4 months ago
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና ቢዩ ድሊቨሪ አብረው ለመስራት ተስማሙ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑት አንዱ የሆነው ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ግብይት አማራጭ የሆነው ቢዩ ድሊቨሪ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው እለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል።
ይህ ስምምነት በዋናነት የሞሐ ምርቶችን ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋትና ለደንበኞች ምቹ የሆነ ግብይትን ለመፍጠር ያለመ ነው።
የስምምነቱን ዝርዝር አስመልክቶ የሞሐ የለስላሳ መጠጦች የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ሰለሞን እንደገለጹት፣ ደንበኞች ከቢዩ ድሊቨሪ ምግብ በሚያዙበት ወቅት የፔፕሲ የፕላስቲክ ምርቶችን በቀላሉ በአንድ ላይ ማግኘት የሚችሉበትን ዕድል ይፈጥራል።
ሞሐ በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩኘ ስር መካተቱን ተከትሎ ባገኘው ጠንካራ የፋይናንስ አቅም፣ የማምረት ሂደቱ ምንም አይነት እክል ሳይገጥመው እየቀጠለ መሆኑን አቶ ንጉሱ ገልጸዋል።
ይህ የትብብር ስምምነት የንግድ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ፣ ከ3,500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረውን ቢዩ ድሊቨሪን አቅም በማሳደግ ረገድ የራሱ ድርሻ ይኖረዋል።
ስምምነቱ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የደንበኞችን ፍላጎት በቤትና በቢሮ ሆኖ ለማርካት ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #mohasoftdrinks #beudelivery #ethiopiabusiness #pepsiethiopia #digitaleconomy #medrocinvestmentgroup

Comments