ከባንክ ሰልፍ ወደ አንድ ንክኪ፦ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እውነታዎች
**********************
ዛሬ መረጃ እና ገንዘብ ፍጥነታቸውን ጨምረው በእጅ ስልካችን ውስጥ የገቡበት ዘመን ላይ ደርሰናል።
በትናንቱ የወረቀት የገንዘብ ቁጠባ ደብተር እና በባንክ ቅርንጫፎች ረጅም ሰልፍ የምናውቃት ኢትዮጵያ፣ ዛሬ በአንድ ንክኪ ወደሚፈጸም ዘመናዊ የዲጂታል አሠራር ተሸጋግራለች።
ይህ ሽግግር የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የሀገርን የኢኮኖሚ ደኅንነት እና ነፃነት የማስከበር የ"ዲጂታል ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት" ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ ሀገራችን በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ አማካኝነት እያካሄደችው ያለው ይህ አብዮት የት ደረሰ?
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቴክኖሎጂን በመግዛት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሕዝብ፣ መንግሥት፣ ባንክ እና ቴሌኮም ተደምረው የሚፈጥሩት አዲስ ሀገራዊ አቅም ነው።
ቴሌብር ወይም የፋይዳ መታወቂያ ብቻቸውን የፋይናንስ ክፍተትን ሊሞሉ አይችሉም። ነገር ግን የፋይዳ መታወቂያ ከግብር ሥርዓቱ እና ከባንክ ጋር ሲተሳሰር የተሟላ የዲጂታል መሠረተ-ልማት ይሆናል።
ይህን መሠረት ይበልጥ ለማጠናከር የአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ኢንስቲትዩት መቋቋሙ እና አሁን ደግሞ የሰው ሠራሽ ዩኒቨርሲቲ በሂደት ላይ መሆኑ ሀገራችን በዕውቀት ላይ ለተመሠረተው የነገ ኢኮኖሚ እየተዘጋጀች መሆኗን በተጨባጭ ያሳያል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የ"5 ሚሊዮን ኮደሮች" የዘመቻ ሥልጠና ሀገራችንን ለነገው ተወዳዳሪነት እያበቃት ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን ከመጭበርበር እና ከደኅንነት ሥጋት ለመጠበቅ የ"ፋይዳ" ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሂሳብ ጋር ማገናኘትን ግዴታ ማድረጉ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን የቻሉ ሲሆን፣ የቁጥጥር ሥርዓቱም በጊዜ ገደብ እየተተገበረ ይገኛል።
በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ፣ ሐረሪ እና 25 ዋና ዋና ከተሞች የመጨረሻው የጊዜ ገደብ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የነበረ ሲሆን፣ ያላገናኙ ደንበኞች ላይ የወጪ እገዳ ተጥሏል።
በተቀሩት ከተሞች እና የገጠር ቅርንጫፎች ደግሞ የመጨረሻው የጊዜ ገደብ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ በተመሳሳይ የወጪ እገዳ ይጣልባቸዋል።
በውጭ ለሚኖሩ ዳያስፖራዎች ግን የ2 ዓመት ማቅለያ የተሰጣቸው በመሆኑ ጊዜያዊ እገዳ ሳይጣልባቸው መደበኛ ግብይት መቀጠል ይችላሉ።
በሌላ በኩል የቴሌኮም ዘርፉ ክፍት መደረግ እና የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት የቴሌኮም ሞኖፖልን በመስበር ጤናማ ውድድር ፈጥሯል።
ይህ ውድድር የ3G ኔትወርክ ሽፋንን በ50 በመቶ ሲያሳድግ፣ የ4G የሕዝብ ተደራሽነትን በ8 እጥፍ ማሳደግ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 87.1 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 49 ሚሊዮንን አልፏል።
የብሮድባንድ ኢንተርኔት ተደራሽነትም በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 20 በመቶ በታች አሁን ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታም 23 ሺህ 26 ኪሎ ሜትር ደርሷል።
