Logo
Getu Temesgen
ዳሸን ባንክ አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

​#ethiopia | ዳሸን ባንክ የቴክኖሎጂ አድማሱን በማስፋት እስከ 6 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኝ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድርን ጨምሮ አራት አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው ደመቅ ያለ ስነ-ሥርዓት ላይ በይፋ አስጀምሯል።

ባንኩ ያስጀመራቸው እነዚህ አገልግሎቶች የደንበኞችን የባንክ አጠቃቀም ዘመናዊና ምቹ ለማድረግ የታለሙ ሲሆኑ፣ በተለይም የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ሱፐር አፕ የሚሰሩት የቲክቶክ ቪዲዮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝና በደጋፊዎች ድምፅ ሲታጀብ ቀዳሚ ለሚወጡት የ3 ሚሊዮን፣ የ2 ሚሊዮን እና የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማቶችን በቅደም ተከተል የሚያበረክት ይሆናል።

​ከሽልማቱ ጎን ለጎን ባንኩ የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም ደንበኞች ባሉበት ሆነው በስልካቸው ብቻ የባንክ ሒሳብ እንዲከፍቱ የሚያስችለውን የዲጂታል ኦን-ቦርዲንግ አገልግሎት አስተዋውቋል፤ ይህም በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ አሰራር ሆኖ ተመዝግቧል።

ከዚህ በተጨማሪ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ለሌሎች በማስተዋወቅ የማበረታቻ ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችለው የዳሸን ስታር ሪፈራል ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

​ሌላው በዕለቱ ይፋ የተደረገው ትልቅ አገልግሎት ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የቀረበው የዳሸን ቨርቹዋል ካርድ ሲሆን፣ ይህ አገልግሎት ደንበኞች እንደ አማዞን፣ አሊባባ እና ኔትፍሊክስ ባሉ ዓለም አቀፍ የንግድ ድረ-ገጾች ላይ ክፍያዎችን በቀላሉ እንዲፈፅሙና ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን ሐዋላ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራውና ከ250 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ያስተናገደው የዳሸን ሱፐር አፕ፣ ከነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች በተጨማሪ እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው የዕድል ጨዋታ በማቅረብ የደንበኞቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#dashenbank #dashensuperapp #digitalbanking #ethiopianbanking #tiktokchallenge #virtualcard #mastercard #digitalonboarding #faydaid #techinnovation

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.