6 months ago
"አላስፈላጊ ጉዞዎች ይቅሩ፣ የእግር ጉዞ ባህል ይሁን" መንግስት
#ethiopia | በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦትና ግብይት ላይ ጫና ማሳደሩን ተከትሎ፣ መንግሥት ማኅበረሰቡ የነዳጅ አጠቃቀም ዘይቤውን እንዲቀይር ጥሪ አቀረበ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ወቅታዊው ቀውስ በአገሪቱ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም መንግሥት አዳዲስ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ገልጸዋል።
ዋና ዋና መመሪያዎችና የቀረቡ ጥሪዎች
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ችግሩን በጋራ ለመወጣት ማኅበረሰቡ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ አሳስቧል፦
ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም አላስፈላጊ የሆኑ የጉዞ ፕሮግራሞችን እንዲሰርዝና እንዲያቆም።
* የእግር ጉዞ ባህል፦ የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ ማኅበረሰቡ የእግር ጉዞን እንደ ባህል እንዲያዳብር።
የግል ተሽከርካሪዎችን አጠቃቀም በመቀነስ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት አማራጮችን በስፋት መጠቀም።
ከነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ሥልቶችን መከተል።
በነዳጅ ሽያጭና ሥርጭት ላይ የሚስተዋሉ ሕገወጥ ድርጊቶችን በማጋለጥ ረገድ ሕዝቡ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ።
ዶ/ር ካሳሁን በመግለጫቸው እንደተናገሩት፣ ሌሎች አገራት መሰል የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ሲያጋጥማቸው ጥብቅ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕቀባዎችን (Sanctions) ተግባራዊ ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የሕዝቡን ኑሮ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ችግሩን በዕቀባ ሳይሆን ከሕዝቡ ጋር በመተባበርና በቁጠባ ለመሻገር መወሰኑን አስረድተዋል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው አለመረጋጋት በነዳጅ ዋጋና አቅርቦት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስና ብሔራዊ ኢኮኖሚው እንዳይጎዳ ለማድረግ የታለመ መሆኑም ተመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ሪፖርተር #ethiopia #fuelshortage #energyconservation #tradeministry #economy #greentransport

በሰከንድ አንድ ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል የትራንስፖርት አማራጭ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | ይህንን አዲስ የክፍያ አማራጭ ወደ ዘርፉ ያስገባው ዘማይ የተባለው የግል ማህበር ነው።
ይህንን አማራጭ የሚፈልጉ ዜጎች ወደ 6312 የጥሪ ማዕከል በመደወል መገልገል ይችላሉ ነው የተባለው።
ማህበሩ "ዘማይ ጉዞ" እና "ዘማይ ብር " የተሰኙ ሁለት አገልግሎቶች ዛሬ በመስቀል አደባባይ ባከናወነው ስነስርአት ለህዝብ ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ስራውን በ1,680 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ቁጥራቸውን ወደ 30,000 የማሳደግ ሰፊ እቅድ መያዙን ገልጿል።
እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ በመሆናቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ ከመሆናቸውም በላይ ለሀገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ተብሏል።
የጉዞ መነሻ ዋጋው 100 ብር ሆኖ በየኪሎሜትሩ ደግሞ 12 ብር በሚታሰብበት ዋጋ ለህብረተሰቡ አቅርቢያለሁ ብሏል።
ከደህንነት አንጻርም አሽከርካሪዎቹ በቂ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ተሽከርካሪዎቹም ተሳፋሪዎች ንብረት ቢረሱ የሚጠቁም የደወል ምልክትና ገመድ አልባ የስልክ ቻርጀር የተገጠመላቸው ናቸው ተብሏል።
የመኪናዎቹ ንጽህና በዘመናዊ የእንፋሎት እጥበት የሚከናወን በመሆኑ የኤሌክትሪክ አካላቶቻቸው ከውሃ ንክኪ ተጠብቀው እንዲቆዩ ያስችላል ተብላል።
ከዚህ በተጨማሪም ዘማይ ብር የተሰኘው መተግበሪያ ከባንኮችና ከቴሌብር ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለደንበኞች የ20 በመቶ ቅናሽና ቀልጣፋ የክፍያ አማራጭን ይዞ መጥቷል።
ድርጅቱ በሰከንድ አንድ ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 6312 የጥሪ ማዕከል በማቋቋም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ የስራ እድልና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#zemayguzo #zemaybirr #electricvehicles #ethiopia #digitaleconomy #greentransport #techinnovation #addisababa

7 months ago
''አጫጭር መንገዶችን በእግር እንጓዝ'' ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ቀውስ በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል። ይህ ክስተት ኢትዮጵያን ጨምሮ ነዳጅ ተቀባይ ሀገራት ላይ የአቅርቦት መቆራረጥ እና እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፣ አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ ህብረተሰቡ ነዳጅን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባ እንዲጠቀም አሳስበዋል። ከንቲባዋ ለችግሩ መፍትሄ ይሆኑ ዘንድ የሚከተሉትን አማራጮች ጠቁመዋል፡-
* የእግር ጉዞ፦ አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ የነዳጅ ፍጆታን መቀነስ።
* አማራጭ ትራንስፖርት፦ የብስክሌት አጠቃቀምን ማዘውተር።
* አረንጓዴ ኢነርጂ፦ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት መጠቀም።
ይህ ወቅታዊ ችግር ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት እስክንመለስ ድረስ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #addisababa #fueleconomy #greentransport #ethiopia #energysaving #adanechabiebie
L

9 months ago
ደሴ : 5 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች 🚌⚡️
#ethiopia | የደሴ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማዘመንና ችግሩን ለመፍታት የገዛቸውን 5 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በዛሬው ዕለት ተረክቧል።
የአውቶቡሶቹ ፋይዳ፡-
✅ ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ያስቀራሉ።
✅ የአየር ንብረት ብክለትን በመቀነስ "አረንጓዴ ትራንስፖርት"ን ያበረታታሉ።
✅ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት በመቅረፍ ለነዋሪው እፎይታ ይሰጣሉ።
አውቶቡሶቹ በቅርቡ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ተሰማርተው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩም ተገልጿል።
#dessie #electricbus #greentransport #ethiopia #development

Comments