15 days ago
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!
* የታገዱ ሂሳቦች መፍትሄ አገኙ
#ethiopia | ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ውድ ደንበኞች በሙሉ፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት፣ በተመረጡ ከተሞች የሚገኙና ከ"ፋይዳ" መታወቂያ ጋር ያልተሳሰሩ የባንክ ሂሳቦች ላይ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ እገዳን በተመለከተ ባንኩ አዲስና ፈጣን መፍትሄዎችን የያዘ መግለጫ አውጥቷል።
የእገዳው መነሻና አዲሱ መፍትሄ
እስከ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥራቸውን ከባንክ ሂሳባቸው ጋር ያላስተሳሰሩ ደንበኞች ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የደረሰውን ከፍተኛ የደንበኞች ጫና ለመቋቋም ባንኩ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦
1. የታገዱ ሂሳቦች መለቀቅ
ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 12 ቀን ድረስ በእገዳ ምክንያት እንዳይንቀሳቀሱ ከተደረጉት ሂሳቦች ውጪ፣ የፋይዳ መታወቂያቸውን ያስተሳሰሩ ደንበኞች ሂሳባቸውን ወዲያውኑ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተደርጓል።
2. አውቶማቲክ እገዳ ማንሳት
ከግንቦት 12 ጀምሮ ደንበኞች የፋይዳ መታወቂያቸውን ከሂሳባቸው ጋር እንዳስተሳሰሩ፣ የባንኩ የመረጃ ስርዓት (System) **በራሱ ጊዜ እገዳውን እንዲያነሳ** ተደርጓል።
አዲስ የቀነ-ገደብ ማሳሰቢያ
እስካሁን ያላስተሳሰሩ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞች፣ የፋይዳ መታወቂያቸውን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በማስተሳሰር ሂሳባቸውን በቀጣይነት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ባንኩ በጥብቅ አሳስቧል።
የማስተሳሰሪያ አማራጮች፦
በማንኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት።
በባንኩ የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ፦ 👉 https://cbefayda.cbe.com.e...
ባንኩ ደንበኞች በመጉላላታቸው ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ የደንበኞችን እርካታ እውን ለማድረግ መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
#getu #cbe #commercialbankofethiopia #nationalid #faydaid #bankblockethiopia #onlineregistration #systemupdate #customersatisfaction #ሰበርዜና #ኢትዮጵያንግድባንክ #ፋይዳመታወቂያ #የባንክእገዳ #የዲጂታልኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago
ዳሸን ባንክ አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ የቴክኖሎጂ አድማሱን በማስፋት እስከ 6 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኝ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድርን ጨምሮ አራት አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት ባዘጋጀው ደመቅ ያለ ስነ-ሥርዓት ላይ በይፋ አስጀምሯል።
ባንኩ ያስጀመራቸው እነዚህ አገልግሎቶች የደንበኞችን የባንክ አጠቃቀም ዘመናዊና ምቹ ለማድረግ የታለሙ ሲሆኑ፣ በተለይም የይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ሱፐር አፕ የሚሰሩት የቲክቶክ ቪዲዮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝና በደጋፊዎች ድምፅ ሲታጀብ ቀዳሚ ለሚወጡት የ3 ሚሊዮን፣ የ2 ሚሊዮን እና የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማቶችን በቅደም ተከተል የሚያበረክት ይሆናል።
ከሽልማቱ ጎን ለጎን ባንኩ የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያን በመጠቀም ደንበኞች ባሉበት ሆነው በስልካቸው ብቻ የባንክ ሒሳብ እንዲከፍቱ የሚያስችለውን የዲጂታል ኦን-ቦርዲንግ አገልግሎት አስተዋውቋል፤ ይህም በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ አሰራር ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚህ በተጨማሪ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ለሌሎች በማስተዋወቅ የማበረታቻ ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችለው የዳሸን ስታር ሪፈራል ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ሌላው በዕለቱ ይፋ የተደረገው ትልቅ አገልግሎት ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የቀረበው የዳሸን ቨርቹዋል ካርድ ሲሆን፣ ይህ አገልግሎት ደንበኞች እንደ አማዞን፣ አሊባባ እና ኔትፍሊክስ ባሉ ዓለም አቀፍ የንግድ ድረ-ገጾች ላይ ክፍያዎችን በቀላሉ እንዲፈፅሙና ከውጭ ሀገር የሚላክላቸውን ሐዋላ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ያፈራውና ከ250 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ያስተናገደው የዳሸን ሱፐር አፕ፣ ከነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች በተጨማሪ እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው የዕድል ጨዋታ በማቅረብ የደንበኞቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#dashenbank #dashensuperapp #digitalbanking #ethiopianbanking #tiktokchallenge #virtualcard #mastercard #digitalonboarding #faydaid #techinnovation