ላኪፔይ በAI የታገዘና በድምፅ የሚሰራውን መተግበሪያ በይፋ አስመረቀ
#fastmereja | የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል የተባለለት ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) የተጠቀመ አዲስ መተግበሪያውን ዛሬ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስመርቋል። ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዚህ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ፣ ተቋሙ "ራስ" የተሰኘውንና በድምፅ ትዕዛዝ የሚሰራ የAI ረዳት ማስተዋወቁ የዕለቱ ደማቅ ክስተት ሆኗል።
የላኪፔይ አዲሱ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ታሪክ ፈርቀዳጅ የተባለለትን አገልግሎት ይዞ ቀርቧል። ደንበኞች በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች በድምፃቸው ብቻ በማዘዝ የተለያዩ የክፍያና የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይህ አሰራር በተለይ መተግበሪያዎችን ለመጫን ለሚቸገሩ ወይም ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ አካታችነትን የሚያረጋግጥ ነው።
በዚሁ መተግበሪያ አጠቃቀም ላይ የኦሮሚያ ባንክ ቀዳሚ ስትራቴጂካዊ አጋር በመሆን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ላኪፔይ "ላንዲ ግሎባል" ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል። ይህም ደንበኞች በቪዛ (Visa) እና በማስተርካርድ (MasterCard) አማካኝነት ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን በቅልጥፍና እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል።
መተግበሪያው ከገንዘብ ዝውውር ባለፈ የሚከተሉትን አዳዲስ አገልግሎቶች አካትቷል፦ የህንጻ አስተዳደር እና የአከራይ ተከራይ ማገናኛ ማህደር። የንግድ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ጋር በቪዲዮ ተገናኝተው የገበያ ተደራሽነታቸውን የሚያሰፉበት ነፃ የቪዲዮ ግንኙነት አገልግሎት።
ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ በየካቲት ወር 2025 (እ.ኤ.አ) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት አከናዋኝ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል። ተቋሙ አሁን ላይ ይዞት የቀረበው የAI ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ይበልጥ እንደሚያቀጣጥለው ይጠበቃል።
#ቢዝነስ #ሳይ_ቴክ

3 months ago