2 days ago
ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት የ10 ቢሊዮን ብር ገደማ ትርፍ ማግኘቱን ይፋ አደረገ
#ethiopia | ዘመን ባንክ በ2018 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 9 ነጥብ 97 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ማስመዝገቡን በዛሬው ዕለት ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ ጉባኤ ላይ አስታውቋል።
በበጀት ዓመቱ የባንኩ በጥቅል የሀብት መጠን የ31 ነጥብ 3 በመቶ እድገት በማሳየት 116 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
በተጨማሪም የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 14 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ጠቅላላ ካፒታሉ 26 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጻል።
የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ እንዬ ቢምር በበኩላቸው 2018 የበጀት ዓመት ለባንኩ ጠንካራ የፋይናንስ አፈጻጸምና ቀጣይነት ያለው እድገት የታየበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
ባለአክሲዮኖች በአንድ አክሲዮን የሚያገኙት የትርፍ ድርሻ 53 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን የጠቆሙት ሰብሳቢዋ፣ ይህ ስኬት የባንኩን ጠንካራ አፈጻጸም፣ የደንበኞችንና ባለአክሲዮኖችን እምነት እንዲሁም የሰራተኞችን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 17 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት 6 ነጥብ 75 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማተረፉን አብራርተዋል።
#zemenbank #banking #bankingsector #ethiopianbanking #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
ከተዘጋ ካዝና እስከ ነፃ ገበያ፡ የባንኮች አዲስ ትንሳኤ
#ethiopianeconomy #ethiopianbanking #macroeconomicreform #cbe #ethiopiabusiness #nbe #forexethiopia
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

5 months ago
የሲንቄ ባንክ አስደናቂ ጉዞ እና ወቅታዊ ቁመና
#ethiopia | በቅርቡ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የቀረበው የሲንቄ ባንክ ዘጋቢ ፊልም የተቋሙን ጠንካራ የዕድገት ጉዞ እና ስኬቶች በዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ከአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተቋምነት ወደ ባንክ ባደገ በአራት ዓመታት ውስጥ ብቻ በኢንዱስትሪው ከነበረበት 29ኛ ደረጃ ወደ 5ኛ ደረጃ በመሸጋገር ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል።
ባንኩን ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ለየት የሚያደርገው ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ከቀድሞው የማይክሮፋይናንስ ተግባሩ ጋር አጣምሮ ማስኬዱ ነው።
በአሁኑ ወቅት የባንኩ የብድር ድርሻ 66 በመቶ የሚሆነው ለማይክሮፋይናንስ ዘርፍ የተመደበ ሲሆን ይህም የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ አቅም በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በተለይም ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከጠቅላላ ብድሩ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን ለዚሁ ዘርፍ በማቅረብ የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
በአኃዝ ሲታይ ባንኩ ለመደበኛ ብድር 108 ቢሊዮን ብር ያሰራጨ ሲሆን የተበዳሪዎቹም ቁጥር ከ800 ሺህ በላይ ደርሷል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በወቢ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አማካኝነት ለአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች ሰባት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር በአንድ ዓመት ውስጥ ማቅረብ መቻሉም ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 192 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የተፈረመ ካፒታሉ 75 ቢሊዮን እና ጠቅላላ ካፒታሉ 21 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
በተጨማሪም የዲጂታል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመን የሲንቄ ሱፐር አፕ የተሰኘ መተግበሪያ በቅርቡ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ ተነግሯል።
ስለ ባንኩ ታሪክ እና የወደፊት እቅዶች ሰፊ መረጃ ለማግኘት የተዘጋጀውን ዘጋቢ ፊልም መመልከት ይቻላል።
https://youtu.be/28X-v6yZP...
#siinqeebank #ethiopianbanking #economy #finance #digitalbanking #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
ዳሸን ባንክ አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ የቴክኖሎጂ አድማሱን በማስፋት እስከ 6 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኝ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድርን ጨምሮ አራት አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው ደመቅ ያለ ስነ-ሥርዓት ላይ በይፋ አስጀምሯል።
ባንኩ ያስጀመራቸው እነዚህ አገልግሎቶች የደንበኞችን የባንክ አጠቃቀም ዘመናዊና ምቹ ለማድረግ የታለሙ ሲሆኑ፣ በተለይም የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ሱፐር አፕ የሚሰሩት የቲክቶክ ቪዲዮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝና በደጋፊዎች ድምፅ ሲታጀብ ቀዳሚ ለሚወጡት የ3 ሚሊዮን፣ የ2 ሚሊዮን እና የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማቶችን በቅደም ተከተል የሚያበረክት ይሆናል።
ከሽልማቱ ጎን ለጎን ባንኩ የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም ደንበኞች ባሉበት ሆነው በስልካቸው ብቻ የባንክ ሒሳብ እንዲከፍቱ የሚያስችለውን የዲጂታል ኦን-ቦርዲንግ አገልግሎት አስተዋውቋል፤ ይህም በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ አሰራር ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚህ በተጨማሪ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ለሌሎች በማስተዋወቅ የማበረታቻ ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችለው የዳሸን ስታር ሪፈራል ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ሌላው በዕለቱ ይፋ የተደረገው ትልቅ አገልግሎት ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የቀረበው የዳሸን ቨርቹዋል ካርድ ሲሆን፣ ይህ አገልግሎት ደንበኞች እንደ አማዞን፣ አሊባባ እና ኔትፍሊክስ ባሉ ዓለም አቀፍ የንግድ ድረ-ገጾች ላይ ክፍያዎችን በቀላሉ እንዲፈፅሙና ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን ሐዋላ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራውና ከ250 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ያስተናገደው የዳሸን ሱፐር አፕ፣ ከነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች በተጨማሪ እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው የዕድል ጨዋታ በማቅረብ የደንበኞቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#dashenbank #dashensuperapp #digitalbanking #ethiopianbanking #tiktokchallenge #virtualcard #mastercard #digitalonboarding #faydaid #techinnovation

