2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ESL) ከ40 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገሪቱን የነዳጅ እና የፔትሮሊየም ምርቶች የማጓጓዝ ስራ በይፋ መጀመሩን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ካፒታል እንግሊዘኛው ጋዜጣ ዘግቧል። ይህ ታሪካዊ ጅምር ኢትዮጵያ ከሱዳን ነዳጅ ማስገባት ካቆመች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ (ከአህጉሪቱ) ሀገር ነዳጅ ያገኘችበትንም አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
በአሜሪካ በእስራኤል እና በኢራን መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በዓለም አቀፉ የነዳጅ መተላለፊያ ላይ የተፈጠረውን መስተጓጎል ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የነዳጅ ግዥ ስትራቴጂውን ወደ ምዕራብ እስያ እና ናይጄሪያ በማስፋት አማራጮችን ፈጥሯል። በዚህም መሰረት፣ በቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ ከሚተዳደረው የናይጄሪያው 'ዳንጎቴ ፔትሮሊየም ሪፋይነሪ' 120,000 ሜትሪክ ቶን የአቪዬሽን (የአውሮፕላን) እና የናፍጣ ነዳጅ በተሳካ ሁኔታ በ3 መርከቦች ወደ ጅቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል ተጓጉዟል። ከዚህ ውስጥ 80,000 ሜትሪክ ቶኑ የአውሮፕላን ነዳጅ ነው።
ባለፉት አራት አስርት ዓመታት የነዳጅ ማጓጓዝ ስራውን በብቸኝነት ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት (EPSE) ሲሆን፣ አሁን ግን መንግስት ዘርፉን ክፍት በማድረግ የግል ባለሀብቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ነዳጅ ማስገባት የሚችሉበትን መመሪያ አውጥቷል።
ኢትዮጵያ ነዳጅ የማታመርት በመሆኗ የገቢ ንግድ በጀቷን ሩብ ያህል ለነዳጅ የምታውል ሲሆን፣ በመጪው በጀት ዓመት የነዳጅ ወጪዋ እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለፓርላማው መግለጻቸውን በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል። መንግስት በያዘው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መሰረት፣ የነዳጅ ድጎማን ቀስ በቀስ ለመቀነስ በማቀድ በመጪው በጀት ዓመት ለዘርፉ 20 ቢሊዮን ብር ብቻ የድጎማ በጀት አቅርቧል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ቅናሽ ያሳየ ነው።

#የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ማግኘት፤ የሀገር በቀል ባንኮች ዕድልና ስጋት ምን ሊሆን ይችላል?
አዲስ ወደ ተመሠረተው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለመቀላቀል የመጀመርያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል (United Capital) ማግኘቱ ታውቋል።
ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ማግኘት፤ የሀገር በቀል ባንኮች ዕድልና ስጋት ምን ሊሆን ይችላል?
ይህ ታሪካዊ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግርና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ በር የሚከፍት ቢሆንም፣ ገና በማቆጥቆጥ ላይ ላሉት የሀገር ውስጥ ባንኮች የራሱ የሆነ ስጋት ይዞ ይመጣል።
ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ስድስት (6) ሀገር በቀል የኢንቨስትመንት ባንኮች ማለትም CBE Capital, Wegagen Capital, First Addis Investment Bank, Awash Capital, Siinqee Investment Bank እና Prime Capital ፈቃድ ወስደው ወደ ገበያው ለመግባት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ የዩናይትድ ካፒታልን መግባት ተከትሎ የባንኮቹ ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ብሏል።
የዚህ ልምድ ያለው የውጭ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀል በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መነቃቃት ላይ የራሱ የሆነ ሰፊ ጥቅምና ስጋት ይዞ እንደሚመጣ የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።
የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ መግባት ከሚሰጣቸው ቀዳሚ ጥቅሞች መካከል የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር (Knowledge Transfer) ዋናው ነው።
የኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ የረጅም ጊዜ ልምድና የዳበረ ቴክኖሎጂን የሚጠይቅ ሲሆን፣ ዩናይትድ ካፒታል በአፍሪካ የቦንድ እትም እና በሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (IPO) ላይ የቆየ ልምድ ያለው በመሆኑ ገበያው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል።
ለምሳሌ ያህል፣ እንደ የኢትዮጵያ ቴሌኮም ያሉ ግዙፍ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አክሲዮኖቻቸውን ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ ለመሸጥ (IPO) በሚዘጋጁበት ጊዜ፣ ባንኩ ያለውን ዘመናዊ የዋጋ ትመና እና የቴክኖሎጂ አደረጃጀት በመጠቀም ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
በተጨማሪም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና የውጭ ምንዛሬን በመሳብ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል።
የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች ከዓለም አቀፍ ባለሀብቶችና የፈንድ አደራጆች ጋር ሰፊ ትስስር አላቸው።
በሌላ በኩል፣ ይህ ሂደት ሊከተሉ የሚችሉ ዋና ዋና ስጋቶችንም የደቀነ ነው። የመጀመሪያው የሀገር በቀል ባንኮች በገበያው የመዋጥ ስጋት (Infant Industry Threat) ነው።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ገና በጅምር ላይ ያለና ፈቃድ የወሰዱት ስድስቱ የሀገር ውስጥ ባንኮች ገና በተግባር ያልተፈተኑ ድርጅቶች በመሆናቸው፣ ትልቅ ካፒታልና ሰፊ የሰው ኃይል ያለው የውጭ ባንክ ሲገባ ገበያውን የመጠቅለል ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
ባጠቃላይ የዩናይትድ ካፒታል መግባት የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ በአቋራጭ መንገድ በፍጥነት እንዲያድግና ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ የሚያደርግ ቢሆንም፣ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ህልውና አደጋ ላይ እንዳይጥል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) የሀገር ውስጥ ባንኮች ተወዳዳሪ ሆነው እስኪያድጉ ድረስ የተወሰኑ ትልልቅ የሀገር ውስጥ ሥራዎች በጋራ (Joint Venture) እንዲሠሩ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ፣ ተገቢውን የቁጥጥርና የጥበቃ ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት የዘርፉ ተንታኞች በማሳሰብ ላይ ናቸው።
ይህንን ዘገባ ስናዘጋጅ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ያወጣቸውን የሕግ ማዕቀፎች እና መመሪያዎች ተጠቅመናል። በተጨማሪም መሰል የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች ወደ ታዳጊ ሀገራት ገበያ ሲገቡ የሚኖራቸውን ጥቅምና ስጋት፣ በተለይም በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የታዩትን ተጨባጭ ተሞክሮዎችና የፋይናንስ ዘርፍ መርሆዎች መሠረት በማድረግ ዘገባው ተዘጋጅቷል፡፡
Seledadotio

የናይጀሪያ ባንክ ኢትዮጵያ ገባ‼
ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን ፈቃድ አገኘ
በአፍሪካ ግዙፍ የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ የሆነው የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል (United Capital Plc) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ አግኝቷል።
ይህ ስኬት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም አካል የሆነው የፋይናንስ ሊበራላይዜሽን (Financial liberalization) ትግበራ ውጤት ሲሆን፣ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ገበያ ክፍት በማድረግ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ እየተሰሩ ካሉ ሰፋፊ የፖሊሲና የሕግ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ ነው።

3 months ago
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የሀብት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ በሀብታቸው ላይ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገባቸው ተሰማ።
እንደ ብሉምበርግ የቢሊየነሮች መረጃ መሠረት፣ የዳንጎቴ ጠቅላላ የሀብት መጠን ወደ 34.0 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።
ይህ የሀብት ዝላይ በፈረንጆቹ 2026 ዓመት ውስጥ ብቻ 3.99 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ እንዲያገኙ ያስቻላቸው ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥም ወደ 69ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል።
ምንም እንኳን ሌሎች አፍሪካውያን ቢሊየነሮች በዓመቱ ውስጥ ያስመዘገቡት የትርፍ ዕድገት መጠን ከእሳቸው ቢበልጥም፣ ዳንጎቴ አሁንም የአህጉሪቱን ቀዳሚነት በሰፊ ልዩነት እንደያዙ ቀጥለዋል።
ከዚህ የሀብት እድገት ጋር ተያይዞ በሌጎስ የሚገኘው የናይጄሪያው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ የጄት ነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ የተዘገበ ሲሆን፣ ይህም ከአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ ጋር ያለውን የኢነርጂ ትስስር አጠናክሮታል።
ማጣሪያው በቀን 650,000 በርሜል የማምረት ሙሉ አቅሙን እየተጠቀመ ሲሆን፣ የጄት ነዳጅ ኤክስፖርትም በቀን ወደ 158,000 በርሜል ከፍ ብሏል። በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በተፈጠረው የአቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ለነዳጁ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።(ካፒታል ኢትዮጵያ)
seledadotio

5 months ago
♦️በናይጄሪያ ካላባር የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ንጋት ላይ ይገባል
♦️አትሌቶቹ ውጤታማ ቢሆኑም ሚኒማ ማሟላት አልቻሉም
♦️ቡድኑ ከ27 ሠዓታት በላይ በመጓዝ በጉዞ ተንገላቷል፤በመርከብ ሳይቀር ተጉዘው በቀጥታ ስታዲየም ገብተዋል
♦️እኩለሊት ተነስቶ ንጋት ላይ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል
#ethiopia | በቦትስዋና ጋቦሮኒ ከሜይ 2-3/2026 ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሪሌ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የሚረዳ ስዓት ለማስመዝገብ ወደ ናይጄሪያ ካላባር ተጉዞ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኃላ ከሌጎስ ተነስቶ ንጋት ላይ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ።
ቡድኑ በአሁን ሠዓት የውድድሩ ስፍራ ከነበረችው ካላባር ትናንት ወደ ሌጎስ በመምጣት ኤክሴል ሆቴል አርፈው ለጉዞ እየተዘጋጀ ሲሆን በናይጄሪያዊያን ሠዓት ዛሬ ምሽት 4:00 በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር ደግሞ ከሌሊቱ 6:00 ከሌጎስ ተነስቶ 5:20 አካባቢ የሚጠጋ ሠዓት ከበረረ በኃላ ንጋት ላይ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
♦️ውጤታማ ቢሆኑም ሚኒማ ማሟላት አልቻሉም
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ የልዑካን ቡድኑ ወደ ናይጄሪያ ካላባር የተጓዘው ከቦትስዋና 60ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ጋር አብሮ በሚካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሪሌ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ሚኒማ ለማሟላት ሲሆን አትሌቶቻችን በውድድሩ ውጤታማ ቢሆኑም፣ልምድ የሚያገኙበት ዕድል ቢመቻችላቸውም ቦትስዋና ለምታዘጋጀው የአለም ፈጣን እግሮች ትንቅንቅ መሳተፍ የሚያስችለውን ሚኒማ ግን አንዳቸውም ማስመዝገብ አልቻሉም።
የአጭር ርቀት ስፔሺያሊስቶችን የያዘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በካላባር በነበረው ቆይታ በ4X400 ሜትር ሪሌ በሴቶች 2ኛ ፣በወንዶች ደግሞ 3ኛ ደረጃን በአጠቃላይ በ400 ሜትር ወርቅ፣በ400 ሜትር ሴቶች ብር እና በ 400 ሜትር ወንዶች ነሃስ፣
በድብልቅ ሪሌ ውድድር አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ጥሩ በሚባል ደረጃ ቢያጠናቅቁም አንዳቸውም ለቦትስዋናው ጋቦሮኒ የሚያሳትፋቸውን ትኬት መቁረጥ የሚያስችል ሚኒማ ግን ማሟላት ሳይችሉ ነው ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱት።
♦️ፌዴሬሽኑ ጥሩ ስራ ቢሠራም ከወቀሳ አይድንም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በተለይ ፕሬዝዳንቱ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በጀት ከመመደብ አንስቶ አትሌቶቹ ሚኒማ የሚያመጡበትን የናይጄሪያውን የውድድር እድል እንዲያገኙ ውድድሩን ከሚያዘጋጀው አካል ጋር ግንኙነት በመፍጠር ዕድሉ እንዲሳካ ያደረገው ጥረት በእጅጉ የሚያስመሠግነው ቢሆንም ነገሮች በጥድፊያ የተሞሉ መሆናቸው፣አትሌቶች በሆቴል ለአንድ ሳምንት እንኳን ተሠባስበው በቂ ልምምድ ሳያደርጉ ለአንድ ቀን ሆቴል ገብተው በነጋታው ለውድድር መጓዛቸው ፌዴሬሽኑን በተለይ ይሄን የማመቻቸት ኃላፊነት ያለበትን ፅ/ቤቱን ያስወቅሳል።
♦️ ከ27 ሠዓታት አድካሚ ጉዞ በኃላ ካላባር
ከሁሉም በላይ እጅግ አስገራሚው ነገር የልዑካን ቡድኑ ውድድሩ የሚካሄድባት ካላባር ለመድረስ ከ27 ሠዓታት በላይ የፈጀበት ከመሆኑም በላይ ከአውሮፕላን አድካሚ ጉዞ እንደገና የመርከብ አድካሚ ጉዞ አድርጎ ያለአንዳች እረፍት ከመርከብ ወደ ስታዲየም እንዲያመራ የተደረገበት መንገድ የፌዴሬሽኑን የጉዞ ዕቅድ ለትችት አሳልፎ የሚሠጥ ነው።
ሚኒማ ማምጣት ግቡና ዕቅዱ አድርጎ ወደ ናይጄሪያ የተጓዘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በፅ/ቤቱ አስቀድሞ የጉዞ ዝግጅት ባለማድረጉ ከአዲስ አበባ ሌጎስ፣ከሌጎስ ቀጥታ ወደ ካላባር ጉዞ ለማድረግ ዕቅድ ቢይዝም በዕለቱ ፍላይት(በረራ)የለም በመባሉ ቡድኑ ያለ ዕቅዱ ኦሮ የምትባል ትንሽ ከተማ ለማረፍ ተገዷል፤ከኦሮ ከተማ ወደ ካላባር ለመጓዝ በረራ ባለመኖሩ ቡድኑ እንደገና እንደቱሪስት አድካሚ የመርከብ ጉዞ አድርጎ ከመርከብ በቀጥታ ወደ ስታዲየም ለመግባት የተገደዱበት ሁኔታ እንደነበር ነው የካላባር የመረጃ ምንጮቻችን የገለፁልን፤በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የውድድሩ ስፍራ ከ27 ሠዓታት በላይ ጊዜን እንክት አድርጎ በመብላቱ የልዑካን ቡድኑን ለከፍተኛ ድካምና መንገላታት ዳርጎታል።
♦️የናይጄሪያዊው የቡድኑ ኮርዲኔተር ትልቅ ድጋፍ
ይህ አድካሚ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ እንዳይደገም ከፌዴሬሽኑ በላይ ጆን የሚባለው የናይጄሪያ ፌዴሬሽን ሠራተኛና የቡድኑ ኮርዲኔተር ትልቅ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ነው የሠማነው፤በእሱ ድጋፍም የነገ የርቀቱ የሀገር ተስፋ የሆነው የአትሌት መርዶኪዮስ ወልዴ የውድድር ቀንን በጉዞ በመንገላታቱ ምክንያት እስከማስቀየር የደረሠ ትልቅ ስራን የሠራ ሲሆን ቡድኑ ወደ ናይጄሪያ ሲጓዝ የገጠመው አይነት ረዥም ጉዞ አድርጎ እንዳይንገላታ በማሠብ ትናንት ከካላባር ተነስተው ወደ ሌጎስ ገብተው ደረጃውን በጠበቀው ኤክሴል ሆቴል እንዲያድሩና ዛሬ እኩለሊት ተነስተው ንጋት ላይ አዲስ አበባ እንዲገቡ ትልቅ ሚና በመጫወቱ ሁሉም የቡድኑ አባላት አመስግነውታል ናይጄሪያዊውን ጆንን።
♦️የጉዞ መንገላታት፣ከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ፣የትራኩ ምቹ አለመሆን የሚኒማ እንቅፋት
የናይጄሪያው ውድድር በጉዞ መንገላታት፣በከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ የታጀበ መሆኑ እንዲሁም ትራኩ የጭቃ ያህል የሚጣበቅና ለስፓይክ አመቺ ባለመሆኑ አትሌቶቻችን ያሠቡትን ያህል ውጤታማ እንዳይሆኑ የራሱን እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ነው መረዳት የቻለው።
ከዚህ ከጉዞ ጋር በተያያዘ ፌዴሬሽኑ አሁንም ከወቀሳ አልዳነም ለአትሌቶቹ ሚሊየን ብሮችን መድቦ ውድድሮችን አመቻችቶ መላኩ የሚያስመሠግነው ቢሆንም በቪዛ ጉዳይ ከአሜሪካው ችግር አሁንም እንዳልተማረበት ነው እየደረሱን ያሉት መረጃዎች የሚጠቁሙት።
ከናይጄሪያው የጉዞ ችግር በተጨማሪ በፖላንዱ ጉዞ የቪዛ ጉዳይ ዙሪያም መረጃዎች በስልክ እየደረሱን ነው፤ምንድነው የተፈጠረው?በቀጣይ ትክክለኛውን መረጃ አጠናክረን ለህዝብ የምናደርስ ይሆናል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
👉ፎቶ ክሬዲት:የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ

Sponsored by
Surafel
5 months ago
AFG አቪዬሽን አየርላንድ
#ethiopia | በአውሮፕላን ንግድና ሀብት አስተዳደር የሚታወቀው ኤ ኤፍ ጂ ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) እህት ባንያ የሆነው ኤ ኤፍ ጂ አቪየሺን አየርላንድ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ሀገራት መግባቱን ተናገረ
ኩባንያው ለአፍሪካ ስራው ሲልም ሁለት ከፍተኛ ባለሞያዎቹን በአፍሪካ ተገኝተው እንዲሰሩ እንደመደባቸው ባወጣው መግለጫ ተናግሯል ።
AFG አቪዬሽን አየርላንድ የናይጄሪያው ካሊ ኤር ሁለት CRJ1000 አውሮፕላኖች ባለቤት እንዲሆን ማስቻሉን ተናግሯል ።
በዚህም የተነሳ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች፣አፕሬተሮች፣የመንግሥት እና የአቪዬሽን ዘርፍ ሀላፊዎች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ተረድቻለሁ ብሏል።
ይህ ፍላጎት የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ መምጣቱን ያሳል ሲልም ኩባንያው ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።
የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ ፍላጎትን ለሟሟላትም AFG አቪዬሽን አየርላንድ ሁለት ከፍተኛ ባለሞያዎቹን ወደ አፍሪካ በመላክ ከዘርፉ ተዋኒያን ጋር እንዲገናኙና እንዲሰሩ እንዳደረገ ተናግሯል ።
በዚህም የኩባንያው የቢዝነስ አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ክርስቲያን ሃትጄ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና ዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት ሺኤኩማ ጌማዴ ተመድበዋል ተብሏል።
ሁለቱ ከፍተኛ ባለሞያዎች በአውሮፕላን ንግድ፣ሊዝ፣ፋይናንስ፣በአየር መንገድ የንግድ ስትራቴጂ እና የበረራ መዳረሻዎች ማስፉት ላይ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ እንደሆኑ ኩባንያው በመግለጫው ጠቅሷል።
ሁለቱ ባለሞያዎች በመጪዎቹ ወራት በአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ በአቪዬሽን ዘርፍ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር በቀጥታ ውይይት ለማድረግ ማሰባቸውም ተጠቅሷል።
የንግድ አውሮፕላኖች ግዢና ምደባ፣የግል ጄት ግብይትና የመዋቅር ስራ፣የፋይናንስ ሊዝ መፍትሔዎች ፣የበረራ ማዘመን ስትራቴጂ ፣የማማከር አገልግሎት ኩባንያው ከሚሰራዎች ስራዎች መካከል መሆናቸው ተነግሯል ።
"በአለም ላይ ከፍተኛ የአቪዬሽን እድገት እየታየባቸው ካሉት ውስጥ አፍሪካ ምሳሌ ናት "ያሉት በኩባንያውን የአፍሪካ ስራ ለመምራት የተመደቡት ክርስቲያን ሃትጄ "እያየነው ያለውነው የተሳትፎ መጠን በአፍሪካ በአካል ተገኝተን ሁኔታዎችን ለማጤንና ዘላቂነት ያለው ትብብር ለመመስረት ያግዘናል" ብለዋል።
"በአፍሪካ ያየነው የትብብር ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው።በአህጉሪቱ ዘላቂ የአቪዬሽን ልማት ለመደገፍ፣የምክር አገልግሎት ለመስጠት፣በግል አቪዬሽን እና ተያያዥ ዘርፎች የኩባንያውን የካበተ ልምድ ይዘን ወደ አፍሪካ ተቀላቅለናል ሲሉ "ሺኤኩማ ጌማዴ ተናግረዋል ።
በአፍሪካ አቪዬሽን ገበያ መግባቱን የተናገረው AFG አቪዬሽን አየርላንድ "ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) ኩባንያ እህት ኩባንያ ነው።
AFG በአለም ላይ በአውሮፕላን ንግድ እና ሀብት አስተዳደር የሚታወቅ ኩባንያ ነው።

