁትን ባለጋማ አንበሳ ሳይሆን፣ ቢጫ ክብ ውስጥ የተሰመረች እንቆቅልሽ የሆነች "ጥቁር ጭረት" ነው። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ራሱን "ዲጂታል ባንክ" ለማድረግ የወሰደው ይህ እርምጃ፣ በንግዱ ዓለም "ድፍረት" ወይስ "ራስን ማጥፋት" የሚል ክርክር አስነስቷል።
የግርማው ፍጻሜ፦ አንበሳ የሌለበት "አንበሳ ባንክ"
ባንኩ ለሁለት አስርት ዓመታት የገነባው ትልቁ ሀብት ስሙ ብቻ አልነበረም፤ ያ ምስላዊ መታወቂያው (Visual Identity) እንጂ። በንግድ ፍልስፍና "Brand Equity" የሚባለው ትልቁ ካፒታል ደንበኛው ተቋሙን በሰከንድ ውስጥ ለይቶ የሚያውቅበት ምልክት ነው።
ዛሬ ግን ባንኩ ያንን ግዙፍ ካፒታል "በዘመናዊነት" ስም ወደ ቆሻሻ መጣያ ወርውሮታል። አዲሱ አርማ "የሁሉም ነገር ጅማሬ" የሚል ፍልስፍና ቢሰጠውም፣ ለብዙዎች ግን "የማንነት መጥፋት" (Identity Crisis) ነው። ስሙ "አንበሳ" ሆኖ ምልክቱ "ጭረት" መሆኑ፣ በደንበኞች አእምሮ ውስጥ ያለውን ስዕላዊ ትስስር የበጠሰ የንግድ ቁማር ይመስላል።
የዲዛይን እንቆቅልሽ፡ "ዘመናዊነት" ወይስ "መደናገር"?
የአሁኑ ዘመን የባንክ ፍልስፍና ወደ ቀላልነት (Minimalism) ማዘንበሉ አይካድም። እንደ Mastercard ያሉ ኩባንያዎች አርማቸውን አቅልለዋል። ነገር ግን ማስተርካርድ የድሮውን ማንነቱን የሚገልጹትን ሁለት ክበቦች አላጠፋም፤ ይልቁንም አሻሻላቸው እንጂ።
አንበሳ ባንክ ግን የወሰደው እርምጃ እንደ አሜሪካዊው Gap ኩባንያ ነው።
ጋፕ ለዓመታት የታወቀበትን ሰማያዊ አርማ በ"ዘመናዊ" ጭረት ለመተካት ሞክሮ ደንበኞቹ "ማንነታችንን መልሱ" ብለው በማመጻቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ወደ ነባሩ አርማ ተመልሷል።
የአንበሳ ባንክ አዲስ ምልክትም "አንበሳው የት ሄደ?" የሚለውን ስሜታዊ ጥያቄ መመለስ ካልቻለ፣ በገበያው ውስጥ ሰርጎ የመግባት (Market Penetration) አቅሙ ሊዳከም ይችላል።
ቢጫና ጥቁር፦ የደህንነት ወይስ የጥንቃቄ ምልክት?
በባንክ ስነ-ልቦና ውስጥ ቀለሞች ትልቅ ትርጉም አላቸው። ሰማያዊ እምነትን፣ አረንጓዴ እድገትን፣ ቀይ ጥንካሬን ይወክላሉ። የአንበሳ ባንክ አዲሱ ቢጫና ጥቁር ጥምረት ግን በትራፊክ ህግ "ተጠንቀቅ" (Caution) የሚል መልዕክት አለው። በአንጻሩ የቀድሞው ወርቃማና ቀይ ቀለም የንግስናና የሀብት ምልክት ነበር። ከዚህ አንጻር የባንኩ አዲስ ቀለም ደንበኛው ሊሰማው የሚገባውን "የመረጋጋትና የደህንነት" ስሜት ይሸረሽረው ይሆን? የሚለው የባለሙያዎች ስጋት ነው።
በጭረት የታሰረው "አንበሳ ፕላስ"
ባንኩ "አንበሳ ፕላስ" የተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ ከአዲሱ አርማ ጋር ማስተዋወቁ፣ ፍላጎቱ ከባህላዊ ባንክነት ወጥቶ ወደ ቴክኖሎጂ ኩባንያነት (FinTech) ለመጠጋት መሆኑን ያሳያል። ሆኖም የንግድ ፍልስፍና እንደሚለው፦ “Brand is not a logo, it’s a promise.” (ብራንድ ማለት አርማ ሳይሆን ቃል ኪዳን ነው።)
አርማው ቢዘምንና በውስጡ ያለው የዲጂታል አገልግሎት ግን እንደ ድሮው የሚቆራረጥ ከሆነ፣ ለውጡ "የላይ ላዩ" (Superficial) ብቻ ሆኖ ይቀራል። 2.6 ሚሊዮን ደንበኞችን በአዲስ "ጭረት" ማሳመን ቀላል ባይሆንም፣ ባንኩ ግን "ወይ መዝመን ወይ መጥፋት" የሚለውን የህልውና መንገድ መርጧል።
ማጠቃለያ፦ ድፍረት ወይስ ውድቀት?
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ራሱን እንደገና ለመውለድ (Rebirth) የቆረጠ ይመስላል። ነገር ግን አንበሳ ባልታየበት አርማ "አንበሳ ነኝ" ብሎ መቀጠል ትልቅ ፈተና ነው። ይህ አዲስ "ጭረት" የኢትዮጵያን ባንክ ዘርፍ የሚቀይር "የሁሉም ነገር ጅማሬ" ይሁን ወይም ደንበኛን የሚያባርር "የማንነት መናጋት"፣ ውጤቱን የሚወሰነው በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት በሚታየው የአገልግሎት ጥራት እንጂ በአርማው ውበት አይሆንም።
አንበሳው ተመልሶ ይመጣ ይሆን ወይስ በዚህ ጭረት እንደታሰረ ይቀራል?