10 days ago
ዜና እረፍት | ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ – የምሕረት፣ የጀግንነትና የአገር አገልግሎት ተምሳሌት አረፈች
#ethiopia | የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ፕሮፌሽናል ነርሶች መካከል አንዷ፣ የኮሪያ ጦርነት ዘማች፣ የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ እና ዓለም አቀፍ የነርስነት ክብር ተሸላሚ የነበሩት መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ በ96 ዓመታቸው አርፈዋል።
ሲስተር ብርቅነሽ በአዲስ አበባ ከአቶ ከበደ ዘውገ እና ከወ/ሮ አልመዝ የግሉ ተወለዱ። ወላጆቻቸውን በለጋ ዕድሜያቸው በሞት ካጡ በኋላ፣ በአያታቸው ወ/ሮ ላቀች ጻታ እጅ አደጉ። የአባታቸው የአርበኝነት ታሪክ በመታሰቡ፣ በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በነጻ እንዲማሩ እድል አግኝተዋል።
በኋላም በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሆስፒታል (አሁን የካቲት 12 መታሰቢያ ሆስፒታል) በነበረው የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የነርሶች ትምህርት ቤት ተምረው፣ ከሀገሪቱ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ፕሮፌሽናል ነርሶች መካከል በክብር ተመርቀዋል።
በ1943 ዓ.ም. ከሦስተኛው ቃኘው ሻለቃ ጋር ወደ ኮሪያ በማቅናት፣ ከሁለት ጥቁር አፍሪካዊ ሴት ነርሶች አንዷ ሆነው ታሪክ ሠርተዋል። ከሲስተር አስቴር አያና ጋር በመሆን የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የቀይ መስቀል ዘማቾች በመሆን በተባበሩት መንግሥታት ሥር በኮሪያ ጦርነት ውስጥ ለወታደሮች ሕክምና እና ሰብዓዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። ከሕክምና ሥራቸው በተጨማሪ ለኢትዮጵያውያን ወታደሮች የትርጉም አገልግሎትም አበርክተዋል።
ከኮሪያ በኋላ በጃፓን ወታደራዊ ሆስፒታል እንዲሁም በኢትዮጵያ በክብር ዘበኛ ሆስፒታል፣ በጳውሎስ ሆስፒታል፣ በድሬዳዋና በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ተቋማት ለብዙ ዓመታት በታማኝነት አገልግለዋል።
ለሰብዓዊ አገልግሎታቸው ዓለም አቀፍ ዕውቅና በማግኘት፣ በነርስነት ሙያ ከፍተኛ ክብር የሆነውን Florence Nightingale Award የተሸለሙ ጥቂት አፍሪካውያን ሴቶች መካከል አንዷ ሆነዋል።
የአገር አገልግሎታቸውን ለማክበር፣ እናት ባንክ በቦሌ ቡልቡላ የሚገኘውን አንድ ቅርንጫፍ በስማቸው ሰይሟል፤ ይህም ለሀገር ያበረከቱትን የማይረሳ አስተዋፅኦ የሚያሳይ የክብር ምልክት ነው።
መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በ96 ዓመታቸው አርፈዋል። ከባለቤታቸው ከጄኔራል ደስታ ገመዳ ጋር ያፈሯቸውን አራት ልጆችና ስምንት የልጅ ልጆች ትተው አልፈዋል።
ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ በጀግንነታቸው፣ በሰብዓዊነታቸው እና ለሀገራቸው ባበረከቱት አገልግሎት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለዘላለም የሚታወሱ ባለውለታ ሆነው ይኖራሉ።
ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ።
#tizbit Assefa

2 months ago
ዜና እረፍት
#ethiopia | የታዋቂው አርቲስትና ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ የረጅም ዘመን የትዳር አጋር የነበሩት ወይዘሮ መንበረ ግርማ በ75 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ለ37 ዓመታት ያህል በትዳር አብረው የዘለቁት ወይዘሮ መንበረ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ማረፋቸው ታውቋል።
የስንብት እና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ሰኞ፣ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለናፈቋቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።
#tesfayegesese #bereavement #ethiopianartist #condolences #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
ዜና እረፍት፦ ታዋቂዋ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቦኒ (Boni) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
በቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ማፍራት የቻለችው ወጣት ቦኒ (Boni) ህይወቷ ማለፉ ተሰማ።
ቦኒ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ስራዎቿ የምትታወቅ ሲሆን፣ በቲክቶክ ከ823 ሺህ በላይ እንዲሁም በፌስቡክ ገጿ ከ298 ሺህ በላይ ተከታዮች ነበሯት።
ወጣቷ ከዚህ ዓለም ከመለየቷ በፊት ባስተላለፈችው የመጨረሻ መልዕክት፤ በህይወት ጉዞዋ ውስጥ የገጠሟትን ተግዳሮቶች በማንሳት ለተከታዮቿ እና ለሚወዷት ሰዎች በሙሉ ስንብቷን ገልጻለች።
በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች እና የቃላት ጥቃቶች በሰዎች የአእምሮ ጤና ላይ የሚያሳድሩት ጫና ከፍተኛ መሆኑን ይህ ክስተት ዳግም አሳስቧል።
የብዙዎችን ቀልብ የሳበው የመጨረሻ መልዕክቷም፦ "ለሁላችሁም ይቅርታ አድርጌያለሁ፣ እናንተም ይቅር በሉኝ" የሚል ይዘት ነበረው።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ሁላችንም በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን ላይ እንድንጠነቀቅ እና ለሰዎች የምንሰጠው አስተያየት በህይወታቸው ላይ የሚያመጣውን ለውጥ እንድንገነዘብ ያደርጋል።
ለቤተሰቦቿ፣ ለቅርብ ወዳጆቿ እና ለተከታዮቿ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።#ጉርሻ
ነፍስ ይማር!
seledadotio

