Logo
Getu Temesgen
አዋሽ ባንክ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ
#ethiopia | ​አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን በይፋ ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ።

ባንኩ ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ይፋ ያደረጋቸው መተግበሪያዎች

👉 “አዋሽ ሬሚት”፣
👉 “አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ” እና
👉 “አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት” የተሰኙ መተግበሪያዎችን ማስተዋወቁን ገልጿል።

​ባንኩ እነዚህን የዲጂታል አገልግሎቶች በዝርዝር እንደሚከተለው አብራርቷል፡-

​1. አዋሽ ሬሚት (Awash Remit)
​ይህ መተግበሪያ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣንና ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ ዝውውር እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው። ደንበኞች የቪዛ (Visa) ወይም የማስተር ካርድ (MasterCard) በመጠቀም በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ አካውንት፣ ወደ አዋሽ ብር ፕሮ ዋሌት ወይም በቅርንጫፎች በኩል የሚከፈል ገንዘብ በቀላሉ መላክ ይችላሉ።

​2. አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ (Awash e-Ticketing)
​ይህ አገልግሎት ኮንሰርቶችን ጨምሮ ማንኛውንም ሁነት (Event) የሚያዘጋጁ አካላት ትኬቶቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ነው። የወረቀት ትኬቶችን በQR ኮድ በመተካት ለአዘጋጆችም ሆነ ለታዳሚዎች ምቹ፣ ግልጽና ደህንነቱ የተጠበቀ አሠራርን ይፈጥራል። አገልግሎቱ ለኮንፈረንሶች፣ ለስፖርታዊ ኩነቶችና ለሃይማኖታዊ ስብሰባዎች እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።

​3. አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት (Awash e-Property Management)
​ይህ መተግበሪያ የህንጻ ባለቤቶችና ተከራዮች ግንኙነትን በዲጂታል መንገድ የሚያቀላጥፍ ነው። የቤት ኪራይ አሰባሰብን፣ የፋይናንስ ክትትልንና የውል ስምምነቶችን በዘመናዊ መልኩ ለማስተዳደር ይረዳል። በተጨማሪም የሚከራዩ ክፍሎችን፣ የንግድ ቦታዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በዝርዝር ለመለየትና ለማስተዳደር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።

ባንኩ በመግለጫው እንዳመለከተው፣ ከሐምሌ እስከ ታኅሣሥ 2025 ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የተከናወነው የገንዘብ ልውውጥ መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጿል።

ይህም ባንኩ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሥራቱ የተመዘገበ ውጤት መሆኑ ተጠቅሷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#awashbank #digitalbanking #fintechethiopia #awashremit #eticketing #propertymanagement #ethiopiabanking #digitaltransformation #financialinnovation #cashlessethiopia

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.