6 months ago
የክብር ቀብር፦ በታምራት ደስታ "ከአንቺ አይበልጥም" ውስጥ በፍቅር ሰንሰለት የታሰረው የነፍስ ጩኸት
ለዚህ ዘፈን መነሻ ነው የተባለ ታሪክ ነው። ከሆነ አመት በፊት አንዲህ ሆነ። በአዲስ አበባ የሰው ድምፅ በሚበዛባቸው ምግብ ቤቶች መካከል አንድ የምግብና መጠጥ ቤት ባለቤት የሆነ ሰው፣ ሕይወቱንና ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ክብሩንም ለሚስቱ አሳልፎ ሰጥቷል። ሚስቱ በሰው ፊት ስትጎነተል፣ ከሌሎች ጋር ስትላፋና እንዲያውም "እንሶላ ትጋፈፋለች" ተብሎ በሚወራበት ሁኔታ ውስጥ፣ እሱ ግን ምርጫው ሆዱ እያረረ ዝምታ ሆነ።
አንድ ቀን ሆድ ሲከፋው ተጣላት ። ግን ፍቅሯ አገረሸብኝ ብሎ በሽማግሌ ቢመልሳትም፣ ድርጊቷ አልታረመም። በመጨረሻም ይህ ሰው "ካንቺ አይበልጥም ክብሬ" ብሎ ራሱን ለውርደት አሳልፎ ሰጠ።
ይህ ዝምታ ግን የትዕግስት ሳይሆን፣ የማንነት መፈራረስ ምልክት ነው። ታምራት ደስታ በዜማው እንዳቀነቀነው፣ ይህ ሰው ክብሩን እንደ አሮጌ ልብስ አውልቆ ጥሏል። ለምን? ምክንያቱም ከብቸኝነት ይልቅ ውርደት ይቀልለዋልና። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ፍርሃት "ብቻን መቅረት" ነው። ይህ ባል ሚስቱን ለብቻው ሳይሆን ከህዝብ ጋር ይጋራታል።
እሷ በሰው ፊት ክብሩን ስትገፈው፣ እሱ ግን ውስጡ እያረረ "ይሁን" ይላል። ይህ ውሳኔ ከፍቅር የሚመነጭ ሳይሆን፣ ራስን ካለመቀበል የሚመጣ የባርነት ጽዋ ነው። ራሱን እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ቁስ (Object) እየቆጠረ፣ የሰዎችን ትዝብትና ንቃትን ዋጥ አድርጎ ለመኖር መወሰኑ፣ የሰብአዊነቱ ማብቂያ ደወል ነው።
ፈላስፎች "ገሃነም ማለት ሌሎች ሰዎች ናቸው" ይላሉ። ለዚህ ባል ግን፣ ገሃነም የሚስቱ መሄድ እንጂ የሰዎች ትዝብት አይደለም። በሰው ፊት ስትላፋ፣ ሌላው ሲዳብሳት እያየ "ክብሬን ተውት" አለ።
ለእሱ ገሃነም የሚጀምረው እሷ የቤትዋን በር ዘግታ ስትወጣ ነው። የሰዎች አይን እንደ ሾህ ቢወጋውም፣ የእሷ አለመኖር ግን እንደ ሞት ይከብደዋል። "ካንቺ አይበልጥም" የሚለው ቃል፣ የፍቅር መገለጫ ሳይሆን የነፍስ ባርነት መግለጫ ነው። ነፃነት የሌለው ፍቅር ደግሞ ፍቅር ሳይሆን እስራት ነው።
እዚህ ጋር ፍቅረኛው ወህኒ ቤት ሆናለች፣ እሱ ደግሞ በገዛ ፈቃዱ ቁልፉን የዋጠ ዘበኛ ነው።
የናይጄሪያው ደራሲ ቺኑዋ አቼቤ በታላቅ ስራው Things Fall Apart ላይ፣ ወንድ ልጅ ክብሩ ሲነካ የሚሰማውን መርዶ ይገልጻል። በዚህ ግጥም ውስጥ ግን "ነገሮች አልተበተኑም" ። ይልቁንም በውርደት ውስጥ ተለጥፈው እንዲቆዩ ተደርጓል።
ባለታሪኩ የባህልን አጥር ሰብሮ፣ የወንድነትን ካባ አውልቆ፣ በባዶነቱ ፊት ቆሟል። "የት አባቱ ክብሬ" ሲል፣ የዘመናት ባህልንና የቤተሰብን ስም አቃጥሎ አመዱን ለንፋስ ሰጥቶታል።
አቼቤ እንደሚለው ባህል ሲፈርስ ህዝብ ይበተናል፤ እዚህ ግን ግለሰቡ ሲፈርስ ክብሩ ይበተናል። ይህ ሰው የቆመው በባዶ መሬት ላይ ሳይሆን፣ በራሱ ማንነት ፍርስራሽ ላይ ነው።
ግጥሙ "የማየውና የምሰማው ክብሬን ይነካኛል" በማለት ይጀምራል። ይህ ማለት ሰውየው ድንዛዜ ውስጥ አይደለም፤ ህመሙ ይሰማዋል። የሚስቱ እጅ በሌላ ሰው ትከሻ ላይ ሲያርፍ፣ ልቡ እንደ መስታወት እንደሚሰበር ያውቃል። ነገር ግን ሰባሪዋን ሴት ከመጥላት ይልቅ፣ የተሰበረውን ማንነቱን ይዞ ሊለምናት ይመርጣል።
ይህ አስለቃሽ እውነት ነው—አንድ ሰው ራሱን ማክበር ሲያቅተው፣ የሚሰጠው ፍቅር ሁሉ የውርደት ውጤት ይሆናል። ሕመሙን እያወቀው ወደ ሕመሙ መሮጥ፣ የሥነ-ልቦና ራስን የማጥፋት ተግባር ነው።
እያንዳንዱ ስንኝ የልብ ትርታ ሳይሆን የቁስል አቃቂር ነው።
ይህ ባል የቆሰለ ትዳሩን በውርደት ተሸክሞ በየቀኑ ወደ ምግብ ቤቱ ይሄዳል። ሚስቱ ስታዋርደው ድንጋዩ ይንከባለላል፤ እሱ ግን ደግሞ "ካንቺ አይበልጥም" እያለ ድንጋዩን ለመጫን ይሮጣል።
ይህ ትርጉም አልባ ህይወት በኢትዮጵያዊው ይሉኝታ ውስጥ ሲያልፍ፣ ታሪኩን እጅግ መራራ ያደርገዋል። የዚህ ሰው ድንጋይ የሚወደው ሰው ክህደት ነው። በየቀኑ የሚደገም ውርደት፣ በየቀኑ የሚታደስ መሸነፍ።
"ፈጣሪዬ አቅሜን ያውቃል ላልችል አልሰጠኝም" የሚለው ስንኝ፣ የግጥሙ እጅግ ልብ ሰባሪ ክፍል ነው። እዚህ ጋር ግለሰቡ መለኮታዊ ኃይልን ለውርደቱ ምስክር ያደርገዋል።
እግዚአብሔር የሰጠው አቅም "ክፋትን የመቋቋም" ሳይሆን "ውርደትን የመቻል" ይመስል ይናገራል። ይህ የሀይማኖታዊ እይታ ስህተት ሳይሆን፣ የግለሰቡ ተስፋ መቁረጥ የመጨረሻ ደረጃ ነው። መሸከም የማይገባውን ቀንበር፣ የፈጣሪ ፈቃድ አድርጎ መውሰዱ የሞራል ሞቱን ያፋጥነዋል።
ፈጣሪ ነፃነትን ሰጥቶት ሳለ፣ እሱ ግን ባርነትን የፈጣሪ ስጦታ አድርጎ መቁጠሩ የነፍስ ጨለማ ነው።
በናይጄሪያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ የሚታወቀው ወሌ ሶይንካ፣ "በአምባገነን ፊት ዝም የሚል ሰው በቁሙ የሞተ ነው" ይላል። እዚህ ጋር አምባገነኑ ፖለቲከኛ ሳይሆን "ፍቅር" ነው። ይህ ባል በፍቅር ስም የሚፈጸምበትን ግፍ ዝም ብሎ ሲቀበል፣ በቁሙ እየሞተ ያለ በድን ሆኗል።
"ሄደሽብኝ ከምሰቃይ ችላለሁ ቢያመኝም" የሚለው ቃል፣ በብቸኝነት ጨለማ ውስጥ ከመኖር፣ በውርደት ብርሃን ውስጥ መቃጠልን እንደሚመርጥ ያሳያል። ሞት አንድ ጊዜ ነው፤ ውርደት ግን በየቀኑ የሚሞቱት ሞት ነው። እሱ ግን የዘላለም ሞትን መርጧል።
ግጥሙ "ክብሬን አይል ያፈቀረ የተሸነፈ ሰው" ሲል የሽንፈትን አዋጅ ያውጃል። ፍቅር ድል መሆን ነበረበት፤ እዚህ ግን ፍቅር መሸነፍ ሆኗል። "የተሸነፈ ሰው" ለራሱ የሚሆን ትርፍ የለውም።
ለራሱ የማይራራ ሰው፣ ለክብሩ አይቆምም። ይህ ስንኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንባ ያፈስሳል። ምክንያቱም ብዙዎች በዝምታ የሚሰቃዩበትን፣ ለፍቅር ሲሉ ማንነታቸውን ያጡበትን ድበቅ ህይወት ይገልጻልና። ሽንፈቱ ከሚስቱ ጋር ሳይሆን ከገዛ ራሱ ህሊና ጋር ነው። ራሱን ድል ያደረገ ሰው ብቻ ነው ለክብሩ የሚሞተው፤ እሱ ግን በራሱ ተሸንፏል።
ታሪኩ በአዲስ አበባ ምግብ ቤት ውስጥ መከሰቱ፣ ማህበራዊ ትዝብቱን ያጠነክረዋል። ሰዎች "እንዴ ባሏን እንኳን አትፈራም?" ብለው ሲጠይቁ፣ መልሱ "ባሏ ራሱን አይፈራም" የሚል ነው። ራሱን የማያከብር ሰው፣ ሌላው እንዲያከብረው ሊጠይቅ አይችልም።
የሚስቱ ድፍረት የመነጨው ከእሱ ደካማነት ሳይሆን፣ እሷን ለማጣት ካለው ከፍተኛ ስጋት ነው። ይህ ስጋት ደግሞ እንደ ካንሰር ውስጡን እየበላው፣ የውጭውን ስሙን አርክሶታል።
"ካንቺ አይበልጥም ክብሬ ክብሬ" የሚለው መደምደሚያ፣ የአንድን ሰው ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ያሳያል። ግጥሙ ሲያልቅ የሚቀረው ዜማ ሳይሆን፣ የክብር የቀብር ስነ-ስርዓት ነው።
በሞት የተለየን ታምራት ደስታ ይህንን ሲዘፍን፣ የአንድን ግለሰብ ታሪክ ሳይሆን፣ የብዙዎችን ስውር ስቃይ ነው ያወጣው። "ክብሬ" የሚለው ቃል ደጋግሞ ሲነሳ፣ ትርጉሙ እየጠፋ ይሄድና "ባዶነት" ብቻ ሆኖ ይረፋል።
ይህ ነው እንግዲህ ፍቅር ከክብር በላይ ሲሆን የሚመጣው አሳዛኝ ፍጻሜ። የሰው ልጅ ያለ ፍቅር ሊኖር ይችላል፣ ያለ ክብር ግን መኖር አይችልም—ቢኖርም ጥላ ሆኖ ነው።
ፍቅር መስዋዕትነትን ይጠይቃል ይባላል፣ ነገር ግን መስዋዕቱ የሰውየው ክብር ሲሆን፣ መለኮታዊነቱ ቀርቶ ሰይጣናዊ እስራት ይሆናል።
ክብር አንዴ ከተቀበረ ትንሳኤ የለውም። ታሪኩም ሆነ ዜማው የሚያስተምሩን መራራ እውነት ቢኖር፡- ለሌላው ክብር ስንል የገዛ ክብራችንን የምንቀብር ከሆነ፣ የምንኖረው ሕይወት የራሳችን ሳይሆን የገዳያችን ነው የሚል ነው።

7 months ago
የሜንዲ ፎጣ፦ ከዋንጫው በላይ የታደነችው ብርቅዬ ንብረት
በካዛብላንካ ስታዲየም ውስጥ የነበረው ድባብ ከእግር ኳስ ጨዋታ ይልቅ፣ የጠፋ ንብረትን ለማስመለስ የሚደረግ የፖሊስ ፍለጋ ይመስል ነበር። ጨዋታው እንደተጀመረ የሞሮኮው አጥቂ ብራሂም ዲያዝ ወደ ሰኔጋል ጎል ሲቃረብ፣ የስታዲየሙ ደጋፊዎች አይን ኳሱ ላይ ሳይሆን ጎሉ ውስጥ በተሰቀለው ፎጣ ላይ ነበር።
ሞሮኮዎች በልባቸው "ሜንዲ ጎል እንዳይገባበት ያደረገው ግርግዳ ሳይሆን፣ ይሄ ፎጣ ውስጥ ያለው ድግምት ነው" ብለው አምነዋል።
በጨዋታው አጋማሽ ላይ አንዱ የኳስ አቀባይ ህጻን፣ ልክ እንደ 'ሚሽን ኢምፖሲብል' ተዋናይ በረኛው ሜንዲ ፊቱን ለማየት ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲዞር በዝግታ ተንፏቆ መጣ። ልክ ፎጣውን ነክቶ ሊፈረጥጥ ሲል ግን፣ ያልታሰበ አደጋ ገጠመው። የሰኔጋል ተጠባባቂ በረኛ ዬቫን ዲዩፍ፣ ልክ እንደ አፍሪካ አንበሳ ከሞቅታው መንንጭቶ በመነሳት ህጻኑን አየር ላይ አቆመው።
"ወዴት ነው የምትወስደው?" የሚል ይመስላል የዲዩፍ አይን። ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ጨዋታው በሁለት ተከፈለ። ሜዳው ውስጥ ሜንዲ ኳስ ይከላከላል፤ ከሜዳ ውጭ ደግሞ ዲዩፍ ፎጣውን ይከላከላል። ዬቫን ዲዩፍ በዛ እለት ከሰኔጋል መከላከያ ሰራዊት በበለጠ ንቁ ነበር። ፎጣውን አጥፎ ደረቱ ላይ አጣብቆ ይዞት፣ ማንም እንዳይነካው እንደ ውድ ሀብት ይጠብቀው ጀመር።
ሞሮኮዎች ስልታቸውን ቀየሩ። አሽራፍ ሀኪሚ ሳይቀር ወደ መስመር መጥቶ "እባክህ ፊቴን ልጥረግበት" በሚል የሽንገላ ጥያቄ አቀረበ። ዲዩፍ ግን "ይህ ፎጣ የሰኔጋል ብሄራዊ ክብር ነው፤ በላቡ ካልሆነ በስተቀር በሞሮኮ እጅ አይነካም" የሚል በሚመስል ጽናት ፊቱን አዞረበት።
ሁኔታው ያስቃቸው የነበሩት የናይጄሪያው በረኛ ንዋባሊ ደጋፊዎች ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያ "ፎጣው ድግምት የለውም፣ ሞሮኮዎች ግን ሳሙና ስለሌላቸው ሊሰርቁት ነው" እያሉ ይቀልዱ ነበር።
በመጨረሻም ሰኔጋል 1 ለ 0 አሸንፋ ዋንጫውን ስትቀዳጅ፣ ዲዩፍ ዋንጫውን ለመቀበል ሲሄድ ፎጣውን አልጣለውም ነበር። እንዲያውም በድል ማግስት ዲዩፍ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የሜዳሊያውን እና የፎጣውን ፎቶ ለጥፎ "ለፎጣው ብዬ የተጋደልኩትን ያህል ለዋንጫው አልተጋደልኩም" የሚል መልዕክት አስተላልፏል።
አሁን ላይ በሞሮኮ ገበያ ውስጥ "የሜንዲ ፎጣ" የሚሉ ሀሰተኛ ፎጣዎች በውድ ዋጋ እየተሸጡ እንደሆነ ይነገራል፤ ትክክለኛው ፎጣ ግን በሰኔጋል ቤተ-መዘክር ውስጥ "ሞሮኮን ያስለቀሰችው ጨርቅ" ተብሎ ሊቀመጥ ጥቂት ቀርቶታል።