ከዚህም በላይ የሀገራችን የሞባይል ክፍያ አካውንት በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 12.2 ሚሊዮን አሁን ወደ 139.5 ሚሊዮን አድጓል።
በዚህ ዘርፍ የዲጂታል ክፍያ ፈርቀዳጅ የሆነው ቴሌብር የደንበኞቹን ቁጥር 58.61 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን፣ በቴሌብር የተቀመጠው የጥቃቅን ቁጠባ መጠን 34.41 ቢሊዮን ብር ደርሶ ከመደበኛ ባንክ ውጭ ለነበሩ 16 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጥቃቅን ብድር ማድረስ ተችሏል።
ሳፋሪኮም በበኩሉ ኤም-ፔሳን (M-Pesa) ከኢትዮ ስዊች ጋር በማዋሃድ የደንበኞቹን ቁጥር ከ5.2 ሚሊዮን በላይ አድርሷል።
ይህን ዕመርታ በስትራቴጂ ለመምራት የወጣው የBRIDGE 2030 ዕቅድ ደግሞ እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ የዲጂታል ክፍያዎችን አጠቃላይ ዋጋ ከሀገራችን ጠቅላላ ምርት (GDP) አንፃር 750 በመቶ ለማድረስ አልሟል።
ኢኮኖሚውን ከጥቁር ገበያ አደጋ ለመታደግ እና የፍራንኮ ቫሉታ አሠራርን ግልጽ ለማድረግ በአዲሱ መመሪያ (FVD/01/2018 ዓ.ም) መሠረት ግዙፍ መዋቅራዊ ለውጥ ተደርጓል።
ማንኛውም የፍራንኮ ቫሉታ ግብይት ከግንቦት 2018 ዓ.ም ጀምሮ FEMoUS በተባለው የብሔራዊ ባንክ እና ጉምሩክ ኮሚሽን የተቀናጀ የዲጂታል ሥርዓት ውስጥ ማለፍ ግዴታ ሆኖ መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች እንዳይጠቀሙበት ተከልክሏል።
በዚህ አሠራር መሠረት የሐኪም ማዘዣ እና የጤና ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው ለሕክምና የሚሆኑ አስቸኳይ መድኃኒቶች ምንም የዋጋ ገደብ የሌላቸው ሲሆን፣ ለዳያስፖራዎች እና የውጭ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ፈቃድ እስከ 10 ሺህ ዶላር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚመጡ ዜጎች በነዋሪነት ፈቃድ እስከ 5 ሺህ ዶላር (ከቀረጥ ነፃ)፥ እንዲሁም ለንግድ ናሙናዎች ከሕጋዊ የንግድ ሥራ ጋር የሚያስተሳስር የጉምሩክ ሰነድ በማቅረብ እስከ 4 ሺህ ዶላር የገንዘብ ጣሪያ ተቀምጦባቸዋል።
በተጨማሪም መንግሥት ከብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) ጋር በመሆን 657 ሕገወጥ የባንክ ሂሳቦችን ያገደ ሲሆን፣ ሸጌ፣ አዱሊስ፣ ታጅ እና ረመዳ የተባሉ 4 ሕገወጥ የሐዋላ ድርጅቶች እንዲዘጉ አድርጓል።
ብሔራዊ የገንዘብ ሉዓላዊነትን ለማስከበር እንደ ባይናንስ (Binance) እና ሜክስክስሲ (MEXC) ያሉ የክሪፕቶ መገበያያ መድረኮች ከኢትዮጵያ ገበያ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ተደርጓል።
ይህ ደፋር እርምጃ የሀገር ውስጥ መረጃ ማከማቻ አሠራር ከመዘርጋቱ እና የዳታ ማስተላለፊያ ፍጥነት ከ500 ጊጋ ባይት በሰከንድ ወደ 3 ቴራ ባይት በሰከንድ ከፍ ካለበት ስኬት ጋር ተዳምሮ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመታደግ አስችሏል።
ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን በማገዝ የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ወደ 2.7 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል እና የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር የሚያስተምረን ትልቁ እውነት ቴክኖሎጂ በራሱ ብቻ ተዓምር እንደማያመጣ ነው።
እውነተኛ እና ዘላቂ ልማት የሚረጋገጠው ቴክኖሎጂ ከተቋማዊ ውህደት፣ ከሕግ ቁጥጥር እና ከሕዝብ ተሳትፎ ጋር በ"መደመር" ፍልስፍና ሲቀናጅ ብቻ ነው።
ይህ ቅንጅት በተሳካ ሁኔታ ሲቀጥል፣ ዲጂታል ኢኮኖሚው ሀገርን ወደ ብሔራዊ ብልጽግና የሚመራ እውነተኛ የልማት ጎዳና መሆኑ ይረጋገጣል።
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #digitaleconomy #banking #digitalfinance #digitalethiopia #ebc

4 days ago