የናይጄሪያ ተማሪዎች ከታገቱ ከአንድ ሳምንት በኃላ 24ቱ ተለቀቁ
#ethiopia | ከአንድ ሳምንት በፊት ከአዳሪ ትምህርት ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱት ተማሪዎች መካከል 24ቱ የናይጄሪያ ልጃገረዶች መፈታታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
የታጠቂ ቡድን አባላት በናይጄሪያ ኬቢቢ ግዛት የመንግስት ልጃገረዶች አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በወረሩበት ወቅት አንድ ሰራተኛ ገድለው 25 ተማሪዎችን አግተዋል። አንደኛዋ ተማሪ ብዙም ሳትቆይ ማምለጥ ችላለች።
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ የጸጥታ ሃይሎችን ለችግሩ “ፈጣን ምላሽ” መስጠታቸዉን አመስግነዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ ግን እንዴት የታገቱት ተማሪዎች ሊለቀቁ እንደቻሉ ግልፅ አላደረጉም።
በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችዉ ናይጄሪያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሰዎች እገታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ ባለፈው አርብ ከ250 በላይ ሕፃናት ከካቶሊክ ትምህርት ቤት ታግተው እስካሁን ድረስ የደሰረሱበት አልታወቀም፡፡
የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ በሰጡት መግለጫ በኬቢ ግዛት ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች የተወሰዱ ልጃገረዶች በሙሉ ተጠያቂ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፣ ክስተቱ በሌሎች ሁለት የናይጄሪያ ግዛቶች መፈጸሙን ጠቁመዋል።
አማካሪዉ ኒኒፉ እንዳሉት ተጨማሪ የአፈና አደጋዎችን ለመከላከል የጸጥታ ኃይሎች ወደ ተጋላጭ አካባቢዎች እንደሚሰማሩ ተናግረዋል ያለው ዳጉ ጆርናል ነው።

9 months ago