የራባት ሌሊት፦ የደም ስር ትርታ
የነፋሱ ሹክሽክታ
ጥር 6, 2018 ከምሽቱ 5:00 ሰአት ።ብዙ ኢትዮጵያዊ በእንቅልፍ ላይ ነው ።ሞሮኮ ላይ አንድ ከባድ የኳስ ግጥሚያ ጀምሯል።
የራባት ምሽት ብርዳማ ቢሆንም፣ በልዑል ሞውላይ አብደላህ ስታዲየም ውስጥ ያለው ድባብ ግን የጋለ እሳት ነበር። ስልሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ስምንት ነፍሳት ስታዲየሙን ሞልተውታል። አየሩ በጭስ፣ በባንዲራዎች ሽውሽውታና በከበሮ ድምፅ ተሞልቷል።
በመልበሻ ክፍል ውስጥ ዋሊድ ረግራጉ የቡድኑን አባላት ትኩር ብሎ ተመለከተ። በ2004 ተጫዋች ሆኖ የፍጻሜውን ዋንጫ ሲያጣ የተሰማው ቁስል ዛሬም በልቡ ውስጥ አለ። "ዛሬ ታሪክ ራሱን አይደግምም፣ ዛሬ ታሪክን አዲስ አድርገን እንጽፋለን" አላቸው።
በሌላ በኩል የናይጄሪያው አሰልጣኝ ኤሪክ ሼል ከዋክብቱን—ቪክቶር ኦሲሜንን፣ ሉክማንንና ቹኩዌዜን—ይዞ የሞሮኮን ኩራት ለመስበር ቆርጦ ተነስቷል።
የ90 ደቂቃው ትግል
ጨዋታው ሲጀመር የሞሮኮው ብራሂም ዲያዝ ልክ እንደ አስማተኛ ኳሷን እግሩ ስር አጣበቃት። እያንዳንዱ ንክኪው ስታዲየሙን ያስጮኻል። አሽራፍ ሀኪሚ ከመስመር ወደ መስመር እንደ መብረቅ ይመላለሳል። ሆኖም የናይጄሪያው ተከላካይ ካልቪን ባሴ እንደ ጥቁር ድንጋይ የማይናወጥ ግድግዳ ሆነባቸው።
ናይጄሪያውያን ልክ እንደ አድብቶ እንደሚጠብቅ አንበሳ ነበሩ። ጥቂት ኳሶችን ብቻ ወደ ግብ ሞከሩ፣ ነገር ግን እያንዳንዷ ሙከራቸው የሞሮኮን ደጋፊዎች ልብ ትነቅላለች። ደቂቃዎቹ ሲከንፉ፣ በሜዳው ላይ ያለው ትግል ከእግር ኳስ አልፎ የጥንካሬና የጽናት ፈተና ሆነ። 90ኛው ደቂቃ ሲጠናቀቅ ሰሌዳው አሁንም 0-0 ይላል። ጭንቀቱ ነፍስ ያስጨንቃል። በዚህ ሰአት ስልክ ቢደወል ጆሮ ቀልብ ሰጥቶ መስማት አይችልም።
የሁለቱ ደቂቃዎች ቁማር
ተጨማሪ 30 ደቂቃዎች። ተጫዋቾቹ በድካም እየተዝለፈለፉ ነው። ብራሂም ዲያዝ ኃይሉ አልቆበታል፣ ግን አሁንም ይሮጣል። የሞሮኮው ግብ ጠባቂ ያሲን ቡኑ ጓንቶቹን እያጠባበቀ ወደ ሰማይ ተመለከተ።
118ኛው ደቂቃ ላይ አሰልጣኝ ኤሪክ ሼል አለምን ያስገረመ ውሳኔ አስተላለፉ። የቡድኑን መሪና ድንቅ አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜንን አስወጥተው ሳሙኤል ቹኩዌዜን አስገቡ። ስታዲየሙ በሹክሹክታ ተሞላ። "ኦሲሜን ሳይኖር መለያ ምት?" ይህ ውሳኔ ወይ የታሪክ ጀግና ያደርጋቸዋል፣ ወይም የውድቀታቸው መጀመሪያ ይሆናል።
የያሲን ቡኑ "ጥቁር አስማት"
መለያ ምት ተጀመረ። ስታዲየሙ መቃብር ውስጥ ያለ ይመስል ፀጥ አለ። መርፌ ቢወድቅ ይሰማል።
የናይጄሪያው ቹኩዌዜ... አሰልጣኙ ተስፋ ጥለውበት ያስገቡት ተጫዋች። ሮጦ መታ... ቡኑ እንደ ድመት ተወርውሮ ኳሷን አዳናት! ስታዲየሙ ሊፈርስ ደረሰ። የሞሮኮው ደጋፊዎች ድምፅ ራባትን አናወጣት።
ቀጥሎ ብሩኖ ኦንዬማቺ መጣ። በቡኑ አይኖች ውስጥ ያለው መተማመን ተጫዋቹን ያስፈራው ይመስላል። ቡኑ በድጋሚ ኳሷን አዳናት! "ያሲን! ያሲን!" የሚለው ጩኸት ሰማዩን ቀደደው። በሞሮኮ በኩል አሽራፍ ሀኪሚ፣ ኒል ኤል አይናዊ እና ኤሊሴ ቤን ሰጊር ያለምንም ስህተት መረቡን አናወጡት።
የታሪክ መደምደሚያ
የመጨረሻው ምት። ዩሱፍ ኤን-ነስሪ ኳሷን ይዞ ቆሟል። ኳሷን ከመታ መላው ሞሮኮ ወደ ፍጻሜ ትገባለች። ካልመታ ግን ጭንቀቱ ይቀጥላል።
ኤን-ነስሪ ኳሷን አያት... ስታዲየሙ ትንፋሹን ዋጠ። ሮጦ መታ! ኳሷና መረቡ ሲገናኙ፣ የራባት ሌሊት ወደ ደማቅ የብርሃንና የደስታ ውቅያኖስ ተለወጠች። ሞሮኮ 4-2 በሆነ ውጤት ናይጄሪያን አሸንፋ ለፍጻሜ አለፈች።
የሰሜን አፍሪካ ንጋት
በዚህ ሌሊት ማንም አልተኛም። ከታንጂየር እስከ ካዛብላንካ፣ ከማራካሽ እስከ ፌዝ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጣ። መኪናዎች ጡሩምባ ያሰማሉ፣ እናቶች እልል ይላሉ። አየሩ በ "ዲማ ማግሬብ" መዝሙር ታጥቧል።
በናይጄሪያ በኩል ግን ጸጥታ ነገሰ። የቀድሞ ተጫዋች ዋይዲ አካኒ በአሰልጣኙ ውሳኔ ተቆጥቶ "ዝግጅት አነስቶን ነበር" ሲል ለጋዜጠኞች ተናገረ። ኦሲሜን በመልበሻ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ በሀዘን አንገቱን ደፍቷል።
አሁን ጥር 10ይናፍቃል። የአትላስ አንበሶች ከሴኔጋሉ አንበሳ ሳዲዮ ማኔ ጋር ለዋንጫ ይፋጠጣሉ። የራባት ሌሊት የድል ሽታ እንደያዘች ወደ ንጋት ተሻገረች። ሞሮኮ ታሪክ ለመስራት የቀራት አንድ እርምጃ ብቻ ነው።

