ናይጀሪያ አፍሪካውያንን ከጥገኝነት ልታላቅ ነዉ / ዳንጎቴ/
የናይጄሪያው ዳንጎቴ ፔትሮሊየም ማጣሪያ ቢያንስ 1.6 ሚሊዮን በርሜል ቤንዚን እና ናፍታ መያዝ የሚችል
ታንከሮችን በናሚቢያ ዋልቪስ ቤይ ሊገነባ መሆኑ ተሰምቷል ።
ይህ የዳንጎቴ ዉሳኔ በአፍሪካ የነዳጅ አቅርቦትን የመቆጣጠር ስልታዊ እርምጃን ያሳያል ።
ይህ በናይጄሪያ ኦንዶ ግዛት ውስጥ በ15 ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው በቀን 500,000 በርሜል የማጣራት አቅም ያለው ማጣሪያ ሲጠናቀቅ እ.ኤ.አ. በ2024 ሥራ የጀመረው በቀን 650,000 በርሜል ድፍድፍ ዘይት የማጣራት አቅም ያለው እና በ20 ቢሊዮን ዶላር ከተገባዉ ንብረትነቱ የዳንጎቴ የሆነዉ የነዳጅ ማጣሪያ ቀጥሎ በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ሁለተኛው ማጣርያ ይሆናል ተብሏል ።
ይህ ፕሮጀክት ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር በኢላጄ ኢንዱስትሪያል ነፃ ዞን ውስጥ በሚገኘው በኦንዶ ግዛት ልማትና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በኩል የሚለማ ሲሆን የመግባቢያ ሰነዱን እ.ኤ.አ ሀምሌ 15 ቀን 2025 ከናይጄሪያ ብሄራዊ ፔትሮሊየም ኩባንያ (NNPC) ጋር ለመፈረም ቀጠሮ ይዘዋል ።
የቢንኤል ባለስልጣናት እንዳሉት የመጀመሪያው ምዕራፍ በ48 ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ታቅዷል በቀን 100,000 በርሜል የሚያጣራዉ ክፍልን ጨምሮ እንደ መንገድ፣ ማከማቻ ታንኮች፣ ተርሚናሎች እና ማስተናገጃ መሳሪያዎች ያሉ ተዛማጅ መሠረተ ልማቶችን ለመሥራት አቅዷል።
የናይጄሪያን ኢነርጂ ሉዓላዊነት የአካባቢያዊ ዕድገትን እና የህዝብ ገቢን ሊያጠናክር ትልቅ አቅም እንደሚሆን የገለፁት የቢንኤል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዋለ አዴኮላ
ከሃገሪቱ አልፎ ለቦትስዋና፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አንዳንድ ክፍሎች የነዳጅ ስርጭትን ለማቅረብ ያለመ ነው።ይህም ከጥገኝነት ያላቀናል ብለዋል።
ዳንጎቴ በነዳጅ ማጣርያዎች ላይ እያሳየ ያለዉ ፍላጎት የአፍሪካን የነዳጅ አቅርቦት ከምዕራባውያኑ እጅ በመንጠቅ ለመቆጣጠር ነዉ እየተባለ ይገኛል ።
ስናዘጋጅ ሮይተርስ አፍሪካ ኢንሳይደር የናይጀሪያ ኮሚኒኬሽን ተጠቅመናል ።
የኔታ ትዩብ ዘጋቢ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago