Logo
Getu Temesgen
በሰከንድ አንድ ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል የትራንስፖርት አማራጭ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | ይህንን አዲስ የክፍያ አማራጭ ወደ ዘርፉ ያስገባው ዘማይ የተባለው የግል ማህበር ነው።

ይህንን አማራጭ የሚፈልጉ ዜጎች ወደ 6312 የጥሪ ማዕከል በመደወል መገልገል ይችላሉ ነው የተባለው።

ማህበሩ "ዘማይ ጉዞ" እና "ዘማይ ብር " የተሰኙ ሁለት አገልግሎቶች ዛሬ በመስቀል አደባባይ ባከናወነው ስነስርአት ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ስራውን በ1,680 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ቁጥራቸውን ወደ 30,000 የማሳደግ ሰፊ እቅድ መያዙን ገልጿል።

​እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ በመሆናቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ ከመሆናቸውም በላይ ለሀገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ተብሏል።

​የጉዞ መነሻ ዋጋው 100 ብር ሆኖ በየኪሎሜትሩ ደግሞ 12 ብር በሚታሰብበት ዋጋ ለህብረተሰቡ አቅርቢያለሁ ብሏል።

​ከደህንነት አንጻርም አሽከርካሪዎቹ በቂ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ተሽከርካሪዎቹም ተሳፋሪዎች ንብረት ቢረሱ የሚጠቁም የደወል ምልክትና ገመድ አልባ የስልክ ቻርጀር የተገጠመላቸው ናቸው ተብሏል።

​የመኪናዎቹ ንጽህና በዘመናዊ የእንፋሎት እጥበት የሚከናወን በመሆኑ የኤሌክትሪክ አካላቶቻቸው ከውሃ ንክኪ ተጠብቀው እንዲቆዩ ያስችላል ተብላል።

​ከዚህ በተጨማሪም ዘማይ ብር የተሰኘው መተግበሪያ ከባንኮችና ከቴሌብር ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለደንበኞች የ20 በመቶ ቅናሽና ቀልጣፋ የክፍያ አማራጭን ይዞ መጥቷል።

​ድርጅቱ በሰከንድ አንድ ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 6312 የጥሪ ማዕከል በማቋቋም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ የስራ እድልና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#zemayguzo #zemaybirr #electricvehicles #ethiopia #digitaleconomy #greentransport #techinnovation #addisababa

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.