በናይጄሪያ በገበያ ቦታ ላይ በተፈጸመ የመሳሪያ ጥቃት 30 ሰዎች ተገደሉ
በሰሜናዊ ናይጄሪያ ኒጀር ግዛት ውስጥ ታጣቂዎች በአንድ ገበያ ላይ በከፈቱት ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ጥቃት አድራሾቹ በሰዎች ላይ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ በገበያው ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሱቆችን ዘርፈዋል እንዲሁም በእሳት አቃጥለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው እሁድ ዕለት በኒጀር ግዛት ዲሞግራም በሚገኘው የካሱዋን ዳኪ ኻሶ ገበያ ውስጥ በአካባቢው አቆጣጠር ከቀኑ 10:30 ላይ ነው።
የኒጀር ፖሊስ ቃል አቀባይ ዋሲዮ አቢዮዱን እንደገለጹት፣ ሞተር ሳይክል የጫኑ በርካታ ታጣቂዎች እሁድ ዕለት ወደ ገበያው በመግባት ተኩስ ከፍተዋል።
በዚህም ቢያንስ 30 ሰዎች በቦታው ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።
በተጨማሪም ሱቆችን ዘርፈው በእሳት አቃጥለዋል።
እነዚህ አሸባሪዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ "ዘራፊዎች" በሚል ስም ይታወቃሉ። አቢዮዱን ለሮይተርስ እንደገለጹት "አሸባሪዎቹ ከመግደል፣ ከመዝረፍና ከማቃጠል በተጨማሪ የተወሰኑ ሰዎችንም አግተው ወስደዋል። ፖሊስ የታገቱትን ሰዎች ለማስለቀቅ ኦፕሬሽን ጀምሯል።"
በጥቃቱ የቆሰሉት ዳውዳ ሳኩሌ የተባሉ ሰው ለሮይተርስ ሲናገሩ "ዘራፊዎቹ ሴቶችንና ሕፃናትን እንኳ አልማሩም። ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በገበያው ውስጥ ምንም ዓይነት የጸጥታ ኃይል አልነበረም። አሁንም በገበያው ውስጥ አስከሬን ፍለጋ እያደረግን ነው" ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ባወጡት መግለጫ፣ በጥቃቱ ላይ እጃቸው ያለበትን ግለሰቦች አስተዳደሩ በፍጥነት በቁጥጥር ስር እንዲያውል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ሮይተርስ

7 months ago