Logo
Getu Temesgen
ልዕልት ገሊላማርያም አረፉ

📌​ ልዕልት ገሊላ (ወ/ሮ ገሊላማርያም ፍሰሃ ገ/ስላሴ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
#ethiopia | ልዕልት ገሊላ የቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት የልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ ባለቤት የነበሩ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን የሚያስረግጥ ነው።

ልዕልት ገሊላ የሚዘከሩት ንጉሳዊ ቤተሰብ ውስጥ የነበሩ ሰው በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ፣ ለኢትዮጵያዊያን ባላቸው ጥልቅ ፍቅር ጭምር ነው።

ልዕልቷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የድጋፍ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ፣በአለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ ባደረጉት ድጋፍ፣ እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወገኖቻቸው ክብር እንዲጠበቅ ባደረጉት ጥረት ይዘከራሉ።

ልዕልት ገሊላ በሕይወት ሳሉ ከልዑል ኤርሚያስ ጋር ሁለት መንታ ልጆችን አፍርተዋል።

🕯የደራው መጽሔት ይህን ዜና እረፍት የሰማው ለንጉሳዊ ቤተሰቡ ቅርብ ከሆነው ከአቢዬ ገ/ህይወት ነው

ዝግጅት ክፍላችን ለልዕልት ገሊላማርያም ወዳጅ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል።

የደራው መጽሔት

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.