6 months ago
🕯️ ዜና እረፍት
የጀግናዋ አትሌት መሠረት ደፋር እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ 🕯️
#ethiopia | በሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያዎች እና በአራት የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ድሎች የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋ ያስቀመጠችው የጀግናዋ አትሌታችን መሠረት ደፋር ወላጅ እናት ወ/ሮ አስቴር መንገሻ ጫላ በዛሬው ዕለት ማለዳ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
📌 ስለ እናታችን ወ/ሮ አስቴር መንገሻ፦
እናታችን ወ/ሮ አስቴር ጀግናዋን አትሌት መሠረት ደፋርን ጨምሮ የስድስት ልጆች (የ2 ወንዶችና የ4 ሴቶች) እናት ነበሩ።
በአደረባቸው ሕመም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከፍተኛ ሕክምና ሲከታተሉ የቆዩ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት ማለዳ ሕይወታቸው አልፏል።
💔 የመሠረት ደፋር መሪር ሐዘን፦
ሁልጊዜም ስለ እናታቸው ፍቅርና ታላቅነት በኩራት የምትናገረው አትሌት መሠረት ደፋር፣ እናቷን ለማዳን ያልፈነቀለችው ድንጋይና ያልደከመችበት ጥረት ባይኖርም፤ ዛሬ የምትወዳትን እናቷን በሞት መነጠቋ እጅግ መሪር ሐዘን ሆኖባታል።
🙏 የሐዘን መግለጫ፦
ለጀግናዋ አትሌታችን መሠረት ደፋር፣ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን። ለእናታችን ወ/ሮ አስቴር መንገሻ አምላክ ዘላለማዊ እረፍትን ይስጥልን።
#meseretdefar #ethiopia #mourning #athleticsethiopia #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
6 months ago
ዜና እረፍት🕯
የEBS ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ በድንገት ሕይወታቸው አለፈ!
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ተሰማ።
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች የነበሩት አቶ አማን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 2018 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ሲል ኢቢኤስ ቴሌቭዥን አስታዉቋል፡፡
የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ማኔጅመንት እንዲሁም ሰራተኞች በአቶ አማን ፍስሃጽዮን ህልፈት የተሰማቸውን መሪር ሃዘን ገልፀዋል።

7 months ago
8 months ago
ልዕልት ገሊላማርያም አረፉ
📌 ልዕልት ገሊላ (ወ/ሮ ገሊላማርያም ፍሰሃ ገ/ስላሴ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
#ethiopia | ልዕልት ገሊላ የቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት የልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ ባለቤት የነበሩ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን የሚያስረግጥ ነው።
ልዕልት ገሊላ የሚዘከሩት ንጉሳዊ ቤተሰብ ውስጥ የነበሩ ሰው በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ፣ ለኢትዮጵያዊያን ባላቸው ጥልቅ ፍቅር ጭምር ነው።
ልዕልቷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የድጋፍ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ፣በአለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ ባደረጉት ድጋፍ፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወገኖቻቸው ክብር እንዲጠበቅ ባደረጉት ጥረት ይዘከራሉ።
ልዕልት ገሊላ በሕይወት ሳሉ ከልዑል ኤርሚያስ ጋር ሁለት መንታ ልጆችን አፍርተዋል።
🕯የደራው መጽሔት ይህን ዜና እረፍት የሰማው ለንጉሳዊ ቤተሰቡ ቅርብ ከሆነው ከአቢዬ ገ/ህይወት ነው
ዝግጅት ክፍላችን ለልዕልት ገሊላማርያም ወዳጅ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።
የደራው መጽሔት

ዜና እረፍት!
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የአቡሻኽር፣ የፍትሐ ነገሥት እና የቅኔ መምህር፤ በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የክብረ ደናግል ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት የሆኑት አራት አይናው መምህር ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ነገ ማክሰኞ ኅዳር 23/2018 ዓ.ም የሚከናወን ይሆናል።
via: ተዋህዶ ሚዲያ