🏆 የዛሬ 50 አመት በኢትዮጵያ ካሳካችው ድል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞሮኮ ለአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ በቃች! 🇲🇦🏟️
አስተናጋጇ ሞሮኮ የናይጄሪያውን "ሱፐር ኢግልስ" በመለያ ምት 4-2 በማሸነፍ ለ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች። የአትላስ አንበሶቹ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ታሪክ ለመድገም ከሴኔጋል ጋር ለዋንጫው ይፋለማሉ።
🔥 የጨዋታው ድምቀቶችና ትኩስ መረጃዎች፦
ታሪካዊ ትዝታ፦ ሞሮኮ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችው እ.ኤ.አ በ1976 በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በተካሄደው ውድድር ነበር። አሁን ከ50 ዓመታት በኋላ ያንን ታሪክ በገዛ ሜዳቸው ለመድገም አንድ ጨዋታ ብቻ ቀርቷቸዋል።
የቡኑ ድንቅ ብቃት፦ የአለም ድንቁ ግብ ጠባቂ ያሲን ቡኑ የሳሙኤል ቹኩዌዜ እና ኦኒዬሜቺን መለያ ምቶች በማዳን በድጋሚ የሀገሩ ጀግና ሆኗል።
የናይጄሪያ መክሸፍ፦ ናይጄሪያውያን በ120 ደቂቃ ውስጥ ለጎል የሚሆን ሙከራ ለማድረግ ተቸግረዋል (2 ሙከራዎች ብቻ)። ኮከቡ ቪክቶር ኦሲሜን በሞሮኮ ተከላካዮች ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ በመለያ ምት ወቅትም በሜዳ ላይ አልነበረም።
ሜዳው በደስታ ተናወጠ፦ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ እና ብራሂም ዲያዝ በደስታ ሜዳውን ሲያጥለቀልቁት፤ በመለያ ምት የሳቱት የናይጄሪያ ተጫዋቾች ግን በሃዘን ተሰብረው ታይተዋል።
🏟️ የፍፃሜው ተጠባቂ ፍልሚያ፦
🏆 ሞሮኮ 🆚 ሴኔጋል
(የአሁኑ ሻምፒዮን ሴኔጋል እና የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ደራሽዋ ሞሮኮ የሚያደርጉት ፍልሚያ በአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል)
ሞሮኮ በኢትዮጵያ ያሳካችውን የ50 ዓመት ድል በገዛ ሜዳዋ ትደግመው ይሆን?

በናይጄሪያ በገበያ ቦታ ላይ በተፈጸመ የመሳሪያ ጥቃት 30 ሰዎች ተገደሉ
በሰሜናዊ ናይጄሪያ ኒጀር ግዛት ውስጥ ታጣቂዎች በአንድ ገበያ ላይ በከፈቱት ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃት አድራሾቹ በሰዎች ላይ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ በገበያው ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሱቆችን ዘርፈዋል እንዲሁም በእሳት አቃጥለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው እሁድ ዕለት በኒጀር ግዛት ዲሞግራም በሚገኘው የካሱዋን ዳኪ ኻሶ ገበያ ውስጥ በአካባቢው አቆጣጠር ከቀኑ 10:30 ላይ ነው።
የኒጀር ፖሊስ ቃል አቀባይ ዋሲዮ አቢዮዱን እንደገለጹት፣ ሞተር ሳይክል የጫኑ በርካታ ታጣቂዎች እሁድ ዕለት ወደ ገበያው በመግባት ተኩስ ከፍተዋል።
በዚህም ቢያንስ 30 ሰዎች በቦታው ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
በተጨማሪም ሱቆችን ዘርፈው በእሳት አቃጥለዋል።
እነዚህ አሸባሪዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ "ዘራፊዎች" በሚል ስም ይታወቃሉ። አቢዮዱን ለሮይተርስ እንደገለጹት "አሸባሪዎቹ ከመግደል፣ ከመዝረፍና ከማቃጠል በተጨማሪ የተወሰኑ ሰዎችንም አግተው ወስደዋል። ፖሊስ የታገቱትን ሰዎች ለማስለቀቅ ኦፕሬሽን ጀምሯል።"
በጥቃቱ የቆሰሉት ዳውዳ ሳኩሌ የተባሉ ሰው ለሮይተርስ ሲናገሩ "ዘራፊዎቹ ሴቶችንና ሕፃናትን እንኳ አልማሩም። ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በገበያው ውስጥ ምንም ዓይነት የጸጥታ ኃይል አልነበረም። አሁንም በገበያው ውስጥ አስከሬን ፍለጋ እያደረግን ነው" ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ባወጡት መግለጫ፣ በጥቃቱ ላይ እጃቸው ያለበትን ግለሰቦች አስተዳደሩ በፍጥነት በቁጥጥር ስር እንዲያውል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ሮይተርስ

አሜሪካ የአይኤስን ምሽግ ደመሰሰች
📌አሜሪካ በአይኤስ ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በሚገኙ የኢስላሚክ ስቴት(አይኤስ) ምሽጎች ላይ ከባድ ጥቃት ማድረሷን ተናግረዋል።
የአሜሪካ ጦር እንደገለጸው ፥ በሶኮኮ ግዛት በታጣቂ ቡድኑ የሚተዳደሩ ካምፖች ከኒጀር ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ተመትተዋል። የሟቾች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውም ተነግሯል።
የአሜሪካ ጦር በርካታ የተሳኩ ጥቃቶችን መፈጸሙን ትራምፕ ሲያረጋግጡ፥ የዩኤስ አፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) በበኩሉ የሐሙሱ ጥቃት በሶኮቶ ግዛት የተፈፀመው ከናይጄሪያ ጋር በመተባበር የተሳካ ነው ብሏል።
የናይጄሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ማይታማ ቱጋር ፥ አሸባሪዎችን ዒላማ ያደረገው ጥቃት ጥምር ኦፕሬሽን የተደረገበት መሆኑን ገልጸው ተጨማሪ እርምጃዎች መወሰዳቸው እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።
ትራምኘ አሸባሪ ሲሉ የጠሩት አይኤስ በንጹሃን ክርስትያኖች ላይ ዒላማ ያደረገ ግድያ እያደረሰ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ባለፈው ኅዳር ትራምፕ በናይጄሪያ የኢስላሚክ ታጣቂዎች እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው።
#nbc

8 months ago
የናይጄሪያ ተማሪዎች ከታገቱ ከአንድ ሳምንት በኃላ 24ቱ ተለቀቁ
#ethiopia | ከአንድ ሳምንት በፊት ከአዳሪ ትምህርት ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱት ተማሪዎች መካከል 24ቱ የናይጄሪያ ልጃገረዶች መፈታታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
የታጠቂ ቡድን አባላት በናይጄሪያ ኬቢቢ ግዛት የመንግስት ልጃገረዶች አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በወረሩበት ወቅት አንድ ሰራተኛ ገድለው 25 ተማሪዎችን አግተዋል። አንደኛዋ ተማሪ ብዙም ሳትቆይ ማምለጥ ችላለች።
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ የጸጥታ ሃይሎችን ለችግሩ “ፈጣን ምላሽ” መስጠታቸዉን አመስግነዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ ግን እንዴት የታገቱት ተማሪዎች ሊለቀቁ እንደቻሉ ግልፅ አላደረጉም።
በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችዉ ናይጄሪያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሰዎች እገታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ ባለፈው አርብ ከ250 በላይ ሕፃናት ከካቶሊክ ትምህርት ቤት ታግተው እስካሁን ድረስ የደሰረሱበት አልታወቀም፡፡
የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ በሰጡት መግለጫ በኬቢ ግዛት ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች የተወሰዱ ልጃገረዶች በሙሉ ተጠያቂ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፣ ክስተቱ በሌሎች ሁለት የናይጄሪያ ግዛቶች መፈጸሙን ጠቁመዋል።
አማካሪዉ ኒኒፉ እንዳሉት ተጨማሪ የአፈና አደጋዎችን ለመከላከል የጸጥታ ኃይሎች ወደ ተጋላጭ አካባቢዎች እንደሚሰማሩ ተናግረዋል ያለው ዳጉ ጆርናል ነው።

