Logo
SeledaPost
🇪🇹🇳🇬 ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ "ሙሉ በሙሉ አፍሪካ ሠራሽ" በሆኑ የድሮን ምርቶች ላይ ለመተባበር ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ

ይህ የተገለፀው የናይጄሪያ አየር ኃይል ልዑክ በቅርቡ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተቋማት ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ ነው፡፡

የናይጄሪያው ወገን በኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የአቪዬሸን ግምጃ ቤት ጥገና ማዕከል፣ ደጀን የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እና የአየር ኃይል አካዳሚ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የሁለቱ ሀገራት አጋርነት አፍሪካ በመከላከያ እና ኤሮስፔስ ዘርፍ በፈጠራ፣ ትብብር እና የጋራ ዕሴት አፍሪካ መር የሆኑ መፍትሄዎችን ገቢር ለማድረግ ያላትን ራዕይ የሚያንፀባርቅ ነው መባሉን የናይጄሪያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.