Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ የአይኤስን ምሽግ ደመሰሰች

📌አሜሪካ በአይኤስ ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በሚገኙ የኢስላሚክ ስቴት(አይኤስ) ምሽጎች ላይ ከባድ ጥቃት ማድረሷን ተናግረዋል።

የአሜሪካ ጦር እንደገለጸው ፥ በሶኮኮ ግዛት በታጣቂ ቡድኑ የሚተዳደሩ ካምፖች ከኒጀር ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ተመትተዋል። የሟቾች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውም ተነግሯል።

የአሜሪካ ጦር በርካታ የተሳኩ ጥቃቶችን መፈጸሙን ትራምፕ ሲያረጋግጡ፥ የዩኤስ አፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) በበኩሉ የሐሙሱ ጥቃት በሶኮቶ ግዛት የተፈፀመው ከናይጄሪያ ጋር በመተባበር የተሳካ ነው ብሏል።

የናይጄሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሱፍ ማይታማ ቱጋር ፥ አሸባሪዎችን ዒላማ ያደረገው ጥቃት ጥምር ኦፕሬሽን የተደረገበት መሆኑን ገልጸው ተጨማሪ እርምጃዎች መወሰዳቸው እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

ትራምኘ አሸባሪ ሲሉ የጠሩት አይኤስ በንጹሃን ክርስትያኖች ላይ ዒላማ ያደረገ ግድያ እያደረሰ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ባለፈው ኅዳር ትራምፕ በናይጄሪያ የኢስላሚክ ታጣቂዎች እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው።
#nbc

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.