9 months ago
በናይጄሪያ ክርስቲያኖች ላይ "ስደት እየደረሰ ነው"
#ethiopia | ክርስቲያኖች ላይ "ስደት እየደረሰ ነው" በሚሉ ክሶች ምክንያት የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ጦር ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ ፣ በመካከለኛው ናይጄሪያ በምትገኝ አንዲት ቤተክርስቲያን ላይ ታጣቂዎች ጥቃት መሰንዘራቸውን ባለስልጣናት ገለጹ።
በማክሰኞ ምሽት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተረጋግጧል።
ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን የለም። የክዋራ ግዛት ፖሊስ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፣ ጥቃቱ የተፈጸመው በኤሩኩ ከተማ ነው።
ፖሊስ የተኩስ ድምጽ ተከትሎ ወደ ስፍራው ሲደርስ፣ "አንድ ሰው በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፣ ሌላኛው ደግሞ በአቅራቢያው" ተገድለው መገኘታቸውን አስታውቀዋል።
ይህ ጥቃት እና ሰኞ እለት በሰሜን ናይጄሪያ 24 ተማሪዎች መታገታቸውን ተከትሎ፣ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ በደቡብ አፍሪካ ሊካፈሉት የነበረውን የ G20 (የዓለም መሪ ሀብታም እና ታዳጊ ሀገራት) ጉባኤ ጉዟቸውን ማዘግየታቸውን ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል።
የክዋራ ግዛት ገዥ በበኩላቸው፣ ፕሬዝዳንት ቲኑቡ 900 ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ ክልሉ በመላካቸው ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ፣ "በናይጄሪያ ክርስትና 'የህልውና አደጋ' (existential threat) ተጋርጦበታል" በማለት ፔንታጎን (የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር) በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ሊወሰድ ስለሚችል ወታደራዊ እርምጃ ዝግጅት እንዲጀምር ማዘዛቸው ተዘግቧል።
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቲኑቡ በበኩላቸው፣ "ናይጄሪያን እንደ ሃይማኖት የማትታገስ ሀገር አድርጎ መግለጽ የሀገሪቱን እውነታ አያንጸባርቅም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ተንታኞች እንደሚሉት፣ ምንም እንኳን ክርስቲያኖች በጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ቢሆኑም፣ በአብዛኛው የጥቃቶቹ ሰለባ የሚሆኑት በሙስሊም በበዛበት የሰሜን ናይጄሪያ ክፍል የሚኖሩ ሙስሊሞች ናቸው።
የመካከለኛው ናይጄሪያ ክልል በአካባቢው አርብቶ አደሮች እና አርሶ አደሮች መካከል በመሬትና በውሃ ውስንነት ምክንያት በሚፈጠሩ ግጭቶች ለዓመታት ሲታመስ ቆይቷል።
እነዚህ ግጭቶች የሃይማኖት መልክ በመያዝ፣ በአብዛኛው ከሙስሊም አርብቶ አደሮች ወይም ከክርስቲያን አርሶ አደር ማህበረሰቦች ጋር የሚወግኑ ሚሊሻዎችን ፈጥረዋል። የሰሜኑ ክፍል ደግሞ በቦኮ ሃራም እና ከዳኢሽ (ISIS) ጋር በተቆራኙ ቡድኖች ጥቃት በየጊዜው ይፈጸምበታል ያለው ዘሃበሻ ነው።

10 months ago
አፍሪካን የመገንባት ራዕይ
#ethiopia | እሳቸው አንድ ሰው ቢሆኑም ራዕያቸው ግን መላው አፍሪካን እያዳረሳት ይገኛል፡፡
በመላው ናይጄሪያ ውስጥ በየቀኑ ከሚመገቡት ጨው አንስቶ እስከሚራመዱበት መንገድ ድረስ ዘልቆ በመግባት የእያንዳንዱን ሰው ሕይወት ይዳስሳሉ።
አያታቸው በእሳቸው አስተዳደግ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ ይነገራል፡፡
በልጅ ልጃቸው ውስጥ ያለውን የስራ ፈጣሪነት መንፈስ ለማነሳሳትም ረድተዋል፡፡
የስምንት ዓመት ልጅ እያሉ ከአያታቸው የተሰጣቸውን የኪስ ገንዘብ ጣፋጭ ነገር በመግዛት ለሌሎች አትርፈው ይሸጡም ነበር፡፡
በግብፅ ካይሮ ከሚገኘው የአል-አዛሃር ዩኒቨርሲቲ የተመረቁት ዳንጎቴ፤ የቢዝነስ ስራቸውን የጀመሩት እንደ ትልቅ ተቋም ሳይሆን መጠነኛ የንግድ ድርጅት በመጀመር ነው።
ከሸቀጥ ንግድ እስከ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኢንዱስትሪ ጅማሬው ከዚህ ተነስቷል፡፡
የዳንጎቴ መስራች አሊኮ ዳንጎቴ በሲሚንቶ፣ በስኳርና በዱቄት በመሳሰሉት ሸቀጦች በመገበያየት፣ በማስመጣትና ናይጄሪያ ውስጥ በመሸጥ ነበር የስኬት ጉዞአቸውን የጀመሩት።
ጅማሬያቸው ቀላል መስሎ ቢታይም መዳረሻቸው ልቆና ገዝፎ ተገኘ፡፡
ገና በለጋነታቸው ‹‹ችግር የሥኬት ምንጭ ነው›› የሚለውን የቢዚነስ እሳቤ የተረዱ ይመስላል፡፡
በዚህ እሳቤ ሰዎች በየቀኑ የሚፈልጓቸውን ሸቀጦች መለየትና አቅርቦታቸውን መቆጣጠርም ጀመሩ።
ፍልስፍናቸው አንድ ሀገር ከሌሎች ሀገራት የሚያስመጣውን ምርት በሀገር ውስጥ ማምረት እንዳለበት ያወሳል።
ይህ ስልትም ዳንጎቴ ነጋዴ ብቻ ሳይሆኑ ብሄራዊ ስትራቴጂስትም አድርጓቸዋል።
በተግባርም ናይጄሪያን ከሲሚንቶ አስመጪነት ወደ ላኪነት ቀይሯታል፡፡
በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ የትኛውንም ትልቅ ግንባታ ካዩ መሰረቱ በዳንጎቴ ሲሚንቶ የጸና ነው።
ዳንጎቴ እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መገባደጃ ላይ ከስኳር ማጣሪያ ጀምሮ የራሳቸውን የምርት ፋብሪካዎች መገንባት ጀመሩ።
ይህ ርምጃ ንግድን ከከባቢው ጋር በማዋሀድ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካትም አስቻለ፡፡
ከትሁት ጅማሬዎች እስከ አህጉራዊ የበላይነትንም እንዲቀዳጁ አስቻላቸው፡፡
በዚህም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በሲሚንቶ ማምረት፣ ነዳጅ በመፈለግ፣ ማዕድን በማውጣት፤ የማዳበሪያ ፋብሪካ በመገንባት፣ የተፈጥሮ ጋዝ በማጓጓዣ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሰማርተዋል፡፡
የዳንጎቴ ትጋት የጀመረው ከተደላደለ ሁኔታ ሳይሆን በድፍረት፣ በብድር እና በማያቋርጥ ራዕይ ነው።
ወጣት በነበሩበት ጊዜ ከአጎታቸው አነስተኛ ገንዘብ ተበድረው የዛሬ መዳረሻቸውን አንድ ርምጃ ተራመዱ፡፡
በሌጎስ፣ ናይጄሪያ በአንደ የንግድ ቦታ የተጀመረው ስራ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
ዳንጎቴ ትክክለኛው ሀብት በማኑፋክቸሪንግ ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ በፍጥነት ከመሸጥ ወደ ማምረት ገቡ።
በመጀመሪያም በስኳር ማጣሪያ፣ ከዚያም በጨው ፋብሪካ እና ሲሚንቶ እያሉ ዛሬም ያልታጎለው ጉዞአቸውን ቀጥሏል፡፡
ዛሬ የዳንጎቴ ኢንደስትሪ የባለብዙ ቢሊየን ዶላሮች ባለቤት ሲሆን፤ የአህጉሪቱ ትልቁ ሲሚንቶ አምራች ሆኗል፡፡
ይህም በናይጄሪያና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚሰራ ነው።
እንዲሁም የዳንጎቴ ስኳር ማጣሪያ የገበያ መሪ ሲሆን፤ የጨው ምርቱም በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ቶን ያመርታል።
በዘይት እና ጋዝም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየሰሩበት ይገኛል፡፡
አፍሪካ ሰፊ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት አህጉር ብትሆንም ለበርካታ አስርት ዓመታት ያክል ከሌሎች ስትገለገል ቆይታለች።
ታዲያ ዳንጎቴ ይህንን ችግር ልብ ያሉ ይመስላል። ለዚህም ኩባንያቸው በሌጎስ ናይጄሪያ የሚገኘውን የዳንጎቴ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት አስጀመረ።
ይህ ፋብሪካም በዓለም ላይ ትልቁ የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻ ሲሆን፤ በዓመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም አለው፡፡
ናይጄሪያ በማዳበሪያ ራሷን እንድትችል እና ለዓለም አቀፍ ገበያ በተለይም ለአፍሪካና ለአሜሪካ ከፍተኛ ኤክስፖርት ማድረግ እንድትችል የተጀመረ ውጥን ነው፡፡
ይህ ተቋም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አርሶ አደሮች የሰብል ምርትን የማሳደግ፣ የግብርና ኢኮኖሚን የማረጋጋትና የዓለም የማዳበሪያ ንግድ ቀመርን የመቀየር ኃይልን ተቀዳጅቷል።
ይህም አፍሪካ እራሷን መመገብ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፋዊ የግብርና ንግድ ውስጥ ወሳኝ ተዋናይ መሆን እንደምትችል አመላካች ሆኗል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም አድማሱን እያሰፋ የመጣው የዳንጎቴ ቡድን የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊያቀና ተሰልፏል።
ለዚህም በ2007 ዓ.ም ያስመረቀው ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ተጠቃሽ ነው።
የዳንጎቴ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የቅርብ ጊዜ ጅማሮ ሳይሆን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ውጥን ነው።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን ኢኮኖሚ እያስመዘገቡ ካሉና ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ፍላጎት ያላት መሆኑን በመገንዘብ ድርጅታቸው ከዓመታት በፊት በሲሚንቶ ማምረት ወደሀገሪቱ ገብቷል፡፡
ይህ ርምጃ የኢትዮጵያን ሥር የሰደደ የሲሚንቶ እጥረት ለማስቆም እና ግዙፍ የግንባታ ግስጋሴዋን የሚደግፍ እና የዳንጎቴን ቡድን ታዋቂነትን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በማሸጋገር ላይም ይገኛል።
ስምምነቱ የዳንጎቴ ቡድን በሙያው ባለባቸው ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ መንገድ የሚከፍት ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል በማዳበሪያ ምርት የናይጄሪያውን ስኬት በመጠቀም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት በምግብ ራስን የመቻል ራዕይ ጋር በቀጥታ የሚጣጣም ነው።
በዚህም ኢትዮጵያ ሲሚንቶና ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ በማምረት ለገቢ ንግድ የምታወጣውን በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ማዳን እንድትችል የሚያግዝ ነው።
ይህ ተግባርም በሺዎች ለሚቆጠሩ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የስራ እድል በመፍጠር የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ያሳድጋል።
እንዲሁም የዳንጎቴ ቡድን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማኑፋክቸሪንግ እውቀትና ቴክኖሎጂን በማምጣት የኢትዮጵያን አጠቃላይ የኢንዱስትሪ ስነ-ምህዳር ከፍ ያደርገዋል።
ኢትዮጵያ የራሷን ሲሚንቶ፣ ማዳበሪያና ሌሎችም ምርቶች ወደ ሰፊው የምስራቅ አፍሪካ ገበያ ኤክስፖርት ማድረግ እንድትችልም ያደርጋታል፡፡
የዳንጎቴ ግሩፕ በአፍሪካ ውስጥ የሚሰራ ኩባንያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ እጣ ፈንታ ቀያሽ መሐንዲስም እየሆነ ነው።
ከናይጄሪያ በተጨማሪ በኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ፣ ሴኔጋል፣ ካሜሮን፣ ኮንጎ፣ ጋና፣ ሴራሊዮንና ኮትዲቭዋር የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ገንብተዋል።
በናይጄሪያ ሌጎስ የአፍሪካ ግዙፉን የነዳጅ ማጣሪያ በመገንባትም ጋና እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት ነዳጅ ያቀርባል።
በአሁኑ ወቅት ከ17 በላይ በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ተሳትፎ ያለው ሲሆን፤ በአህጉሪቱ የሲሚንቶ ገበያም መሪ ነው።
ዳንጎቴ የንግድ ድርጅት ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እጣ ፈንታ እየቀረጸ ይገኛል።
ሀገራት ለግንባታ የሚውል ሲሚንቶ፣ ለምግብ ማዳበሪያ እና ለኃይል ማመንጫ የተጣራ ነዳጅ በሀገር ውስጥ ማምረት እንዲችሉም ድጋፍ በማድረግ ላይ ነው።
በቅርቡ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነትም አፍሪካ እራሷን እንድትችል እና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ለማምጣት ያለውን ተልእኮ የሚያሳይ ነው ሲል ጋዜጣ+ ዘግቧል።