7 months ago
እናት ባንክ የሴት አመራሮችን አቅም ለማሳደግ ያለመ የፓናል ውይይት አካሄደ
#ethiopia | እናት ባንክ "High Level Women Leadership" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ስልታዊ የምክክር መድረክ፣ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ እና የአመራር ብቃት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።
በውይይቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው በዘርፉ ስላለው ተግዳሮት እና ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች ሰፊ ምክክር አድርገዋል።
የሴቶች ተሳትፎ 🔎
የእናት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሳሰቡት፣ ባንኩ ባለፉት 13 ዓመታት የሴት ሠራተኞችን አቅም በማጎልበት እና ወደ አመራርነት በማምጣት የደንበኞች አገልግሎቱን ማሻሻል ችሏል። በአሁኑ ወቅት የባንኩን እድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሴት ሠራተኞች ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት በአሃዝ ሲገለጽ፡-
* አጠቃላይ ሠራተኞች፦ ከ2,000 በላይ ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 952ቱ ሴቶች ናቸው።
* የቦርድ አመራር፦ ከ11 የቦርድ አባላት መካከል 7ቱ ሴቶች ናቸው።
* ከፍተኛ የሥራ ካውንስል፦ 44 በመቶ የሚሆኑት አባላት ሴቶች ናቸው።
ተግዳሮቶች እና የኢኮኖሚ ፋይዳው
የባንኩ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር (CFO) ወ/ሮ ትዕግስት አባተ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ደረጃ ያለው የሴቶች ቁጥር አሁንም አነስተኛ ነው። ለዚህም እንደ እንቅፋት የሚጠቀሱት፦
* በራስ የመተማመን ሁኔታ።
* የቤት ውስጥ ኃላፊነትን ከቢሮ ሥራ ጋር አስተካክሎ የመምራት (Work-life balance) ተግዳሮት ናቸው።
ይሁን እንጂ ሴቶች በአመራርነት ደረጃ መሳተፋቸው የሀገሪቱን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) ከ3 እስከ 4 በመቶ ሊያሳድገው እንደሚችል ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም በፋይናንስ ዘርፉ የሴቶች የአመራር ድርሻ ወደ 25 በመቶ እንዲያድግ ግብ አስቀምጧል ብለዋል።
በመረሃግብሩ ላይ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን፣ ተዋበች ቢሻው (ዶ/ር)፣ ናስሪን መሐመድ እና ገመቹ ዋቅቶላ (ዶ/ር) ያላቸውን የካበተ ልምድ ለታዳሚዎች አጋርተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #enatbank #womeninleadership #ethiopianbanking #empoweringwomen #financialsector #addisababa #ethiopia

8 months ago
ዳሽን ባንክ ለደንበኞቹ የኢፍጣር መርሃ ግብር አዘጋጀ
#ethiopia | ዳሽን ባንክ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ ያዘጋጀውን ልዩ የኢፍጣር መርሃ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሄደ።
መርሃ ግብሩ ባንኩ ያለውን ማህበራዊ ተሳትፎ ለማሳደግና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባደረጉት ንግግር፤ ለባንኩ ደንበኞችና ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አስፋው አክለውም ዳሽን ባንክ ከደንበኞች እሴትና የፋይናንስ ፍላጎት ጋር የሚጣጣሙ፣ የሸሪዓ መርሆዎችን ያከበሩ የባንክ አገልግሎቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ማህበራዊ ኃላፊነትና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት
ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት (ሸሪካ) ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለው ቁርጠኝነት መሰረት ባለፈው ዓመት ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
ከደንበኞች በአደራ መልክ የሰበሰበውን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ለ31 አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማከፋፈሉ፤
በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች ከወለድ ነፃ በሆነ መንገድ የ100 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ማቅረቡ።
ዳሽን ባንክ በአሁኑ ወቅት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የኢንተረስት ፍሪ (ከወለድ ነፃ) አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት የገለጸ ሲሆን፣ ይህም ባንኩ ያለውን ሁሉን አቀፍነትና የጋራ ተጠቃሚነት ባህል እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።
ባንኩ በዘርፉ ባሳየው ጥንካሬ በ2023 በዱባይ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ "በኢትዮጵያ ጠንካራው የኢስላሚክ የችርቻሮ ባንክ መስኮት" (The Strongest Islamic Retail Banking Window in Ethiopia) የሚል እውቅና ማግኘቱም ይታወሳል።
በተጨማሪም ዳሽን ባንክ ዓለም አቀፍ የእስልምና ፋይናንስ ተቋማትን የሂሳብ አያያዝ፣ የኦዲትና የሸሪዓ መስፈርቶችን የሚያወጣው AAOIFI (The Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions) አባል የሆነ ብቸኛው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋም ነው።
#dashenbank #iftarprogram #islamicbanking #shariacompliant #ethiopianbanking #ramadankareem #financialinclusion

Sponsored by
Surafel
Comments