9 months ago
ዜና እረፍት ‼️
በኩላሊት ታካሚዎች ላይ በጎ አበርክቶ የነበራቸው ዶ/ር ሰለሞን አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የኢትዮጵያ ኩላሊት እጥበት በጎ አድራጎት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሰለሞን አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ማህበሩ በገንዘባቸው መታከም የማይችሉ በርካታ ህሙማን መድረስ የቻለ ነው።
በአሁን ሰዓት በማህበሩ ከአራት ሺህ በላይ የኩላሊት ታካሚዎች ዲያሊስስ የሚያደርጉ ሲሆን አንድ ታማሚ በወር ስልሳ ሺህ ብር እንደሚያስፈልገው ለብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።
ለማህበሩ አባላት የእጥበት፣ የህክምና ወጪ ለመሸፈን እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ለታማሚዎች በየዓመቱ የተወሰነ ነጻ የበረራ ትኬት እንዲሰጥ ለማስቻል ዶ/ር ሰለሞን አሰፋ ከፍተኛ ስራን ሰርተዋል።

#ethiopia | በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፖሊስና ኅብረተሰብ ቴሌቪዥን በዜና አንባቢነት፣ በፕሮግራም መሪነት እና በመድረክ አስተዋዋቂነት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ለበርካታ ዓመታት በታታሪነት፣ በታማኝነትና በቅንነት ስታገለግል የነበረችው ኢንስፔክተር ኪያ ንጉሴ ቱሉ ባጋጠማት ህመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በ40 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡
በመሆኑም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ዊንጌት ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት በመኮንኗ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቿ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

12 months ago
#ዜና_እረፍት
#ethiopia | በቢጣ ወረዳ ሸዳ ቀበሌ በስፔን መንግስት ድጋፍ የሴቶች ተጠቃሚነት ላይ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ የቆዩት የቦንጋ ዩንቨርስቲ መምህር እጩ ዶክተር ወርቁ አለሙ በድንገት ማረፋቸው ተገለፀ።
እጩ ዶ/ር ወርቁ አለሙ ሁለገብ መምህር ሲሆን በተለይ ደግሞ በቡና ላይ በሚያደርጋቸው ምርምሮቹ ይታወቃል።
በቅርቡ በስፔን መንግስት ድጋፍ በቢጣ ወረዳ በተጀመረው የተቀናጀ ግብርና ላይ ከማስተማሪያ ማንዋል ዝግጅት ጀምሮ የአካባቢውን ምርትና ምርታማነት በምርምር ለማገዝ እየታተረ የሚገኝ ጉምቱ ምሁር ነው።
የታሪክና ባህል አዋቂው የካፋ ባህላዊ ምክር ቤት /ሚክሬቾ/ አባል ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል።
በዛሬው ዕለት በሰማነው ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ስንገልጽ ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶች በሙሉ ፈጣሪ ፍፁም መፅናናትን እንዲሰጣቸው በመመኘት ነው።
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ

1 year ago
ዜና እረፍት !
ከፍተኛ መኮንኑ ፣ መሐንዲሱ ፣ ደራሲው ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው አርፈዋል።
የአባታቸውን ብ/ጀ ጌታቸው ናደው የውትድርና ፈለግ በመከተል የውትድርና ህይወትን መረጡ። የቀኃሥ ገነት ጦር ት/ቤት ምሩቅ መኮንን በመሆን የውትድርና ህይወት ሀ ብለው ጀመሩ። የአባታቸው በደርግ በግፍ መገደል ተከትሎ ለ7 አመታት በእስር አሳልፈዋል።
በመቀጠል የቀለም ትምህርት በመግፋት በሲቪል ምህንድስና ተመርቀዋል። በስራቸውም በወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እና ኤርፖርቶች ላይ አሻራቸውን አኑረዋል። ከመንግስት ለውጥ በኋላም በዚሁ የሲቪል ምህንድስና ሞያቸው ለረጅም አመት ሠርተዋል። በጡረታ ዘመናቸው እና የመኪና አደጋ ከደረሰባቸው በኋላም 3 መፅሀፍትን ፅፈው ለተደራሲያን አቅርበዋል።
ከጋዜጠኛ ደረጀ ሐይሌ ጋር ATRS TV "በነገራችን ላይ " በሚል ፕሮግራም በ3 ክፍሎች ተቀንብቦ በቀረበው ቆይታቸው ብዙ መሣጭ ታሪኮችን አጫውተውን ነበር። የተዋቂው ሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ አባት ናቸው።
የጀነራሉ ልጅ ፣ ወታደሩ ፣ መሐንዲሱ ፣ ፀኃፊው ሻለቃ ጳውሎስ ጌታቸው ነፍስን ፈጣሪ ይማር።
ለቤተሰብ ፣ ወዳጅ እና ዘመድ እንዲሁም ለባልደረቦቻቸው መፅናናትን ያድል።
Via: አብዮታዊው ሰራዊት ገፅ

#ethiopia | በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፉ ከነበሩት ተወዳጅ የውጭ ስራዎች መሃከል the Cosby show የተሰኝው ተከታታይ ድራማ አንዱ ሲሆን የድራማው ኮከብ ተዋናይ ማልኮልም ጀማል ዋርነር በ54 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

Comments