12 months ago
የናይጄሪያ ብሮድካስተር ከአራት ቀናት በላይ ያለምንም እረፍት የሬዲዮ ንግግር በማድረግ ሪከርድ ሰበረ
#ethiopia | አንድ የናይጄሪያ ብሮድካስተር የጊነስ ወርልድ ሪከርድን ለመስበር አስቦ የሬዲዮ የንግግር ሾውነት ከአራት ቀናት በላይ በማስተላለፍ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል እየተባለ ነው።
ይህ ስርጭት ለረጅም ጊዜ የተላለፈ የሬዲዮ የንግግር ትዕይንት በመሆን ሪከርዱን ሰብሯል ተብሏል።
የዝግጅቱ አዘጋጅ ይህን ያልተቋረጠ ስርጭት ለማካሄድ ያቀደው፣ የህዝብ ግንዛቤን ለመፍጠር እና በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ወሳኝ ጉዳይ ለማንሳት እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ስኬት በናይጄሪያ የብዙሃን መገናኛ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክስተት ተደርጎ ሲታይ፣ በአለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል ነው የተባለው።
ስርጭቱ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ አድማጮችን ማግኘት ችሏል ነው የተባለው።
ብሮድካስተሩ በየመሃሉ ሙዚቃዎች ሲተላለፉ አጭር እንቅልፍ እንደሚተኛ እና ምግብ እንደሚመገብም ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ስርጭት ሪከርድ የያዘው ሌላ ብሮድካስተር የነበረ ሲሆን፣ የናይጄሪያው ብሮድካስተር ይህንን በመስበር አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ችሏል ተብሏል።
ይህ ሪከርድ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ በይፋ ሲረጋገጥ፣ ብሮድካስተሩ እውቅና ያገኛልም ተብሏል ሲል መናኸሪያ ኤፍኤም ዘግቧል።

1 year ago
ናይጀሪያ አፍሪካውያንን ከጥገኝነት ልታላቅ ነዉ / ዳንጎቴ/
የናይጄሪያው ዳንጎቴ ፔትሮሊየም ማጣሪያ ቢያንስ 1.6 ሚሊዮን በርሜል ቤንዚን እና ናፍታ መያዝ የሚችል
ታንከሮችን በናሚቢያ ዋልቪስ ቤይ ሊገነባ መሆኑ ተሰምቷል ።
ይህ የዳንጎቴ ዉሳኔ በአፍሪካ የነዳጅ አቅርቦትን የመቆጣጠር ስልታዊ እርምጃን ያሳያል ።
ይህ በናይጄሪያ ኦንዶ ግዛት ውስጥ በ15 ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው በቀን 500,000 በርሜል የማጣራት አቅም ያለው ማጣሪያ ሲጠናቀቅ እ.ኤ.አ. በ2024 ሥራ የጀመረው በቀን 650,000 በርሜል ድፍድፍ ዘይት የማጣራት አቅም ያለው እና በ20 ቢሊዮን ዶላር ከተገባዉ ንብረትነቱ የዳንጎቴ የሆነዉ የነዳጅ ማጣሪያ ቀጥሎ በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ሁለተኛው ማጣርያ ይሆናል ተብሏል ።
ይህ ፕሮጀክት ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር በኢላጄ ኢንዱስትሪያል ነፃ ዞን ውስጥ በሚገኘው በኦንዶ ግዛት ልማትና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በኩል የሚለማ ሲሆን የመግባቢያ ሰነዱን እ.ኤ.አ ሀምሌ 15 ቀን 2025 ከናይጄሪያ ብሄራዊ ፔትሮሊየም ኩባንያ (NNPC) ጋር ለመፈረም ቀጠሮ ይዘዋል ።
የቢንኤል ባለስልጣናት እንዳሉት የመጀመሪያው ምዕራፍ በ48 ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ታቅዷል በቀን 100,000 በርሜል የሚያጣራዉ ክፍልን ጨምሮ እንደ መንገድ፣ ማከማቻ ታንኮች፣ ተርሚናሎች እና ማስተናገጃ መሳሪያዎች ያሉ ተዛማጅ መሠረተ ልማቶችን ለመሥራት አቅዷል።
የናይጄሪያን ኢነርጂ ሉዓላዊነት የአካባቢያዊ ዕድገትን እና የህዝብ ገቢን ሊያጠናክር ትልቅ አቅም እንደሚሆን የገለፁት የቢንኤል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዋለ አዴኮላ
ከሃገሪቱ አልፎ ለቦትስዋና፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አንዳንድ ክፍሎች የነዳጅ ስርጭትን ለማቅረብ ያለመ ነው።ይህም ከጥገኝነት ያላቀናል ብለዋል።
ዳንጎቴ በነዳጅ ማጣርያዎች ላይ እያሳየ ያለዉ ፍላጎት የአፍሪካን የነዳጅ አቅርቦት ከምዕራባውያኑ እጅ በመንጠቅ ለመቆጣጠር ነዉ እየተባለ ይገኛል ።
ስናዘጋጅ ሮይተርስ አፍሪካ ኢንሳይደር የናይጀሪያ ኮሚኒኬሽን ተጠቅመናል ።
የኔታ ትዩብ ዘጋቢ ታዴ የማመይ ልጅ

🇪🇹🇳🇬 ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ "ሙሉ በሙሉ አፍሪካ ሠራሽ" በሆኑ የድሮን ምርቶች ላይ ለመተባበር ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ
ይህ የተገለፀው የናይጄሪያ አየር ኃይል ልዑክ በቅርቡ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ ነው፡፡
የናይጄሪያው ወገን በኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የአቪዬሸን ግምጃ ቤት ጥገና ማዕከል፣ ደጀን የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እና የአየር ኃይል አካዳሚ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የሁለቱ ሀገራት አጋርነት አፍሪካ በመከላከያ እና ኤሮስፔስ ዘርፍ በፈጠራ፣ ትብብር እና የጋራ ዕሴት አፍሪካ መር የሆኑ መፍትሄዎችን ገቢር ለማድረግ ያላትን ራዕይ የሚያንፀባርቅ ነው መባሉን የናይጄሪያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

Comments