2 months ago
የአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 በይፋ ተከፈተ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም "የአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018" በሚል ስያሜ የንግድ ትርኢትና ባዛር በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።
ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ኤክስፖ፣ ሸማቾችና ነጋዴዎች የበዓል ግብይታቸውን በአንድ ስፍራ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በቆይታውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ይሳተፍበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ዮሐንስ መርጊያ ባንኩ በኤክስፖው ወቅት ለሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዘመናዊና የተቀናጀ የባንክ አገልግሎትን በማዕከሉ ውስጥ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
አዋሽ ባንክ በዚህ ዝግጅት ላይ "አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ" የተሰኘውን አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ በይፋ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ይህም አገልግሎት ማንኛውንም ዓይነት ኩነት የሚያዘጋጁ አካላት ቲኬቶችን ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ደህንነቱ የተጠበቀ መድረክ ነው።
መተግበሪያው የወረቀት ቲኬቶችን በQR ኮድ በመተካት ለዝግጅት አዘጋጆችና ለታዳሚዎች ዘመናዊና ምቹ አሠራርን ይዞ የቀረበ ሲሆን፣ በኤክስፖው ላይ የሚታደሙ ሸማቾችም በባንኩ ዲጂታል መሠረተ ልማት በመታገዝ ፈጣን ግብይት እንዲፈጽሙ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
በተጨማሪም "አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ" በመጠቀም ግብይት የሚፈጽሙ ደንበኞች የመኪና ዕድል ሽልማቶችን የሚያገኙበት አጋጣሚ የተመቻቸ ከመሆኑም በላይ፣ በ"አዋሽ ብር" ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች የ5 በመቶ ተመላሽ ማበረታቻ ተዘጋጅቶላቸዋል።
የዘንድሮውን ኤክስፖ አዋሽ ባንክ ከታሜሶል ኮሚኒኬሽን ጋር በጥምረት ማዘጋጀቱን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#awashbank #awashbirr #easterexpo2018 #ethiopia #digitalbanking #eticketing #addisababa #holidaymarket

አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ መተግበሪያ
===================
👉ኮንሰርቶችን ፣ ስፖርታዊ ውድድሮችን ፣ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎችን ወይም ሌሎች ኩነቶች እያዘጋጁ ነው?
👉ትኬቶችዎን በቀላሉ እና በዲጂታል መንገድ ይሽጡ!
አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ፦
✔️ የወረቀት ትኬቶችን በQR Code ይቀይራል
✔️ ለታዳሚዎች ፈጣንና ቀላል ግብዣ
✔️ ለአዘጋጆች ግልጽ የሽያጭ ቁጥጥር
✔️ ዘመናዊ እና የተመረጠ ቴክኖሎጂ
👉 ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጠውን አዋሽብር ፕሮ በማውረድ ኩነቶችዎን ወደ ዲጂታል ዘመን ያምጡ!
ለ አንድሮይድ ተጠቃሚዎች👉 https://play.google.com/st...
ለ IOS ተጠቃሚዎች 👉 https://apps.apple.com/bf/... #awashbank #nurturingliketheriver #eticketing #digitalethiopia #eventmanagement

3 months ago
አዋሽ ባንክ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ
#ethiopia | አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን በይፋ ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ባንኩ ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ይፋ ያደረጋቸው መተግበሪያዎች
👉 “አዋሽ ሬሚት”፣
👉 “አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ” እና
👉 “አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት” የተሰኙ መተግበሪያዎችን ማስተዋወቁን ገልጿል።
ባንኩ እነዚህን የዲጂታል አገልግሎቶች በዝርዝር እንደሚከተለው አብራርቷል፡-
1. አዋሽ ሬሚት (Awash Remit)
ይህ መተግበሪያ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣንና ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው። ደንበኞች የቪዛ (Visa) ወይም የማስተር ካርድ (MasterCard) በመጠቀም በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ አካውንት፣ ወደ አዋሽ ብር ፕሮ ዋሌት ወይም በቅርንጫፎች በኩል የሚከፈል ገንዘብ በቀላሉ መላክ ይችላሉ።
2. አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ (Awash e-Ticketing)
ይህ አገልግሎት ኮንሰርቶችን ጨምሮ ማንኛውንም ሁነት (Event) የሚያዘጋጁ አካላት ትኬቶቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ነው። የወረቀት ትኬቶችን በQR ኮድ በመተካት ለአዘጋጆችም ሆነ ለታዳሚዎች ምቹ፣ ግልጽና ደህንነቱ የተጠበቀ አሠራርን ይፈጥራል። አገልግሎቱ ለኮንፈረንሶች፣ ለስፖርታዊ ኩነቶችና ለሃይማኖታዊ ስብሰባዎች እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።
3. አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት (Awash e-Property Management)
ይህ መተግበሪያ የህንጻ ባለቤቶችና ተከራዮች ግንኙነትን በዲጂታል መንገድ የሚያቀላጥፍ ነው። የቤት ኪራይ አሰባሰብን፣ የፋይናንስ ክትትልንና የውል ስምምነቶችን በዘመናዊ መልኩ ለማስተዳደር ይረዳል። በተጨማሪም የሚከራዩ ክፍሎችን፣ የንግድ ቦታዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በዝርዝር ለመለየትና ለማስተዳደር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።
ባንኩ በመግለጫው እንዳመለከተው፣ ከሐምሌ እስከ ታኅሣሥ 2025 ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የተከናወነው የገንዘብ ልውውጥ መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጿል።
ይህም ባንኩ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ የተመዘገበ ውጤት መሆኑ ተጠቅሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#awashbank #digitalbanking #fintechethiopia #awashremit #eticketing #propertymanagement #ethiopiabanking #digitaltransformation #financialinnovation #cashlessethiopia

Sponsored by
Surafel